Friday, March 7, 2014

አንድነት በ17 ከተሞች ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊያደርግ ነው

 
bahr dar 19
አንድነት ፓርቲ ሁለተኛውን ዙር የሚሊኖች ድምፅለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ይፋ ማድረጉን አስታወቀ። ህዝባዊ ንቅናቄው የሚካሄድባቸው 17 ከተሞችም ተለይተው ታውቀዋል።
የድርጅቱ ልሳን ይፋ እንዳደረገው አንድነት ለዲሞክራሰና ለፍትህ ፓርቲ ዛሬ ይፋ ያደረገው የህዝባዊ ንቅናቄ መርሃግብር በተከታታይ ሊካሂዳቸው ካቀዳቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች መካከል አንዱ በየሆነውን የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት(Millions of voices for land ownership) የሚል ስያሜ የሰጠውን የህዝባዊ ንቅናቄ ነው፡፡ መረሃ ግብር በዛሬው እለት ይፋ የተደረገው ቀበና መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፊተ ለፊት በሚገኘው የፓርቲው ጽ/ቤት ነው፡፡ ህዝባዊ ንቅናቄው ይፋ በተደረገበት መግለጫ ላይ አንድነት የመሬትን ጉዳይ በአጀንዳነት በመምረጥ ህዝባዊ ንቅናቄ ለማድረግ የመረጠባቸው ምክንያቶች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡
በአዲስ አበባ በሚደረግ ትዕይንተ ህዝብ እንደሚጀመር የሚጠበቀው “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት” ህዝባዊ ንቅናቅ 14 ከተሞች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግና ሶስት ከተሞችም በተጓዳኝ ለህዝባዊ ንቅናቄው መመረጣቸው ታውቋል፡፡ ንቅናቄው የሚካሄድባቸው ከተሞች አዲስ አበባ ፣ደሴ ፣ሐዋሳ ፣አዳማ/ናዝሬት ፣መቀሌ ፣ደብረታቦር ፣ ደብረ ማርቆስ ፣ድሬ ደዋ፣ ጅንካ፣ ቁጫ፣ አሶሳ፣ነቀምት፣ለገጣፎ፣አዲስ አበባ ሲሆኑ ተጓዳኝ ከተሞቹ ወልዲያ፣ ጋምቤላ፣ ም/አርማጨሆ(አብርሃ ጅራ) እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አንድነት ፓርቲ ባለፈው ዓመት(2005ዓ.ም) ለሶስት ወራት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
ምንጭ፣ zehabesha.comhttp://www.zehabesha.com/amharic/archives/13427

No comments:

Post a Comment