እኔ እንኳን ብዙም ፀሐፊ ባልሆንም አንድ ወንድማችን የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ በመገኘት አጠር ባለ ሁኔታ አፍሪካ ውስጥ ስላለው የነፃ ሚድያ ስርጭት የሰጠው አጭር ተጨባጭ ገለፃ ስላስደሰተኝ እኔ ደግሞ ለምን በፅሑፍ መለክ በአጭሩ ለአምባብያን አላቀርበውም ብዬ ነው ይሄን ፁሑፍ ለመፃፍ የተነሳሳውት:: በዚ ፅሑፌ ላይ የተወሰኑ የአፍሪካ አገራትን የነፃ ሚድያ ሽፋናችውን ለማየት የምሞክር ሲሆን ብዙውን መረጃም የወሰድኩት ከዊኪፒድያ ዌብ ሳይት ነው::
በመጀመሪያ ኢትዮጲያን እንመለከት፣ ኢትዮጲያ ከአፍሪካ በህዝብ ብዛት በሁለተኛ ደረጃ የምትገኝ ስትሆን የነፃ ሚድያ ስርጭት በምንመለከትበት ጊዜ የመጨረሻዎቹን ደረጃ ትይዛለች:: ለዚህ ምስክር በ 2013 እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር የወጣው የአለም የነፃ ሚድያ ሰንጠረዥ ነው:: ኢትዮጲያ አንድ ዋና የቴሌቨዥን ፕሮግራም ማሰራጫ ጣቢያ ሲኖራት በዛ ውስጥም ኢቲቪ ይሰራጫል የተቀሩት አዲስ ቲቪ ፣ ቲቪ ኦሮሚያ እና ድሬ ቲቪ ግን በክልል የተወሰኑ ናችው:: ሌላው ከአስር ብዙም የማይበልጡ የግል እና የመንግስት የሆኑ አጭር ሞገድ እና የኤኤም ራዲዮ ማሰራጫ ጣቢያወች አሉዋት::ነገር ግን ሁሉም የቴሌቨዥን እና የራድዮ ስርጭቶች በመንግስት ቁጥጥር ስር ናችው:: በግለሰብ ደረጃ ድምፃችውን ለማሰማት የሚሞክሩትን ደግሞ የእስር ቤት እራት ይሆናሉ:: በተቃራኒው እዚው ጎሮቤት ሀገር ኬንያን እንመልከት ፣ ኬንያ የኢትዮጵያን ግማሽ ያህል ህዝብ ሲኖራት የሚያስገርመው ግን ከ አስራ አምስት በላይ የግልና የመንግስት የቴሌቭዥን ፕሮግራም ማሰራጫ ጣቢያወች ሲኖሯት ከ ዘጠና በላይ የኤፍኤም ማሰራጫ ጣቢያወች አሉዋት::ቁጥራችውም በጣም ብዙ የሆኑ ጋዜጣና መፅሔቶች በየእለቱ ይታተማሉ::የመንግስት ሚድያወች በተወሰነ መልኩ የመንግስት ተፅህኖ ሲኖርባችው ሁሉም የግለሰብ ሚድያወች ግን ከመንግስት ገለልተኛ ናችው::በጣም ብዙ