Friday, May 22, 2015

“በመመካከር ከራሷ ጋር የታረቀች አገር ጥንስስ እኛው ውስጥ እንፍጠር” -አርበኞች ግንቦት 7 -

አርበኞች ግንቦት 7 በመርህ ላይ በተመሠረተ ትብብር ወያኔን በጋራ ታግሎ ማሸነፍ እና በየደረጃው የሚገኝ የመንግሥት ስልጣን ነፃ፣ ፍትሀዊና ተዓማኒን በሆነ የሕዝብ ምርጫ ብቻ የሚያዝበት የፓለቲካ ሥርዓት መገንባት የአርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ተልዕኮ ነው። በዚህም መሠረት አርበኞች ግንቦት 7፣ በተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ከሚገኙት ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ ከጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ፣ ከቤንሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ እና ከአማራ ዴሞክራሲ ኃይል ንቅናቄ ጋር በመርህ ላይ በተመሠረተ ትብብር በጋራ ለመታገል የሚያስችለውን ስምምነት ላይ እየደረሰ ነው። 
ginbot 7

ይህ የትብብር ጥረት ብዙ ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጠንካራ ድጋፍ ይሻል። ህወሓትን ከስልጣን የማባረር ኃላፊነት የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ኃላፊነት ነው። ይህ ትልቅ ኃላፊነት በአንድ ወይም በጥቂት ድርጅቶች ላይ መጣል የለበትም። ይህ ትብብር ይህንን የጋራ ኃላፊነትን በጋራ ለመወጣት የተደረገ በዓይነቱ አዲስ የሆነ ተግባራዊ ትብብር ነው። ህወሓት በትግራይ ውስጥ መቶ በመቶ ተቀባይነት ያለው አስመስሎ ፕሮፖጋንዳ ሲነዛ ቆይቷል። ህወሓት፣ የትግራይና የአማራ ሕዝብ በጠላትነት እንዲተያዩ፤ የትግራይ ሕዝብ ራሱን ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጥሎ እንዲያይ የረዥም ግዜ እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ ነው። ይህን እኩይ ሴራ ማክሸፍ የምንችለው በፀረ-ወያኔ ተግባራዊ ትግል በጋራ ስንቆም ነው። ይህ ትብብር ለአገራችን አንድነትና ዘላቂ ሰላም ወሳኝ የሆነው በፀረ ህወሓት አቋሙ የጠነከረ የትግራይ ሕዝብ እንዲኖር ወሳኝ ሚና ይኖረናል ብለን እናምናለን። በአሁኑ ሰዓት የህወሓት አገዛዝ የቆመው ዘረኛ በሆነ መንገድ ባደራጀው ጦር፣ በስለላ ድርጅቱ እና ኃያላን መንግሥታት ለጥቅማቸው ሲሉ በሚያደርጉለት ሁለተናዊ ድጋፍ ነው። እነዚህ ህወሓትን ደግፈው የያዙ ኃይሎች ጠባቸው ከመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መሆኑን በተግባር የምናሳያቸው ተግባርን መሠረት ያደረገ ጠንካራ ኅብረት ፈጥረን ስንገኝ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ነባራዊ ማኅበራዊ ሀቅ ምክንያት ከፓለቲካ አመለካከት ይልቅ በወል ማንነት ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶች የሚበዙበት ሆኗል። የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት ሁለቱን አመለካከቶች መሠረት አድርገው በተደራጁ ድርጅቶች መካከል ትብብር መፍጠር ወሳኝ ነው። 
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከላይ በአጭሩ በተዘረዘሩት ምክንያቶች እየተፈጠረ ያለው ትብብር የኢትዮጵያን የፓለቲካ መልካምድር ወደተሻለ ሁኔታ ለመቀየር የራሱ አስተዋጽዖ ይኖረዋል የሚል እምነት አለው። በዚህም ምክንያት መጠናቀቅ የሚገባቸው ነገሮች ተጠናቀው ትብብሩ በይፋ እንዲመሠረት የበኩሉን ጥረት ያደርጋል። ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ሳቢያ የትብብር አድማሳችን ከዚህም መስፋት አለበት ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል። ስለሆነም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ለጊዜው የትብብር ማዕቀፍ ውስጥ ያልገቡ የፓለቲካ ድርጅቶች ወደ ትብብሩ እንዲመጡ፤ ለሀገራችን እና ለሕዝብ በጋራ መሥራት በምንችላቸው ጉዳዮች ላይ እንድመክር ጥሪውን ያስተላልፋል። በመመካከር ህወሓትን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን ለሁላችን የሚበጅ የተሻለ ሥርዓት በአገራችን ላይ እንዲመሠረት መሠረት መጣል እንችላለን ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 በጽኑ ያምናል። ስለሆነም እንነጋገር፤ ለሁላችን የሚበጀንን መንገድ በጋራ እንፈልግ፤ የህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝን በጋራ እንታገል፤ ከራሷ ጋር የታረቀች አገር ጥንስስ እኛው ውስጥ እንፍጠር ይላል። ለውጤታማ ትግል እንተባበር! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41535

Friday, February 27, 2015

የመለስ ትሩፋቶች ደራሲ ኤርሚያስ ለገሰ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጻፈው ግልጽ ደብዳቤ

ከአንድ ሰአት በላይ የፈጀውን ጥናታዊ ጵሁፍህን ሰማሁት። ሰምቼ ስጨርስ ደነገጥኩ። ከራሴም ጋር ለሰአታት ሙግት ገጠምኩ ። ኢህአዴግን ለቅቄ የወጣሁት ልቤ የፈቀደውን በነጳነት ለመናገር ነውና የማውቀውን እና የሚሰማኝን መናገር እንዳለብኝ ተሰማኝ ። ርግጥ በሐይማኖት ጉዳዬች ላይ መናገር ከባድ እንደሆነና ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠንቅቄ አውቃለሁ ። በሌላ በኩል የሚያውቁትን አለመግለጵም የፀፀት ዋጋ አለው። በመሆኑም ባለመናገሬ ከሚሰማኝ ሙግት መናገሩን ስለመረጥኩ የሚከተለውን አጭር አስተያየት ለመስጠት ተገደድኩ። 1• ያቀረብከውን መረጃዎች እንዴት እንዳሰባሰብካቸው የተገለፀ ነገር የለም። በተለይም በድህረና ቅድመ ምርጫ 97 ባሉት ሶስት አመታት( ከኃላም ከፊትም) ያቀረብካቸውን መረጃዎች ምንጭ ማወቅ እፈልጋለሁ ። ይህን ጥያቄ የማነሳበት መሰረታዊ ምክንያቶች ስላሉኝ ነው።

daniel kibret

 1•1• በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2001 አ• ም• ኢሕአዴግ ለሕዝቡ ይዞለት የመጣው እቅድ ” በአክራሪነት ” ስም ሀይማኖቶችን ማዳከም ነበር። ይህንንም ለማቀጣጠል እንዲረዳው በኢህአዴግ ቢሮ፣ በኮሙዩኒኬሽን ጵ/ ቤት፣ ፌደራል ጉዳዬች እና ፌደራል ፓሊስ መረጃ እንዲሰባሰቡ ተደረገ። የእስልምና ጉዳዬች ላይ ዝርዝር ጥናቱን እንዲሰራ የቤትስራ የተሰጠው ሽመልስ ከማል ነበር። ዛሬ አንተ ካቀረብክልን ውስጥ ግማሹ የቃላት ለውጥ እንኳን ሳይደረግለት በሽመልስ ከማል ጥናታዊ ፅሁፍ የቀረበ ነበር። በወቅቱ እጅግ ከመደንገጤ የተነሳ ሽመልስ እንዴት እንዲህ አይነት ጥናት እንደሰራ ለማወቅ ከጀርባው መጓዝ ነበረብኝ ። መጓዜ ያልጠበኩትን ውጤት አመጣ። ሽመልስ በእስልምና ላይ ከፍተኛ ጥላቻ የያዘው በቤተሰቡ ውስጥ በተፈጠረው ምስቅልቅል እድገት መሆኑን ተገነዘብኩ። አባቱ በአንድ ወቅት የመስኪድ አስተዳደር ነበሩ። በኃላ የሳውዲ ጉዞ አድርገው ሲመለሱ አስተዳደሩን በመነጠቃቸው ከሀይማኖቱ በተቃራኒ ተሰለፋ ። ” ከመካ መዲና ደርሶ መልስ” የሚል መጵሀፍ አሳትመው ክርስትና ተነሱ። ስማቸውም ወደ ሀይለየሱስ ተቀየረ። ባስታወቀው እርምጃ ቤታቸው ተመሰቃቀለ።ወንድማማች እና እህታማቾች የሚጠሩበት የአባት ስም እስከ መለያየት ደረሰ። ባጭሩ የሽመልስ ፀረ -እስላም የመሆን ምንጩ ይሄ ነው። በመሆኑም በሽመልስ ሲቀርቡ የነበሩ ዳታዎችና ትንታኔዎች እንደወረዱ ከአንተ ሲቀርቡ ስሰማ የመረጃ ምንጭህን ተጠራጠርኩ። በተለይ

Monday, February 23, 2015

የወያኔ ሚኒስተር ከ30 እስከ 40% የግንባታ ወጭ እንደሚዘረፍ አሳወቁ


1619564_780737625344507_8633815854074255488_n
የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና፣ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አምነዋል።
የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት በባቡር መስመር ግንባታ 2.3 ኪሜ የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 ሚልዮን በር ኪሳራ ደርሷል። የአደጋ መከላከያ ብረቶች የተሰሩት ከወጣላቸው የጥራት ደረጃ በሶስት እጅ ያነሱ ሆነው በመገኘታቸው ጉዳዩ ለቦርድ ሰብሳቢው ዶ/ር አርከበ እቁባይ ቢቀርብም ምላሺ ሰይሰጠው በመቅረቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገባ ማወቅ አለመቻሉን ገልጿል።
የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን ያቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ ምላሺ የሰጡት ሚኒስትር መኩሪያ ሃይሌ ፣ ችግሩ የተፈጠረው ለምርጫው ሲባል የባቡሩ ግንባታ እንደ ትልቅ የምርጫ ማሰመኛ በመያዙ ነው ።
የግንባታ ኢንዱስትሪው ከሚያወጣው ወጪ ከ30 እስከ 60 በመቶ የሚሆነው በሙስና ይባክናል ሲሉም ሚኒስትሩ አክለዋል። እንደዚያም ሆኖ በቅርቡ የተመረቀ የአዲስ አበባ መለስተኛ የባቡር ግንባታ፣ አገልግሎት ከመጀመሩ ከወዲሁ በርካታ የመፈራረስ ችግሮች እያጋጠሙት ነው። ለፖለቲካ ፍጆታና ለፕሮፖጋንዳ ሲባል ቶሎ ቶሎ እንዲሰራ ከማድረግ ዉጭ እነ አቶ አርከበ እቁባይ የሕዝቡን ፍላጎት ከግምት ያላስገቡ ሲሆን፣ አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች አልተወሰዱም። በዋናነት የባቡ ሃኢዱ ከተማዋን ለሁለት የከፈለ ሲሆን ከሃዲዱ በስተቀኝ እና በስተግራ ያሉ ነዋሪዎች ለመገናኘት እጅግ በጣም ብዙ ረቀት ለመጓዝ ተገደዋል።
ምንጭ: http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/17401