Wednesday, April 30, 2014

ሴቶችን አብዝቶ የሚፈራው መንግሥት

April 29, 2014
ቹቸቤJailed Ethiopian female bloggers, activists and journalists መነሻቸው ግልብ ጎጠኛነት መድረሻቸው መንደረተኛነት በመሆኑ በዘረፋ እየከበሩ በመለስ ራዕይ እያጨናበሩ ከመኖር ያለፈ ከእውነት ጋር ፊት ለፊት ተያይተው መኖር ያልቻሉት የትግራይ ጉጅሌዎች በወጣቶች ላይ የሚፈጽሙት ሰቆቃ አሳፋሪ ነው። በህጻናትና በሴቶች ላይ የሚበረቱ የማስተዋል ድርቅ የመታቸው፣ የእውቀት ረሀብ ያደነዛቸው ፍርሃት እንቅልፍ የነሳቸው ናቸውና ድፍረት ያላቸው ህጻናት ያስፈሯቸዋል እውነት የያዙ ሴቶች ያስደነግጧቸዋል። ለዚህ ነው የወጣቶችን ግንባር በምንደኛ ጦር ሲነድሉ ወጣት ሴቶችን ሲደፍሩ ሲያስደፍሩና ሲያዋርዱ ደስታን የሚያገኙት።
አብዛኞቹ በዚህ ጎጠኛ ቡድን የሚንገላቱት ወጣቶች ወያኔ በገባበት ዘመን የተወለዱ ወይም ገና ድክድክ የሚሉ ህጻናት ነበሩ። ሲነገራቸው የኖረውና ህይወታቸውን ሙሉ የተመለከቱት ኢትዮጵያ ስትዋረድ የሀገሪቱ ጀግኖች ሲሰደቡና ዘር በዘር ላይ ሀይማኖት በሀይማኖት ላይ የሚያነሳሳ ታሪክ ሲማሩ ነበር ያደጉት። ሬድዮ፣ ቴሌቭዥን ጋዜጣና መጽሄቱ ሁሉ የሰሩት የወያኔን ፕሮፓጋንዳ ነበር። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያዊነት ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እየገነነ፣ ለነፃነት የሚደረገው ትግል እየጠነከረ መምጣቱ ይልቁንም አፍራሹ ፕሮፓጋንዳና ድርጊት ጠንካራ ወጣት ወንዶችና ወይዛዝርቶችን ቁርጠኛ ታጋይ እንዲሆኑ አደረገ እንጂ ኢትዮጵያዊነት ሲሞት አላየንም።
ከዚህ መማርና መለወጥ የሚቻል ቢሆንም ኢትዮጵያዊነትን ያሟጠጠ አእምሮው በጥላቻ የሰከረን መመለስ እንደማይቻል መመልከት አሳዛኝ ነው። “የሚያድግ ልጅ አይጥላህ” የሚባለው ተረት የሚያስተምር ቢሆን በወጣቶች ላይ የሚሰራውን ግፍ ቀነስ ማድረግ በተቻለ ነበር። እኒህ ወጣቶች ይቅር ባይ እንጂ ቂመኛ እንዳይሆኑ ግን ምኞቴ ነው።
እነዚህ ክፉዎች በየቀኑ የሚተክሉት የጥላቻ ችግኝና የእልቂት ድግስ የመቶ አመቱን በደል አስታውሶ ከሚያጫርሰው በላይ ዛሬ የሚደርሰውን ግፍና በደል አጉልቶ የሚያሳይ በመሆኑ የታች አምናውን ሳይሆን የትናንቱን የወያኔን ሕዝብ ከመኖርያ ማፈናቀል፣ ገበሬዎችን መበተን፣ የሀገር ድንበር መቁረስን፣ በአማራና ኦሮሞ ላይ እየተኪያሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት እያስታወሰ የሕዝብ ሃይል መልሶ ጠራርጎ እንደሚያጠፋቸው አለማወቅ የግብዝነትና የድንቁርና ምልክቱ ነው። በዘመነ ደርግና በንጉሳውያኑ ዘመን ከሆነው ሁሉ የበለጠ ግፍና በደል የተፈጸመው በነዚህ ጎጠኞችና የሀገር ጠላቶች እንደሆነ ለመናገር እዚያው ትግራይ ያለውን ተቃውሞ ምሳሌ ማድረግ ይበቃል። ጎጠኞቹ ልብ ያላሉት የታቀፉት የእባብ እንቁላል እነሱኑ ቀድሞ እንደሚነድፍ ነው። ይህ እንደሚሆን ለማወቅ በሀገሪቱ ከተበተኑት ሰላዮች መስማት የሚፈልጉትን ብቻ ሳይሆን እውነት እንዲናገሩ ብቻ ቢፈቅዱላቸው እንኳ ያንዣበባቸውን አደጋ ባወቁት ነበር።
ርዕዮት አለሙ ጽንፈኛና አሸባሪ ልትባል የምትችልበት ምንም መረጃ የለም። ወያኔዎችን ያስፈራው እውነትን መያዝዋና ድፈረቷ ብቻ ነው። ርዕዮትን ማሸማቀቅ ሌሎችን ለማስፈራራት የተወሰደ እርምጃ ነበር ግን ውጤቱ በተቃራኒው ሆነ። እናም አነሆ ወይዛዝርቶቹ ተነሱ! ስለወያኔ ክፋት ሳይሆን ስለሕዝባችን ብርታትና መነሳሳት የምናወጋውም በኩራት የሚሆነው ለዚህ ነው።
ሴቶች ትግሉን አልተቀላቀሉም፣ ብዙዎቹ ወደሁዋላ ይላሉ እንላለን ጥቂት ግን በጣም ጥቂቶቹ ደፍረው ሲወጡ ከጎናቸው ልንቆምና በየአቅጣጫው ልንታገልላቸው ይገባል። ርዕዮት እድሜዋ ገና ሰላሳዎቹ ውስጥ ያለች ወጣት ትዳር ያልመሰረተችና ልጅ የሌላት ብዕረኛ ናት። ትዳሩ ይቅር ልጅም አይኑራት ነገር ግን ለህይወትዋ አስጊ በሆነ የጤና ችግር ላይ መሆንዋ እየታወቀ ህክምና እንዳታገኝ ማድረጉ አሰቃይቶ የመግደል እኩሌታ ነው። ይህ የግፍ ጽዋ ሞልቷል። ወጣቱ ቆርጦ ተነስቷል።
ምስላቸው ከዚህ ጽሁፍ ጋር የሚታየው ወጣቶች የእስርቤት ሰለባ ይሆናሉ ብሎ ማሰብ በጣም ያሳዝናል። ይሁን እንጂ ሁላቸንንም የሚያበረታቱ የጣይቱ የዘር ግንድ የጀግኖች የዜግነት ውርስ በዚህ ትውልድ ደም ውስጥ መፍሰሱን ስለሚያመለክቱ ተስፋ ይሰጡናል ብርታትም ይሆኑናል። እኒህ ወጣቶች ከታሰረው ከሰፊው ሕዝብ ጋር ተቀላቅለው ለነጻነት ለሚደረገው ትግል አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ተባብረን እንነሳ! ከትንሹ እስር ቤት ወደ ትልቁ ይመጡ ዘንድ ድምጻችንን እናሰማ። አብረንም ሆነን የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልስ። ኢትዮጵያችንንም ነፃ እናውጣ!
ኦህ ኢትዮጵያ ባንቺ ተሰፋ አይቆረጥም… ልጆችሽ የነጻነት ዐየርን ይተነፍሱ ዘንድ በጀግንነት እንታገላለን… ሁሌም የመከራ ገፈት የሚቀምሱትና የበደል ጫና አንገት ያስደፋቸው የሀገራችን ሴቶች በሀገራቸው ኮርተው አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲሄዱ የድርሻችንን ሁሉ እናበርክታለን።
ምንጭ፣ http://ecadforum.com/Amharic/archives/12072/

Saturday, April 26, 2014

ከሰማያዊ ፓርቲ የሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በየሃይማኖታችሁ ጣልቃ ለተገባባችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የተደረገ ጥሪ!

 
by admin
ቀን 18/08/ 2006 ዓ.ም
ውድ ሃይማኖታችሁ ላይ ጣልቃ እየተገባባችሁ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፡- ሰማያዊ ፓርቲ ኢትዮጵያውያን በነጻነት የፈለጉትን ሃይማኖት እንዲከተሉ፣ የፈለጉትን እምነት እንዲይዙ ባለው የጸና አቋም ገዥው ፓርቲ በሙስሊሙና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ እያደረገ ያለውን ጣልቃ ገብነት ሲቃወም ቆይቷል፡፡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ገዥው ፓርቲ በሐይማኖቱ ጣልቃ መግባቱን ተቃውሞ የሚያደርገውን ፍጹም ሰላማዊ እንቅስቃሴ በማድነቅ ገዥው ፓርቲ ከህገ ወጥ ተግባሩ እጁን እንዲሰበስብ ምክር ከመለገስ አልፎ በሰላማዊ ሰልፍም ድምጹን አሰምቷል፡፡ በተጨማሪም የሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የተወሰደው ህገ ወጥ እርምጃ እና በእስር ላይ እየደረሰባቸው ያለውን ስቃይም በጽኑ ሲቃወም ቆይቷል፡፡ ወደፊትም በዚሁ አቋሙ እንደሚቀጥል ይገልጻል፡፡
blue party
በተመሳሳይ በክርስቲያኖች በተለይም በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ያለውን ጣልቃ ገብነትም በተመሳሳይ ሲቃወም ቆይቷል፡፡ ለአብነት ያህል በዋልድባ ገዳም ላይ የተወሰደውን ህገ ወጥ ተግባር በግልጽ ተቃውሟል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለይም በማህበረ ቅዱሳን ላይ ጫና እየተደረገ እንደሚገኝ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በማህበሩ ላይ ሊደረግ የታሰበው ሴራ እየተከታተለ ይገኛል፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንም ሆነ በማህበሩ ላይ እየተደረገ

Wednesday, April 23, 2014

በጎንደር 30 ሺህ ቤቶች እንደሚፈርሱ ታወቀ – ‹‹በከተማዋ ውጥረት ነግሷል››

by admin
የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)
የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)
ጎንደር፡- በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ከ30 ሺህ በላይ ቤቶች የተገነቡባቸው ሶስት ሰፈሮች ሊፈርሱ መሆኑን በስፍራው የሚገኙ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አስታወቁ፡፡ በከተማዋ ቀበሌ 18 ከተመሰረቱ ከ7 አመት በላይ የሆናቸው አርማጭሆ፣ ገንፎ ቁጭና ህዳሴ የተባሉ ሰፈሮች ውስጥ የተገነቡ ከ30 ሺህ የሚልቁ ቤቶችን እንዲያፈርሱ ለነዋሪዎች ትዕዛዝ በተሰጠበት ስብሰባ የተካፈሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

በስብሰባው ላይ ነዋሪዎቹ፣ ‹‹ህገ ወጥ ከሆነ ያኔ ሕገ ወጥ ነው ልትሉን ይገባ ነበር፡፡ ህገ ወጥ ነው ከተባለስ ይህ ሁሉ ዜጋ በርካታ ገንዘብ አፍስሶ ቤት ከሰራና ለ7 አመት ከኖረ በኋላ ህጋዊ ማድረግ አይቻልም ነበር? ይህም ካልሆነ ተለዋጭ ቦታ ተሰጥቶንና ሰፊ ጊዜና ተለዋጭ ጊዜ ተሰጥቶን
እንጂ በድንገት ተነሱ ልትሉን አይገባም›› የሚል መከራከሪያ ማንሳታቸው ታውቋል፡፡ በተጨማሪም፣ ‹‹እኛ የራሳችን አገርና ቦታ ላይ የምንገኝ ዜጎች ነን፡፡ ቤታችንን የሰራነው ማንም ሳያግዘን በራሳችን ጥረት ነው፡፡ የኤርትራ፣ የሱዳን፣ የሶማሊያ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው ሲገቡ የሚገባቸው ነገሮች ይሰጣቸዋል፡፡ እኛ ግን ያለምንም ቅድመ ዝግጅት፣ ካሳና ተለዋጭ ታ ሳይሰጠን ቤታችሁን አፍርሱ መባላችን ዜግነታችንም ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ነው›› ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡
የከተማዋ ባለስልጣናት በበኩላቸው፣ ‹‹መንግስት ህገ ወጥ ነው ብሎ የሚያምነውን ሁሉ ማፍረስ መብቱ ው፡፡ አይደለም ጎንደር አዲስ አበባ ውስጥም ቤት ይፈርስባቸዋል፡፡›› በሚል ለማሳመን ሞክረዋል፡፡ ‹‹በዚህ ጊዜ ውስጥ ልጆቻችን ይዘን የት ልንሄድ ነው… ሽማግሌዎችስ የት ይደርሳሉ?›› የሚሉ ሌሎች አንገብጋቢ ጥያቄዎችን አንስተው አጥጋቢ ልስ ያላገኙት ነዋሪዎቹ ከባለስልጣናቱ ጋር ባለመስማማታቸው አብዛኛዎቹ ‹‹ማፍረስ ከተፈለገ እናንተው አፍርሱት እንጂ እኛ አናፈርስም፡፡›› በሚል ስብሰባውን አቋርጠው መውጣታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ነዋሪዎቹ እስከ ሚያዚያ 7 አፍርሱ፣ ካለፈረሳችሁ እኛው ስለምናፈርሰው እቃችሁን አውጡ ቢባሉም አሁንም ድረስ በአቋማቸው ጸንተው የሚመጣውን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ምንጮቻችን ጨምረው ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል ህዝቡ በክረምት ተፈናቅሎ የት ይደርሳል በሚልና እንዲፈርስ በሚፈልጉት
የከተማው ባለስልጣናት መካከል ውጥረት መንገሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም ህዝብን አሳምጻችኋል የተባሉ 12 ሰዎች መታሰራቸውና ከጎንደር በተጨማሪ ቆላ ድባና ሌሎች ከተሞችም ቤቶች እንዲፈርሱ ትዕዛዝ መሰጠቱን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በተመሳሳይ ከሰሞኑ በባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎችን ከማፈናቀል ሂደት ጋር በተገናኘ ህዝብና ፖሊስ በመጋጨታቸው የሰው ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡

Friday, April 18, 2014

በሱሉልታ ከተማ የአማራ ተወላጆች ናችሁ የተባሉ ተደበደቡ(ናፍቆት ዮሴፍ)

ሶስት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በአዲስ አበባ የተለያዩ ሆስፒታሎች ገብተዋል
“ረብሻውን ያነሱት ህዝብን የማይወክሉ ወሮበሎች ናቸው” የከተማው ኮሙዩኒኬሽን
“ባህርዳር በተካሄደው የስፖርት ውድድር ላይ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ አድልዎ ተፈጽሟል” በማለት የተቧደኑ ወጣቶች፣ ባለፈው ሐሙስ የሱሉልታ ከተማ ነዋሪ የሆኑ በርካታ የአማራ ተወላጆች ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡
በድብደባ በርካታ ሰዎች ከመጐዳታቸውም በተጨማሪ፤ ቤት ንብረት ላይም ጥፋት እንደደረሰ የተናገሩት ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ጉዳዩን ሕገወጥ ነው ሲሉ አውግዘውታል፡፡ የከተማዋ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ፤ የስፖርት ውድድርን ሰበብ በማድረግ ረብሻ የቀሰቀሱ ሰዎች ህዝብን የማይወክሉ ወሮበሎች ናቸው ብለዋል፡፡
ረብሻውን ቀስቅሰዋል ተብለው ከተጠረጠሩት ውስጥ አራቱን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለም ገልፀዋል ሃላፊው፡፡ “የቤቴ በርና መስኮት እንዳልነበር ሆኗል፤ አጥር ተገነጣጥሏል፤ መስኮቶች ዱቄት ሆነዋል” ያሉት አንድ የከተማዋ የረጅም ጊዜ ነዋሪ፤ ከ30 በላይ ቤቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ የስድስት ልጆች እናት እንደሆኑ የገለፁልን ሌላዋ ነዋሪ፤ በቤታቸውና በንብረታቸው ላይ አደጋ መድረሱን ጠቅሰው፤ እንደሌሎች ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ባያጋጥማቸውም በእጃቸው ላይ በደረሰባቸው ጉዳት በከተማዋ አንድ ክሊኒክ ህክምና እንደተደረገላቸው ተናግረዋል፡፡
“ይህ ህዝቡ በሰላም አብሮ እንዳይኖርና እንዳይግባባ ሆን ተብሎ የሚጫር የነገር እሳት ነው” ያሉት የ56 አመት አዛውንት በበኩላቸው፤ መንግስት መፍትሔ ከላበጀለት በቀር በአሁኑ ወቅት ከየአቅጣጫው የምንሰማው በዘር ተቧድኖ ግጭት የመፍጠር ጉዳይ አስጊ ነው ብለዋል፡፡
የከተማው አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መሳይ ከበደ፤ ከከተማ አስተዳደር በደረሳቸው ሪፖርት ተዘዋውረው እንደተመለከቱ ገልፀው፣ የተወራውን ያህል ባይሆንም የስምንት ቤቶች የበርና የመስኮት መስታወቶች ተሰባብረዋል፤ የቆርቆሮ አጥሮች ተገነጣጥለዋል ብለዋል፡፡ ሰዎች አራት እንደተጐዱና የሶስቱ ሰዎች ጉዳት ከፍተኛ ስለሆነ በአዲስ አበባ የተለያዩ ሆስፒታሎች ውስጥ በክህምና ላይ መሆናቸውን አቶ መሳይ ጠቅሰው፤ አንዲት እናት በእጃቸው ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸው በከተማው ጤና ጣቢያ ታክመው ተመልሰዋል ብለዋል፡፡
“የረብሻው መንስኤ በቅርቡ ባህርዳር የተካሄደው የመላው ኢትዮጵያ ጫዋታዎች ውድድር ላይ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ አድልዎና ተፅእኖ ተደርጓል የሚል ሰበብ ነው” ብለዋል አቶ መሳይ፡፡
“በረብሻው ዙሪያ ህዝቡንና የከተማ ነዋሪውን በመሰብሰብ ረብሻውን ያስነሱት ሰዎች ህዝብን የማይወክሉ እና ህዝብን ለማጋጨት ፍላጎት ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች መሆናቸውን ተወያተናል” ያሉት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊው፣ ህዝቡ እንዲህ ዓይነት ቡድኖችም ሆኑ ግለሰቦችን አሳልፎ እንዲሰጥ ተግባብተናል ብለዋል፡፡ ረብሻው ወዲያውኑ በፖሊሶችና ከጫንጮ በመጡ የፀጥታ ኃይሎች መቆሙን ተናግረዋል – ሃላፊው፡፡
ምንጭ፣ http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/14008

Monday, April 14, 2014

US Embassy in Addis Warned US Citizens to take Precaution Measures during the up Coming Anti-Gay Demonstration


by admin
US Embassy in Addis has released the following message to its citizens
Security Message for U.S. Citizens: Event and Demonstration Planned for April 12 and April 26
On April 12, a panel discussion described as “Fighting Homosexuality in Ethiopia” is scheduled to take place at the Addis Ababa City Hall, located in Piazza, near the St. George Cathedral. At least 1,500 participants are expected to attend the event. Additionally, on April 26, a demonstration described as “anti-homosexual” has been approved by government officials to take place in Addis Ababa. At this time, the Embassy has no information about the location of this demonstration. These events could involve inflammatory and emotional statements. U.S. citizens are advised to avoid these events.
USA-flag
Even demonstrations intended to be peaceful can turn confrontational and escalate into violence. You should avoid areas of demonstrations, and exercise caution if in the vicinity of any large gatherings, protests, or demonstrations.
Remember to review your personal security plans; remain aware of your surroundings, including local events; and monitor local news stations for updates. Maintain a high level of vigilance and take appropriate steps to enhance your personal security.
We strongly recommend that U.S. citizens traveling to or residing in Ethiopia enroll in the

Sunday, April 13, 2014

ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

 
by admin
Blue Advert April 12
አዲስ አበባ፡- ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የተነጠቁ መብቶችን እናስመልስ!›› በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከአሁን ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ጥያቄዎቹ ምላሽ ያልተሰጣቸው ከመሆኑም ባሻገር ጭራሹን እየተባባሱ በመምጣታቸውና ህዝብም እየተማረረ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉን መጥራት እንዳስፈለገ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 2005 ዓ.ም ያደረገውን ጨምሮ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን ባደረገበት ወቅት የኑሮ ውድነት፣ የእምነት ጣልቃ ገብነት፣ ሉዓላዊነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀልና ሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎችን አንስቶ የነበረ ቢሆንም ጥያቄዎቹ ምላሽ ሊያገኙ እንዳልቻሉ የህዝብ ግንኙነቱ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ በእስልምና እና ኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደረገው ጣልቃ ገብነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉ፣ የኑሮ

Friday, April 11, 2014

የኢትዮጵያ መንግስት በረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ላይ ክስ መሰረተ (ተመስገን ደሳለኝ)

 
-ከ253, 336 ከ42 ሳንቲም ዩሮ በላይ ኪሳራ ደርሷል ተብሏል
-የአእምሮ ችግር እንዳሌለበትም ተረጋግጧል
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ፍትሕ ሚኒስቴር በረዳት አብራሪ ኃይለመድን አበራ ላይ የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ.ም ሌሊት የበረራ ቁጥር ET 702 የሆንን ቦይንግ አውሮፕላንን ከእነ 202 ተሳፋሪዎቹ ወደ ሮም በሚበርበት ወቅት ጠልፎ ሲውዘርላንድ አሳርፏል በማለት በከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መመስረቱን የፍትሕ ሚኒስቴር ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡
በኃይለመድን ላይ የቀረበው ክስ ሁለት ሲሆን፤ የመጀመሪያው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 507/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፡-
‹‹…በዋና አብራሪ ፓትዮዝ ባርቤሪ አማካኝነት ከአዲስ አበባ በሱዳን በኩል ወደ ጣሊያን ሀገር ሮም ከተማ መንገደኞችን ለማድረስ በማጓጓዝ ላይ እንዳለ ዋናው አብራሪው የበረራ መቆጣጠሪያውን ክፍል ከውስጥ በመቆለፍ፣ ያለፍቃድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ

በባህር ዳር በተነሳ ግጭት ፖሊስ በጥይት ሕዝብ በድንጋይ ተከታከቱ፤ የሞቱም የቆሰሉም አሉ

 
(የባህር ዳር ከተማ)
(የባህር ዳር ከተማ ፎቶ ፋይል)

ለዘ-ሐበሻ ከባህዳር የደረሱ መረጃዎች እንዳመለከቱት ዛሬ በከተማዋ በፖሊስና በህብረተሰቡ መካከል በተደረገ የተኩስና የድንጋይ ውርውራ ልውውጥ ሰዎች ሞተዋል፤ የቆሰሉም አሉ፡፡ ፖሊስና ልዩ ሃይል በጥይት፤ ሕዝቡ በድንጋይ ባደረጉት መከታከት ከፖሊስም እንዲሁ የቆሰሉ እንዳሉ ተገልጿል፡፡

ዜናውን ያደረሱን የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ተኩሱ ለተከታታይ ሶስት ሰዓታት የተደረገ ሲሆን ህዝቡ “ቤታችን ለአምስትና ስድስት ዓመታት ያህል ሰርተን እየኖርንበት ያለ እና ሌላ ተለዋጭ ቤት የሌለን በመሆኑ ወይ ተለዋጭ ቦታና ቤት ስጡን ወይም ደግሞ የትንሳኤን በዓል እንኳን እንዋል አታፍርሱብን፤ ሌላ መቀመጫ የለንም” ብሎ ሲጮህ ማፍረሱን ቀጥለው፤ በፖሊስ እና ሚሊሻ የታጀበው አፍራሽ ከህዝቡ ጋር ግጭት ጀምሮ… የተኩስ እሩምታ ህዝቡ ላይ መተኮስ በመጀመራቸው ህዝቡም ምላሽ

ባህር ዳር ከተማ የሰዎችን ህይወት የነጠቀ ግጭት ተነሳ ተኩሱ አሁንም እንደቀጠለ ነው (ሰበር ዜና)

By Nebiyu Hailu -

በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 ሜትሮሎጂ ጀርባ በተለምዶ ዝንጀሮ ወንዝ በሚባለው አካባቢ የከተማው አስተዳደር የመኖሪያ ቤቶችን በግሬደር ማፍረሱን ተከትሎ በአካባቢው ነዋሪዎችና በታጣቂዎች መካከል በተነሳ ግጭት ሁለት ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ከሶስት በላት ሰዎች መሞታቸውን የአይን ምስክሮችን ጠቅሰው ዘግበዋል፡፡ ከስፍራው እየደረሰን የሚገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ግጭቱ እየተባባሰ የመጣ ሲሆን ተኩሱ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
ምንጭ፣ http://ethioforum.org/

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ቀዳሚ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ሆነ

 
ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ በ2005 በጀት ዓመት ከኤክስፖርት ካገኘችው ገቢ ይበልጥ በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊን በሐዋላ መልክ ያገኘችው ገቢ እንደሚበልጥ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ የጹሑፍ መረጃ አመልክቷል።
መረጃው እንደሚያሳየው በ2005 በጀት ዓመት አገሪቱ ከኤክስፖርት 3.1 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን ኢትዮጵያውያን ከውጭ ከሚልኩት ገንዘብ ደግሞ 3 ቢሊዮን 9 መቶ ሚሊዮን ዶላር አግኝታለች፡፡ በ2004 በጀት ዓመትም ከሐዋላ እና ከኤክስፖርት ያገኘቸው ገቢ ተመሳሳይ ማለትም እያንዳንዳቸው 3.2 ቢሊየን ዶላር መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡
መረጃው የሐዋላ ገንዘብ በፍጥነት እያደገ ሲመጣ በአንጻሩ አገሪቱ እንደቡና ፣የቅባት እህሎችና ጥራጥሬና የመሣሠሉትን በመላክ የምታገኘው ዓመታዊ ገቢ እያሽቆለቆለ መምጣቱን ያሳያል፡፡
ESAT Radio Tuesday November 19, 2013የኤክስፖርት ዘርፍ ባለፉት ሶስት ዓመታት መንግስት ከያዘው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አንጻር አፈጻጸሙ ደካማ መሆኑን መረጃው የሚጠቁም ሲሆን ከገቢ ንግድ ጋር ያለው የንግድ ሚዛን ጉድለት እየሰፋ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን ያመለክታል፡፡በ2004 የገቢ ንግድ(ኢምፖርት) መጠን 11 ቢሊየን ዶላር ሲሆን በ2005 ዓ.ም ወደ 11. ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ብሎአል፡፡ የሸቀጦች የወጪ ንግድ ገቢ ከሸቀጦች የገቢ ንግድ ወጪ ጋር ሲነጻጸር በሚጠበቀው ደረጃ ዕድገት ባላማሳየቱ የንግድ ሚዛን ጉድለቱ በ2003 ዓ.ም ከነበረበት 5 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በ2005 ዓ.ም ወደ 8. ቢሊየን 400 ሚሊዮን ዶላር እንዲሰፋ ማድረጉን መረጃው ጠቁሟል፡፡ ይህን የንግድ ሚዛን ጉድለት ለማጥበብ መፍትሔው ኤክስፖርትን ማሳደግ ነውም ብሏል፡፡
እጅግ የተለጠጠ ነው በሚል ትችት የሚቀርብበት የመንግስት የአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት ታሳቢ

Thursday, April 10, 2014

ሰበር ዜና – የአዲስ አበባ መስተዳድር የእውቅና ደብዳቤ ጻፈ ፓርቲው አልተስማማም::

 
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ሊያደርገው ለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ የመስተዳድሩ የሰላማዊ ሰልፍና ማሳወቂያ ክፍል ዘግይቶ በጻፈው ደብዳቤ የሰልፉ ቀን በሌላ ፕሮግራም መያዙን በመጥቀስ የቀን ለውጥ እንዲደረግ መጠየቁ አይዘነጋም፡፡
ፓርቲው የቀረበውን አስተያየት በመቀበል ሰልፉ ለሚያዚያ 5 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲደረግ መወሰኑን በመግለጽ ለመስተዳድሩ አሳውቋል፡፡ሆኖም መስተዳድሩ ዕለቱ በታላቁ ሩጫ መያዙን በመጥቀስ ለፖሊስ ጥበቃ ለመስጠት የሚያስቸግረው በመሆኑ ሰልፉ ለሚያዚያ 4 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲደረግ የእውቅና ደብዳቤ ጽፏል፡፡ፓርቲው በመስተዳድሩ የተሰጠውን እውቅና አለመቀበሉን ለማሳወቅ ከፍተኛ አመራሮቹን ወደ ከንቲባው ጽ/ቤት ልኳል፡፡
በአሁኑ ሰዓትም አመራሮቹና የመስተዳድሩ ሰዎች በጉዳዩ ዙሪያ እየተነጋገሩ ነው፡
Andinet AA Application

ምንጭ፣ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/28987

Wednesday, April 9, 2014

የግብጹ እጩ ፕሬዘዳንት ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት የማይቀር መሆኑን አሳወቁ!

በግብፅ በቅርቡ ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ራሳቸውን በዕጩነት ያቀረቡት የሕግ ባለሙያው ሞርታዳ ማንሱር፣ ‹‹ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ካላቆመች ወታደራዊ ኃይል እጠቀማለሁ፤›› በማለት አስጠነቀቁ፡፡
አወዛጋቢና ስሜታዊ እንደሆኑ በይፋ የሚታወቁት የሕግ ባለሙያና ከሳምንት በፊት ደግም ዛማሌክ ለተባለው ታዋቂ የግብፅ እግር ኳስ ቡድን ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ማንሱር፣ ማስጠንቀቂያውን ያስተላለፉት ባለፈው እሑድ ፕሬዚዳንታዊ ውድድርን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ጦነርት በመክፈት የግብፅ ሕዝብን ጥቅም እንደሚያስከብሩም ተናግረዋል፡፡ የዓባይ ወንዝን በተመለከተ እ.ኤ.አ. በ1929 እና በ1959 የተፈረሙ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መኖራቸውን ያስታወሱት ማንሱር፣ ኢትዮጵያ ይህንን ስምምነት ወደጎን ብላ ግንባታውን መቀጠሏን ተቃውመዋል፡፡
‹‹ኢትዮጵያና ግብፅን ከማግባባት የተቆጠቡ ዓለም አቀፍ ተቋማት አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ በአቋሟ ፀንታ ግድቡን መገንባት ቀጥላለች፡፡ ኢትዮጵያ ወታደራዊ አቅም እንዳላት በመግለጽ ግብፅን እያስፈራራች ነው፡፡ ነገር ግን ግብፅም ወታደራዊ አቅም አላት፤›› ብለዋል፡፡
Mortada Mansour
Mortada Mansour
ከኢትዮጵያ ጀርባ እስራኤል እንዳለች የተናገሩት ማንሱር፣ ይህ ቢሆንም የግብፅን የውኃ ድርሻ ለመገደብ የሚደረግ ጥረት ለግብፃውያን የሞትና ሽረት ጉዳይ ነው ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
‹‹ወደ ግድቡ የጦር ጄኔራሎቻቸውን ወስደው እየፎከሩ ግብፅ ከመጣች የሚሉ ከሆነ ግብፅም ጄኔራሎችና ተዋጊ ጄቶች እንዳላት ይወቁ፡፡ ግብፅ ጠብታ ውኃ እንዲጎድልባት አትፈቅድም፡፡ በዚህ ጉዳይ አንደራደርም፡፡ ይህ ለግብፃውያን ሞትና ሽረት ነው፤›› ብለዋል፡፡ ለግብፅ ፕሬዚዳንትነት ራሳቸውን በዕጩነት ያቀረቡት ማንሱር ገና ወደ ውድድር ለመግባት የግብፅ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ኮሚሽንን ይሁንታ ማግኘት እንደሚጠበቅባቸው የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
የሕግ ባለሙያው ማንሱር የኮሚሽኑን ይሁንታ እንኳን ማግኘት ቢችሉ የሚወዳደሩት በቅርቡ ከግብፅ መከላከያ ሚኒስትርነትና

Monday, April 7, 2014

Independent Magazine in Ethiopia Shut Down


 
By Betre Yacob
ebonyOne of the few independent Ethiopian magazines, Ebony, has been shut down after 6 years of publishing, putting many full-time and part-time workers out of a job. Tessema Dessalgn, the share holder and editor in chief of the magazine, told to journalists today that they had closed the magazine because of exaggerated tax.
“We hadn’t other option but to shut down the magazine” Tessema told to journalists. “The tax was so exaggerated, and impossible to us to manage. We didn’t have even the half of the requested amount”, he explained. Tessema said that the tax had come while they had already been in a serious financial

Thursday, April 3, 2014

“የእሪታ ቀን” እንዲሰረዝ የኢህአዴግ መንግስት ጠየቀ (ደብዳቤውን ይዘናል)

(EMF) በአንድነት ፓርቲ አማካኝነት – መጋቢት 28 ቀን፣ 2006 ሊደረግ የነበረው የ እሪታ ቀን በአዲስ አበባ መስተዳድር ተቃውሞ ገጥሞታል። ከአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የወጣው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ከሆነ፡ ሰልፈኞቹ የሚሄዱበት ስፍራ የተከለከለ በመሆኑ የሰላማዊ ሰልፉን ጥያቄ እውቅና አንሰጠውም ብሏል። ቀበና መድሃኔአለም ከሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ተነስቶ በፒያሳ እና ቸርችል ጎዳና አድርጎ፤ ጥቁር አንበሳ ድላችን ሃውልት ጋር ይጠናቀቅ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ፤ የአዲስ አበባ አስተዳደር ጽ/ቤት… መንገዱ የባቡር መስመር የሚዘረጋበት፣ ትራፊክ የሚበዛበት እና ሆስፒታል የሚገኝበት መሆኑን በመግለጽ ነው፤ ለሰልፉ እውቅና የነፈገው። ይህ በ’ንዲህ እንዳለ የአንድነት ፓርቲ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰልፉን የሚያካሂድ መሆኑን

Wednesday, April 2, 2014

የሰው ለሰው ድራማ 6 ሚሊዮን ብር የት ደረሰ? * በአካውንቱ ውስጥ 78 ብር ብቻ ነው የተገኘው


 
sew le sew
በርናባስ
(ለሎሚ መጽሔት እንደጻፈው)
በኢትዮጵያ ውስጥ ጥበብ በሁለት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፡፡ የመጀመሪያው በአሁን ሰዓት ደራሲዎችም ሆኑ የጥበብ ባለሙያዎች አዲስ ነገር ይዘው መምጣት ካለመቻላቸው ጋር በተያያዘ በህብረተሰቡ ዘንድ ቦታ እያጣ መምጣቱ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደረጃ ደግሞ ጥበብን ንግድ ያደረጉ አርቲስቶች መበራከት በራሳቸው አንገት ላይ ሸምቀቆ በማሰር ጥበቡን እየገደሉት ይገኛሉ፡፡ በአሁን ወቅት ምናልባትም ጥበብ ያለ ንግድ የታባቱ ያለ የጥበብ ሥራን ከተመለከትን ያለምንም ጥርጥር ‹‹ሠው ለሠው›› ድራማን በግንባር ቀደምትነት ማየት ይቻላል፡፡ ሲጀመር በርካቶች ለመመልከት የተሻሙበት ዛሬ ላይ ግን ‹‹ይህ ነገር አያልቅም እንዴ?›› ተብሎ የተለያየ ሂስ እየተሰጠበት ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ ውስጥ እንደ ሠው ለሠው የዘመኑ ማለቂያ አጥቶና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም መረን የለቀቀ ዕድል የሰጠው የለም፡፡
መቼም በየሣምንቱ እንደምንመለከተው ከሆነ የሠው ለሠው ድራማ ሃሣብ አልቆበት እዛው በዛው መዳከሩ ብቻ ሣይሆን፣ ገንዘብ የማባከንና የመዝናናትንም ነገር እየተመለከትን ነው፡፡ ከድራማው መውረድ ጐን ለጐን ካላስፈላጊ ታሪኮችም ጋር ተደማምሮ አሁን በተለይ ተዋናዮቹ እራስን የማዝናናት ጊዜ ላይ የደረሱ ይመስላል፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ ምናልባትም ለሌሎች ባይገባም መስፍን

በሐዋሳ ከተማ 2 ትምህርት ቤቶች በቋንቋ የተነሳ ብጥብጥ ተነስቶ ሰዎች ቆሰሉ


 
hawasa federal policeከዳዊት ሰለሞን
በሀዋሳ ከተማ ታቦር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚማሩ የሲዳማ ተወላጆች የሚኒ ሚዲያ ፕሮግራም በሲዳመኛ ቋንቋ ይተላለፍ፣ ታቦር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚለውን ታፔላ በሲዳመኛ ቋንቋ ይጻፍ በሚል መነሻና ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ረብሻ ተፈጥሮ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ግቢው ሲጠጉ ተማሪዎቹ ድንጋይ በመወርወር በርካታ ፖሊሶች ቆስለዋል፡፡ ፖሊሶቹ በወሰዱት ርምጃ ብዙዎች ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡
በሐዋሳ ከተማ በሚገኙ ሁለት የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች እንደቀሰቀሱት በተገመተ ረብሻ ከፍተኛ ጉዳት በተማሪዎችና በአስተማሪዎች ላይ መድረሱ ተሰምቷል፡፡
የትምህርት ቤቱ የመማሪያ ቋንቋ እንዲለወጥ በጠየቁ የኦሮሞ ተወላጆችና በሲዳማ ተወላጆች መካከል ረብሻው መቀስቀሱን ከስፍራው ያናገርኳቸው ሰዎች በስልክ ገልጸውልኛል፡፡ ረብሻውን ለማብረድ ፖሊሶች መሳሪያ መተኮስ በመጀመራቸውም የተጎዱ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ሐዋሳ ውስጥ የተኩስ ድምጽ ያለ ማቋረጥ እንደሚሰማም ምንጮች ተናግረዋል።