Sunday, March 16, 2014

አንድነት እና መኢአድ የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት ፊርማ ሊፈራረሙ ነው


 

 

UDJ
aeupየአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤትና የመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት አባላት በጋር ባካሔዱት ስብሰባ ሁለቱ ፓርቲዎች የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት ፊርማ እንዲያደርጉ መመሪያ ማስተላለፋቸውን ስብሰባውን የተከታተለው የፍኖተ ነፃነት ባልደረባ ዘገበ፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ላዕላይ ምክር ቤት አባላት ዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት ባደረጉት ስብሰባ የሁለቱ ፓርቲዎች በአስቸኳይ እንዲዋሀዱ መመሪያ ያስተላለፉት ሁለቱን ፓርቲዎች ፓርቲዎች ለማዋሀድ እያሸማገሉ የሚገኙ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦች የተካተቱበት ኮሚቴ ያቀረባቸው የማስማሚያ ነጥቦች ከቀረቡ በኋላ እና የሁለቱም ፓርቲዎች ፕሬዘዳንቶችና የውህደት ኮሚቴ አባላት ውህደቱ የዘገየበትን ምክንያት ከዘረዘሩ እንዲሁም የሁለቱ ፓርቲዎች ምክር ቤት አባላት ሰፊ ውይይትና የመፍትሔ ሀሳብ ካቀረቡ በኋላ ነው፡፡ የቅድመ ውህደት ፊርማው በሚፈረምበት ዕለት ሁለቱም ፓርቲዎች የውህደቱን ሂደት የሚያመቻቹ ወኪሎቻቸውን እንደሚያሳውቁም የፍኖተ ነፃነት ባልደረባ ዘግቧል፡፡
ምንጭ፣  http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13623

No comments:

Post a Comment