Wednesday, June 25, 2014

በሀዋሳ በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አባላት ዛሬም የረሀብ አድማ ላይ ናቸው!! በሀዋሳ ሰ.መ.ጉ እስረኞችን እንዳይጎበኝ ተከለከለ – የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)ባሳለፍነው ሳምንት ሰኔ 15 ቀን 2006ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አባላት ‹‹ፍትህን ተነፍገን ትግላችን አይቆምም ››በማለት ዛሬም ለ4ኛ ቀን በርሀብ አድማ ላይ ናቸው፡፡አባላቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ቅዳሜ እለት ጀምሮ በረሀብ አድማ ላይ ሲሆኑ በትላንትናው እለት ሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው በኢ/ፌ/ዲ/ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 27(1-ሀ)32/1-ሀ/እና 257 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በሚል የአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ዐ/ሕግ ክስ ተመስርቶባቸው የዋስትና መብታቸው ተነፍጎ በእስር እንዲቆዩና ዓቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለሰኔ 20 ቀን 2006 እንዲያሰማ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በማስተላለፉ ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
በተያያዘም ዜና ሰ.መ.ጉ በሃዋሳ ከተማ በእስር ላይ የሚገኙትን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላትን ሁኔታ ለመመልከት ወደ ወደ ሃዋሳ እስር ቤቶች ያመሩት የሰብዓዊ መብት ጉባዔ ሀላፊዎች እስረኞቹን ለማግኘት እንደማይችሉና ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ትዕዛዝ በመተላለፉ ምክንያት ታሳሪዎቹን ማግኘት እንዳልተቻለና የጣቢያ ሀላፊዎቹን ለማናገር የተደረገውም ጥረት እንዳልተሳካ አስረድተዋል፡፡

10450753_657204294364508_6267425299544943631_n
10448208_657204214364516_9050720156707149922_n

ምንጭ፣ http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/15021
 

Sunday, June 8, 2014

እየራበንም ቢሆን በምግብ እራሳችንን ችለናል – ኃ/ማሪያም ደሳለኝ

June 8, 2014
Ethiopian PM Hailemariam Desalegn on Al Jazeera(ግንቦት7 ዜና) – ወያኔ ስልጣን በያዘባቸዉ አመታት በተለይም ባለፉት አስር አመታት የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በድርብ አኃዝ አደገ፤ ኢትዮጵያ በ2015 ዓም መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ አገሮች ተርታ ትሰለፋለች፤ በኤሌክትሪክ ኃይል እራሳችንን ችለን ለጎረቤት አገሮች እንተርፋለን፤ በቅርቡ ደግሞ በምግብ ምርት እራሳችንን ቻልን የሚሉ በአይን የማይታዩና በእጅ የማይዳሰሱ የ”ላም አለኝ በሰማይ” ክምሮች እየከመረ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመደለል ሞክሯል። የአገሩ ኤኮኖሚ በእጥፍ አደግ ሲባል ችግርና መከራዉ በሦስት እጥፍ የጨመረበት የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እንኳን መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ አገሮች ተርታ ሊሰለፍ ከሦስቱ ዕለታዊ ምግቦች አንዱን በቅጡ መብላት ተስኖት መብራት በሳምንት አንድ ቀን ብቻ እያገኘ “ጽድቁ ቀርቶብኝ በወጉ በኮነንከኝ” እያለ ጨለማ ቤት ዉስጥ ቁጭ ብሎ የመከራ ዘመን መቁጠር ጀምሯል።
የኢትዮጵያ ህዝብ እንመራሀለን ከሚሉት የወያኔ መሪዎች እጅ እጅ ብሎ የሰለቸዉ ነገር ቢኖር እንደሰዉ በእግሩ ቆሞ የሚሄደዉ ዉሸታቸዉና ቅጥፈታቸዉ ነዉ። የወያኔ መሪዎችና እዉነት አንድ ላይ ታይተዉ ስለማያዉቁ ህዝብ አይኑ እያየ የሆነዉን ነገር አልሆነም ወይም ጭራሽ ያልተሞከረዉን ነገር ሆነ ብለዉ ሲዋሹ ለአፋቸዉም ለሰብዕናቸዉም አይሳሱም። ለምሳሌ ሠላማዉ ዜጎችን በጅምላ ገድለዉ ብርድልብስ ጠቅልለዉ እየቀበሩ ማንንም አልገደልንም፤ መብቱን የጠየቀ ሰላማዊ ሰልፈኛ በጥይት እየጨፈጨፉ – ባንክ ተዘረፈ፤ መሬታችንን ለምነዉ ለሱዳን እየሰጡ – የተሰጠ መሬት የለም፤ አኝዋክን ከመሬቱ አፈናቅለዉ መሬቱን ለባዕዳንና