Monday, March 31, 2014

ፖሊሱ ሚኒባሷን በጥይት መታት፤ አንዲት እህት ወዲያው ሞተች ሁለቱ ቆሰሉ


የህዝብን ደህንነት እንዲጠብቁ የሰለጠኑ ፖሊሶች የንፁሀንን ህይወት በማጥፋት ስራ ላይ ተጠምደዋል
news
ትላንትና ማታ ከእምድብር ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ በአካባቢው የጥበቃ ተረኛ በነበረ ፖሊስ በጥይት ከተመታ በኋላ በውስጡ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መሀከል የአንድ ከአረብ ሀገር ተመላሽ እህታችን ህይወት ወዲያው ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ተከስቷል ይላል ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ።
እንደደረሰው መረጃ ከሆነ ፖሊሱ ይህን እርምጃ የወሰደው ሚኒባሱ ኮንትሮባንድ የጫነ መኪና መስሎት እንደሆነ በአካባቢ የነበሩ የአይን እማዬች ቢገልጹም የጥበቃ ፖሊሱ ይህን እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ወደ ላይ ተኩሶ መኪናውን ለማስቆም ወይም ለማስጠንቀቅ ያደረገው ጥረት አለመኖሩን አክለው ይገልፃሉ።
አደጋው የደረሰው በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ ልዩ ስሙ ጋሶሬ እየተባለ በሚጠራው መንደር ሲሆን በቅርብ ጊዜ ይህ አካባቢ ከወልቂጤ ከተማ ተካሏል) የእምድብር ከተማ ነዋሪ የሆነችው ሟች ኮከቤ አለማየሁ ባለ ትዳር እና የሁለት ልጆች እናት ስትሆን በቅርብ ጊዜ ከአረብ ሀገር ተመልሳ ኑሮዋን ለማቸነፍ አነስተኛ ሱቅ ለመክፈት ለሱቅ እሚሆን እቃ ለማምጣት ወደ አዲስ አበባ

የማሕበረ ቅዱሳን የመጨረሻዎቹ ቀናት – ከተመስገን ደሳለኝ


 
“ማሕበረ-ወያኔ” 
mahbere-kidusan-300x168በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የሚመራው መንግስት ከናቅፋ እስከ ጉና ተራራ ያሉ ምሽጎቻቸውን ከሰማይ በጦር አይሮፕላን፣ ከምድር እሳት በሚያዘንቡ ቢ.ኤሞችና መድፎች ሳያቋርጥ ደበድብም፤ በሀገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢ ከቀን ወደ ቀን ግዛታቸውን እያሰፉ የተጠናከሩት ‹‹ወንበዴዎች›› ራስ ምታት ሆነውበታል፡፡ የኤርትራ ‹‹ነጻ አውጪ›› ቤዝ-አምባው በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለጥቃት የመጋለጥ እድሉ አናሳ በሆነው የሳህል በረሃ በመሆኑ አብዛኛው የአመራር አባል መሸሸጊያው አድርጎታል፡፡
 
በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ አካባቢ የሚንቀሳቀሱት የወያኔ መሪዎች ምሽጋቸው እንደ ሳህል ምቹ ባለመሆኑ፤ በርካታ ክፉ ቀናትን ያሳለፉት በተራራማ አካባቢዎች በሚገኙ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ገዳማት ውስጥ ተደብቀው እንደሆነና ከቦታ ቦታ መዘዋወር ሲፈልጉም የመነኮሳቱን አልባሳት ይጠቀሙ እንደነበረ በትግሉ ዙሪያ የተዘጋጁ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ በተለይም ታጋይ መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሀዬ፣ ግደይ ዘርአፅዮን፣ ስዩም መስፍን፣ ስብሐት ነጋን…. የመሳሰሉ የአመራር አባላት የገዳማቱ ቤተኛ ነበሩ፡፡ ከዚሁ ጋ ተያይዞ የሚነገርም አንድ ታሪክ አለ፤ የመንግስት ፀጥታ ሰራተኞች ሁለት የ‹‹ወንበዴ›› መሪዎች በትግራይ በሚገኝ አንድ ገዳም ውስጥ ከመነኮሳቱ ጋር ተመሳስለው መሸሸጋቸው መረጃ ይደርሳቸውና በጥቂት ሰዓታት ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ወታደሮችን በመላክ ዙሪያ ከበባ ያደርጋሉ፡፡ ይሁንና መደበቂያ በመስጠት የረዷቸው መነኮሳት ሁለቱን ታጋዮች ‹‹ወይባ›› በመባል የሚታወቀውን ረጅሙን ቀሚሳቸውን አልብሰው እና ቆብ

Sunday, March 30, 2014

መጋቢት 28 2006 ደረሰ !!! አዲስ አበባ‹‹ለእሪታ ቀን!››ትዘጋጅ ዘንድ ጥሪ ተደርጓል። የሰማህ ላልሰሙት ንገራቸው !!! – ምንሊክ ሳልሳዊ

መብራት ውሃ የስልክና የኢንተርኔት ኔትወርክ አገልግሎቶች መብቶች የህዝብ ናቸው!!!!!
አቤቱታችን ከፖለቲካ ነጻነት እና ዲሞክራሲያዊነት ጎን ለጎን የመሰረታዊ አገልግሎቶች ጥያቄ ነው …ይህ ደሞ ለየት ባለ መልኩ አብዮታዊ ነው::እኛ በሰው አገር የምንኖር ዲያስፖራዎች በወገናችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ከማውራት እና መኖሪያ ፍቃዳችን ሲታደስ ከመቀዝቀዝ ዉጪ በወያኔ ላይ የምናሳድረው ጫና እምብዛም ጉልፍ ስፍራ የለውም:: እርስ በርሳቸው የሚላተሙ የጆተኒ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በላም አለኝ ተስፋ ህዝባችንን አረንቋ ውስጥ እየጨመሩት ነው::
ለጋች አገራት የሚያወጧቸው ሃሰተኛ ጸረ አፍሪካ ሪፖርቶች በተለይ የምስራቅ አፍሪካን ተገን አድርጎ የተመቻቸው የብሄራዊ ጥቅማቸው ፎርሙላ ስኬት የአምባገነኖችን እድሜ በማስረዘም ህዝብ እንዲጭበረበር የህዝብ ጥያቄዎች እንዲደናቀፉ ለገዢዎቻችን የልብ ልብ ሰቷቸዋል:: ለብሄራዊ ጥቅም አስጊ ይሆናሉ የተባሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን እስከማጨማደድ እየዘለቀ በኢጅ አዙህ ህዝባዊ ጥያቄዎች እንዲታፈኑ እየተደረገ አምባገነናዊ አገዛዝን አፍልተውብናል እንሱ ለጋሽ አገራት::
መሰረታዊ ፍላጎቶች እና የአገልግሎት ፍጆታችን በበቂ ሁኔታ ባልተሟላበት አገር መንግስት ፕሮጀክት ለመጨረስ የገንዘብ እጥረት ገጠመኝ በሚልበት አገር ብሄራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሬ የለኝም በሚልበት እና የመንግስት ካዝና ባዶ ሆኖ በዕቃ ግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታ ከቱጃሮች መንግስት በሚበደርባት አገር ጥቂት ፖለቲካው የወለዳቸው ሃብታሞች እጅግ ብዙ የኢኮኖሚ ድቀት ያፈራቸው ደሃዎች በፈሉበት አገር ምን አይነት የኢኮኖሚ እድገት እንደተመዘገበ አነጋጋሪ ነው:; እስከመቼ የአምባገነኖችን ደጋፊዎች ዉሸት ተሸክመን እንዘልቃለን::
መብራት ውሃ ስልክ ሀገሪቷ ተሰርቶ እና ተበድራ ሳይሆን በተፈጥሮ የታደለችው ጸጋዋ እንደሆነም ያለን ሃብት ይመሰክራል ህዝቡ ያለውን ቴክኖሎጂ ከተፈጥሮ ሃብቱ ጋር አደባልቆ እንዳይጠቀም እኛ እናውቅላቹዋለን የሚሉ የወያኔ አውሬዎች ቀፍድደው ይዘውታል::
በቀላል ሊፈታ የሚችል ችግርን በፖለቲካዋ ሳንካ መተብተብ ምንም የሚጠቅም ስላልሆነ ህዝቡ አስፈላጊውን የአገልግሎቶች አቅርቦት እንዲያገኝ መደረግ አለበት ብለን ካሁን በፊት ብንጮህም ከቀድሞ በባሰ መልኩ ብሶበት ይገኛል::
በአለማችን በረሃ በተባሉት አገሮች የውሃ አቅርቦት በሰፊው ለህዝባቸው እየሰጡ ሲሆን የተጣሩ ውሃዎች ሳይቀር በርካሽ ዋጋ

ይድረስ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳ

 
 
 
ኤሎሄ! ቅዱስ! ኤልሻዳይ! አዶናይ! ያህዌ! ጸባዖት! ኢየሱስ! ክርስቶስ! አማኑኤል! በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ሥም! አሜን!
አቤቱ አባት ሆይ ከእኛ ወገን ለአንተ እናት ሆናህ በእሷ በኩል በሥጋ ትዛመደን ዘንድ በመረጥካትና ስለብዙዎች ልቧ (አእምሮዋ) ሐዘንን (ነብዩ እንደተናገራት ፍላጻዎችን) ሁሉ ያስተናግድ ዘንድ ባጸናሀት፣ ቅድስት፣ ንፅህትና ዘላለማዊት ድንግል በሆነች እናትህ ማሪያም ሥም ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እለምንሀለሁ! አሜን!
ብፁዕ አባታችን፡ ከዚህ በፊት የጻፍኩልዎት ደብዳቤ ይደረስዎት አይድረስዎት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ግን እንደደረሰዎት እገምታለሁ እኔ ለአንባብያን በማህበራዊ ድህረገፆች እንዲነበብ ባደርገውም በደብዳቤው መልዕክት የተሳቡ አንዳንድ ሰዎች የእኔን ፍቃድ ጠይቀው በቀጥታ በፋክስ እንላኩልዎት ነግረውኛል፡፡ ጉዳዩ ዛሬ ደግሜ ከማነሳው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ የበፊቱንም ደብዳቤ በድጋሜ አንባብያንም ይሁኑ እርሶም ማመሳከር ትችሉ ዘንድ ከዚሁ መልዕክት ጋር አያየዛለሁ፡፡ ከጉዳዩ መመሳሰል ባሻገር የወራቶቹም መመሳሰል ነገሩን በውል ላስተዋለው አስገራሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ወራት በመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የጾምና ጸሎት እንዲሁም የንስሃ መቀበያ ወቅት እንደሆነ ልብ እንበል፡፡ ልክ የዛሬ ዓመት በዚሁ የጾም ወቅት ተከስቶ የነበረ (እንደውም የዛሬ ዓመት በጌታ ሕማም መታሰቢያ ሳምንት በነበረው የጾሙ ጊዜ ነበር) ጉዳይ ዛሬም ተከስቶ ሳየው ተገረምኩ እናም ተመሳሳይነት ያለው መልዕክት በድጋሜ ለእርሶና ለቤተክርስቲያኒቱ የውጭ ግንኙነጽ ኃላፊ እንዲሁም ለትዝብት ለሕዝብ ማስተላለፍ ፈለግሁ፡፡ ይህ ጉዳይ የመልአከ መንክራት (መምህር)ግርማ ወንድሙን አገልግሎት ይመለከታል፡፡
ሰሞኑን በአቡነ ገሪማ መምህሩን አስመልክቶ እንደተጻፉ የሚያሳዩ ሁለት ተቃራኒ መልዕክት ያለቸው ደብዳቤዎች ለሕዝብ በማሕበራዊ ገጾች በመድረሳቸው የዛሬ ዓመት ተከስቶ የነበረው አይነት ወዥምበር በሕዝብ ዘንድ ፈጥረው ታላቅ መነጋገሪያ ጉዳይ

Saturday, March 29, 2014

ኢህአዴግ የእምነት ተቋማትን በጥብቅ የሚቆጣጠርበት ህግ ሊያጸድቅ ነው

ህጉ ጣጣ እንዳያመጣ የሰጉ ኢህአዴግን እየመከሩ ነው

ኢትዮጵያን ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ እየገዛ ያለው ኢህአዴግ የሃይማኖት ተቋማትንና ምዕመናኑን በጥብቅ የሚቆጣጠርበትን ህግ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። የህጉ ረቂቅ የደረሳቸው ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ኢህአዴግን አበክረው እየመከሩና በሚያመጣው አጠቃላይ መዘዝ ዙሪያ እያስጠነቀቁ ነው።
ጎልጉል የተባለው ድረገጽ ከዲፕሎማት ምንጮች አገኘሁት ባለው መሰረት ኢህአዴግ በእምነት ተቋማት ላይ ቁጥጥሩን የሚያጠብቅበትንና ከሃይማኖት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውጭ መሰብሰብን፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግንና የተቃውሞ ድምጽ ማሰማትን የሚከለክል ህግ አዘጋጅቷል።
church_and_mosque
የዜናው ምንጮች ዝርዝር ህጉን ለጊዜው ይፋ ከማድረግ እንደሚቆጠቡ አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ የሚደነገገውን አዲስ ህግ ጥሰዋል በሚል የሚከሰሱ ምዕመኖች እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የሚያዝ አንቀጽ አለበት። አዲሱ ህግ ከሽብርተኞች ህግ ጋር የሚጣቀስ እንደሆነም የጠቆሙት ክፍሎች ኢህአዴግ “ከእምነት ነጻነት” ጥያቄ ጋር በተያያዘና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ውስጥ ውስጡን እየነደደ ያለው ችግር ስላስጨነቀው ይህንን ህግ ለማውጣት መገደዱን አስረድተዋል። በሌላ በኩልም እስካሁን መፍትሔ ያላገኘው የሙስሊሞች ጥያቄ ከዚያም ጋር ተከትሎ የተከሰተው ደም መፋሰስ ወደፊት ሊያመጣ በሚችለው ጉዳይ ላይ ኢህአዴግን በብርቱ አሳስቦታል፡፡
ኢህአዴግ ከቀን ወደ ቀን ቀውስ እየተደራረበት እንደሆነ የተረዳችው አሜሪካ በከፍተኛ ባለስልጣኖቿ አማካይነት ኢህአዴግን እየመከረች እንደሆነ ከዲፕሎማቶች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ከፖለቲካው ቀውስና በቀጠናው ካለው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አሜሪካ በተደጋጋሚ የህወሃትን ሰዎች በተናጠል እያነጋገረች እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። ዲፕሎማቶቹ እንደሚሉት አሜሪካ መለስ “ከተሰዉ” በኋላ አገሪቱን ማን እየመራት እንደሆነ በቅጡ ለመረዳት በሚያስቸግር ሁኔታ የስልጣን መዛነፍና ደረጃን የጠበቀ የስልጣን ተዋረድ አለመኖሩም አሳስቧታል። ኢህአዴግ ለህልውናዬ ያሰጋኛል በሚል መንግሥታዊ ባልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች /መያዶች/ ላይ ያወጣውን አፋኝ ህግም ጠቅሰዋል። ዲፕሎማቶቹ በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ወቅቱ አሁን እንዳልሆነ አመልክተዋል።
ምንጭ፣  http://www.ethioforum.org/

የወያኔን ከፋፋይ አገዛዝ እናምክን

         
የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ ሊከበርላቸውና ሊያሳድጋቸው የሚገቡ የተለያዩ የባህልና የታሪክ ቅርሶች ያሏቸውን ያህል በብዙ መንገድ የሚያይዝ የጋራ ታሪክ ቅርስና ዝምድና አላቸው። ልዩነቶቹ ራሳቸው ተጠቃቃሚ ለሆነ የእርስበርስ ግንኙነታቸው ጠቃሚ እንጂ ከአንድ ሀገር ማህበረሰብነታቸውና ከጋራ ህልማቸው ጋር የሚጋጩ የጠብና የግጭት መንስኤዎች አይደሉም። ከጠብና ግጭት ማንኛውም ብሄር ብሄረሰብ ተጠቃሚ አይደለም። ከጠብና ግጭት ጥቅም ይገኛል ብለው የሚያስቡ “ግርግር ለሌባ ይመቻል” የሚለውን የወሮ በላ ፍልስፍና የሚከተሉ የቀን ጅቦች እንጂ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች አይደሉም። በወያኔ የግዛት ዘመን የደረሱትን ግጭቶች መፈናቅሎችና የተፈጠሩትን የእርስበርስ ጥርጣሬዎችን ልብ ብሎ ለተመለከተ ሁሉም በአገዛዙ እና በሎሌ የበታች ሹማምንቱ የተፈጠሩ እንጂ አንድም ጊዜ እንኳን ከህዝብ የመነጩ አይደሉም።
የወያኔ ጉጅሌ በአገዛዝ ዘመኑ ሁሉ ብሄር ብሄረሰቦችን ከሚያይዟቸው የጋራ ማህበራዊ ቅርሶችና ህልሞች ይልቅ ካለመታከት ልዩነቶቻችን ላይ ያተኮረ ፖለቲካ እያካሄደ እንዳለ ግልጽ ነው። ከዚህ አልፎም አዳዲስ የእርስበርስ ግጭቶችን እና ጠቦች እንዲፈጠሩ ተግቶ የሚሰራ ከፋፋይ ቡድን ነው። እርስበርሱ መጠራጠርና መፈራራት እንዲሰፍን ልዩ ልዩ ስልቶችን ይቀይሳል። ከአንዱ ብሄረሰብ ተንኳሽ አዘጋጅቶ ሌላው ብሄረሰብ ላይ አደጋ እንዲደርስ ከዚያም ተጠቃሁ የሚለው አጸፋ እንዲመልስ ያደርጋል። የአንዱን ብሄረሰብ መንደርና ንeበረት በእሳት ለኩሶ በሌላው ብሄረሰብ እንዲመካኝ ያድርጋል። አንዱ በአንዱ ላይ እንዲያማርር ከንፈሩን እንዲነክስ ማድረግ ለወያኔ ጉጅሌዎችና ለሎሌዎቻቸው እንደፖለቲካ ጥበብ ከታየ ሁለት አስርት አመታት አልፈዋል። በየትኛውም የሀገራችን አካባቢዎች የተቀሰቀሱ የርስበርስ ጥርጣሬዎችና ግጭቶችን ያሸተተ ሁሉ ወያኔ፣ ወያኔ

Friday, March 28, 2014

አስማተኛው የኢኮኖሚ እድገት!


በ ገብርኤሉ ተስፋዬ
ከየት ጀምሬ ወደየት እንደምሄድ አላውቀውም፣ አሁን አሁን የእድገት መለኪያው ምን እንደሆነ እንኩዋን ግራ ገብቷችዋል:: ወይስ የኢኮኖሚ እድገቱ ለኢትዮጲያውያን ሳይሆን ኢትዮጲያን ለሚያስተዳድሯት ብቻ ነው ወይ? እውነቱ በገሀድ ግልፅ ብሎ እያለ ካለፉት አስር አመታት ጀምሮ ጆሮዋችንን በሁለት ዲጅት ሀገሪቱ አድጋለች እያሉ ሲያደነቁሩን ከረሙ:: ለኔ እድገት የሚለው ቃል በአሁን ሰሀት ስድብ መስሎ እየታየኝ ነው:: የተወሰኑ ሰዎች ብር በብር ላይ አካበቱ፣ሀፍታም ሆኑ፣ ህንፃ ገነቡ፣ከመኪና መኪና ቀያየሩ ወዘተ እየተባለ  በኢትዮጲያ ስም መነገዱ አግባብ አይደለም:: ለመሆኑ የኢትዮጲያ ህዝብ ጠግቦ የሚበላው ሀሁን ነው ወይስ የዛሬ 10 እና 20 አመት በፊት ነው? መልሱን የሁላችንም ልቦና ያውቀዋል! ህዝቡ አንገቱን ደፍቶ ሁሉን ነገር ሰምቶ እንዳልሰማ  አይቶ እንዳላየ ዝም ሲል ጅል የሆነ መሰላችው:: እስቲ የኢትዮጲያ እድገት ተብየው ያመጣውን ለውጥ ለመመልከት ልሞክር::
በመጀመሪያ መመለከት የምፈልገው የምግብ ዋስትናን ነው::የምግብ ዋስትና ማሽቆልቆሉን የማያምኑ ለሆዳችው የሞቱ እነሱ ብቻ ሲበሉ ሌላውም የበላ የሚመስላችው ብዙ አሉ:: ሆኖም ግን እውነት እውነት ነች እና ምንም ምንም ቢሉ እውነትነቷን  አትቀይርም:: ስለምግብ ዋስትና ለመናገር በአዲስ አበባ ስለሚኖረው ህዝብ መናገርን መረጥኩ ምክንያቴም አዲይስ አበባ የኢትዮጲያ ዋና ከተማ እንደ መሆኑዋ መጠን፣የኢህአዴግ አመራሮች ስለእድገት ሲያወሩ የሚጠቅሱዋት ከተማ ስለሆነች እና በጣም ብዙ ህዝብ(ከ 5 እስከ 6 ሚልየን) ስለሚኖርባት ነው:: እዝይጋ ሥራ አልባ የሆኑትን፣ሚበላ የሌላችውን ብዙዎቹን የማሀበረሰባች አካላትን ሳይሆን ማየት የምፈልገው ስራ አገኘው ብሎ በመንግስት መስሪያቤት ተቀጥሮ የሚሰራውን ነው:: አንድ የመንግስት ሰራተኛ የድግሪ ምሩቅ የሆነ በወር 1600 ብር የሚያገኝ ሲሆን ከዚያ ላይ 250 እስከ 300  ግብር ይከፍላል በእጁ ላይ 1300 ይቀረዋል እንበል ፣ የቤት ኪራይን በተመለከት በአሁን ሰሀት በአዲስ አበባ አንድ ክፍል ቤት በትንሹ ከ 700 እስከ 800 ብር የሚያወጣ ሲሆን ከ 1300 ላይ ይሄን ብር ስናነሳ  500 ብር አካባቢ ይቀረዋል፣ በየቀኑ ለትራንስፖርት በትንሹ 3 ብር አወጣ ቢባለ 400 ብር እጁ ላይ ቀረው

በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ደማቅ የተቃውሞ ትእይንት ተደረገ::

March 28, 2014
ሳዲቅ አህመድ
Ethiopian Muslims protest, Addis Ababa (March 28, 2014)በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስኪድን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ዋናዋና ከተሞች ‹‹ሰላታችንን በመስጂዳችን!›› በሚል መሪ ቃል ህዝበ ሙስሊሙ እያካሄደው ያለው መስጂድ ተኮር የዘመቻ እንቅስቃሴ አካል የሆነው እና የዘመቻው ማጠናቀቂያ የጁምኣ የተቃውሞ ትእይንት በደመቀ መልኩ ተካሂዷል::
ህዝቡን ከመስጂዱ ለመነጠል በመንግስት በኩል እየተሰራ ያለውን ህገ ወጥና ኢ-ህገ መንግስታዊ ስራም ለራሱ ተረድቶ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማትና መስጂዶቹን በዒባዳ በማድመቅ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ይህ ወቅታዊና አንገብጋቢ የመስጂድ ባለቤትነትን የማረጋገጥ እንቅስቃሴ የመንግስትን እና የመጅሊስን ሴረኞች እንቅልፍ ማሳጣቱንም ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ የውስጥ መረጃዎች እያጋለጡ ነው፡፡ ‹‹ሰላታችንን በመስጂዳችን!››ዘመቻ የዛሬው ጁሙአ ድረስ ቀጥሎ የቆየ ሲሆን በአዲስ አበባና በተመረጡ የክልል መስጂዶች ላይም አስቀድሞ የነበሩንን ቋሚ ትዝታ ጥለው ያለፉ ግዙፍ ተቃውሞዎችን በሚያስታውስ መልኩ የደመቀ የተቃውሞ ስነስርአት በማድረግ በሰላማዊ ሁኔታ ዘመቻው መጠናቀቁ ታውቋል::
በዚህም መሰረት ከቀኑ ስድሰት ጀምሮ በአዲስ ወደ አዲስ አበባ አንዋር መስኪድ እና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ የተቃውሞ ወደተመረጡ መስኪዶች የተመመው ህዝበ ሙስሊሙ የመስኪዶችን ውስጥ እና ደጅ በመሙላት መስኪዶቹ የራሱ ሃብት መሆናቸውን እና ሙስሊሙ ህዝብ ሰላም ፈላጊ መሆኑን በደመቀ ተቃውሞ ነጭ ምልክቶችን በማውለብለብ ገልጿል::
ህዝበ ሙስሊሙ ዘመቻውን በተሳካ መልኩ በማድረግ ሰላማዊ ተቃውሞውን አሰምቶ ከኮሚቴው ጎን ዛሬም ቃሉን አክብሮ እንደቆመ በማሳየት በሰላም መመለሱን ለማረጋገጥ ተችሏል:: [ተጨማሪ ፎቶዎችን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ] [ቪዲዮዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ]
ምንጭ ፣ http://ecadforum.com/Amharic/archives/11586/

Sunday, March 23, 2014

የኢሕአዴግ መንግስት የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ዶክመንተሪ ሊያዘጋጅ ነው ተባለ


ዶክመንተሪው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት አካል እንደኾነ ተጠቁሟል
‹‹ማስረጃ አቅርቡና እንነጋገርበት›› ለሚለው የማኅበሩ ጥያቄ ምላሽ አልተሰጠም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሲኖዶሱን ይኹንታ አግኝቶ በመላው አገሪቱ የሚንቀሳቀሰውን የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ነው የተባለ ዶክመንተሪ ፊልም ለማዘጋጀት መታቀዱ ተጠቆመ፡፡
mahbere-kidusan-300x168
የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አንዳንድ ሓላፊዎች አቀብለውታል በተባለ መረጃ እንደሚታገዝና በመንግሥት አካል እንደሚሰናዳ የተገለጸው የዶክመንተሪ ዝግጅቱ በማኅበሩ ኻያ አመራሮች እና አባላት ላይ እንዳነጣጠረ ተገልጧል፡፡ መንግሥት በምርጫ – 97 ውጤትና በተከታይ ኹኔታዎቹ ላይ ባካሔደው ግምገማ፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው የሚባሉ ግለሰቦች በተለይ በገጠር ቀበሌዎች ለተቃዋሚዎች ተሰሚነት ማግኘት በምክንያትነት መጥቀሱ በዜና ጥቆማው የተመለከተ ሲኾን ‹‹የአክራሪነትና የጽንፈኛ ፖሊቲከኞች ምሽግ ነው›› በሚል የሚያቀርበው ክሥም ከዚኹ የሚነሣና ለመጪው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅትም አካል እንደኾነ ተነግሯል፡፡
በቅድመ ዝግጅቱ የሚወሰዱ ርምጃዎች የማኅበሩን አቅሞችና እንቅስቃሴዎች በመቆጣጠር በተለይም የማኅበሩ መሠረቶች ናቸው የሚባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያትን ‹‹በሴኩላሪዝም መርሖዎች የመግባቢያ ሰነድ›› ጠርንፎ ‹የአገልግሎት ቅኝቱን

Saturday, March 22, 2014

Group: Ethiopia regularly records phone calls

Associated press
March 21,2014
NAIROBI, Kenya (AP) — A rights group says that Ethiopia's government regularly listens to and records the phone calls of opposition activists and journalists using equipment provided by foreign technology companies.
Human Rights Watch said in a report Friday that the foreign equipment aids the Ethiopian government's surveillance of perceived political opponents inside and outside the country. The group's Arvind Ganesan said Ethiopia is using its government-controlled telecom system to silence dissenters. The group says that recorded phone calls with family and friends are often played during abusive interrogations. Human Rights Watch said most of the monitoring technology is provided by the Chinese firm ZTE. Several European companies have also provided equipment, the group said, including from the U.K., Germany and Italy.

Source: http://www.ethiomedia.com/broadway/4336.html

የዋሸው ማን ነው? – ለመምህር ግርማ ከቤተክርስቲያን የተጻፉላቸው 14 ደብዳቤዎችና ምስክር ወረቀቶች እጃችን ገቡ


 
girma wendimu
“ለምንድ ነው የምትገፉኝ?” – መምህር ግርማ
(ዘ-ሐበሻ) ዘ-ሐበሻ የመምህር ግርማ ወንድሙን ጉዳይ ተከታትላ በመዘግብ ላይ ትገኛለች። አንባቢዎቻችን እውነታውን እስኪጨብጡ ድረስ ዘገባዎችን ማቅረቧ የሚቀጥል ይሆናል። በትናንትናው የዜና እወጃችን ቤተክርቲያን በአቡነ ገሪማ አማካኝነት የተጻፈን ደብዳቤ በመጥቀስ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን “መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ” በሚል ስያሜ የተበተነው ደብዳቤ ሕገ ወጥ በመሆኑ የሚመለከተው ሁሉ ይህን ግንዛቤ እንዲወስድ አሳሰበች፡፡” በሚል የተጻፈውን ደብዳቤዎች አቅርበን ነበር።
ቤተክርስቲያን መምህር ግርማን በፎርጂድ ደብዳቤ ማሰራጨት የሚወነጅል ደብዳቤ ቢወጣም ዘ-ሐበሻ ለመምህር ግርማ ከቤተክርስቲያን የተጻፉ 14 ደብዳቤዎችና የምስክር ወረቀቶች ደርሰዋታል። ይህም ፎርጂድ ደብዳቤ ጽፈዋል በሚል የወነጀላቸውን አካል ወይም መምህር ግርማ ህጋዊ ደብዳቤ ተሰጥቶኛል ብለው ያሰራጩትን ደብዳቤ ለተመለከተ ማን ነው የዋሸው ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ። ያንብቡ ና የዋሸው ማን ነው ለሚለው ምላሽ ይስጡ።
“አንድ ሙዚቀኛ የሙዚቃ ትምህርት ቤት አንድ ሰርተፊኬት ብቻ ካለው ተቀባይነትና የታዋቂነት ክብር ይሰጠዋል፤ የሥራ መስኩም ይወደዳል፣ ይፈቀራል። ማንም የሚቃወመውም የለም፤ በሁሉም ዘርፍ ተፈላጊ ተወዳጅ ተሸላሚ ነው። በክፉ መንፈስ ከተጠቁት ጋር ለምውለው ለእኔ ግን የተገላቢጦሽ ነው። በሺህ የሚቆጠሩ የጥሪ አገልግሎትና የምስጋና ሰርተፊኬት አለኝ። ዛሬ ይህ ሁሉ ውሸት ሆኖ የመንደር አስማተኛ፤ የሱዳን ጠንቋይና የማይታወቅ አጭበራባሪ መለያ ስሜ ሆነ፤ ግን ለምን? ከጥቁር ፀጉር እስከ ነጭ ሽበት ያገለገልኩባት ቤተክርስቲያን ትምህርትና ፈውስ የሚፈልገው ሕዝብ ሲበዛ የፈውሱ ሂደት ከሃገር ውስጥና ከውጭ ዓለም ነጮችን ጨምሮ ሲከናወን የቤተክርስቲያን የወር ባጀት እና የዓመት ገቢ በእጥፍ ሲያድግ ለአባቶች እና በየአገረ ስበከቱ ላሉ አባቶች ሕዝቡ የፈውስና የትምህርት ፍላጎት ጥያቄ ሲበዛ ለምንድ ነው አስማተኛና ጠንቋይ የተባልኩት? ከነ ሙሉ መረጃው በሚቀጥለው… “አጥርቶም አየ… ከሩቅም ሳይቀር ሁሉን ተመለከተ” (ማር.23) መቆሚያና ማብቂያ የለውም ፈተና… ግን ለምን? ለምንድን ነው የምትገፉኝ?”
- መልአከ መንከራት ግርማ ወንድሙ
ደብዳቤዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
ምንጭ፣ zehabesha.comhttp://www.zehabesha.com/amharic/archives/13731

Thursday, March 20, 2014

አዲስ አበባ “ለእሪታ ቀን” እንድትዘጋጅ ተጠየቀ! “ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!!”


(ዘ-ሐበሻ 1)በውሃ እጦት፣ 2)በኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ፣ 3)በትራንስፖርት ችግር፣ 4)በልማት ሰበብ በሚፈርሱ መኖሪያዎችና የንግድ ሱቆች የተነሳ ዜጎች እየተበደሉ በመሆናቸው፣ 5)በስልክ መስመር ችግር ና በሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ ዛሬ የአንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲ የአዲስ አበባ ጽ/ቤት ስራ አስፈጻሚ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በከተማይቱ ደማቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ ይፋ አደረገ። “ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት” የሚል ርእስ የተሰጠው መግለጫ ከተማይቱ ከላይ በተጠቀሱት ችግሮች በመዘፈቋ ነዋሪው ከፍተኛ ችግር ውስጥ መውደቁን በመገንዘብ ገዢው ፓርቲ ከተማይቱን ብሎም አገሪቱን የመምራት ብቃት እንደሌለው የችግሮቹ ግዝፈት ዓይነተኛ ማሳያ ነው ብሏል፡፡
UDJ
ሙሉ መግለጫውን ዘሐበሻ እንደሚከተለው እንደወረደ አስተናግዳዋለች።
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!!
መግለጫ
ሌሎች አገሮች ለዋና ከተሞቻቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የየአገሮቻቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማሳያ በማድረግ አለም አቀፍ ተቋማትንና ጎብኝዎችን በመጋበዝ የከተሞቻቸውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ግን በብዙዎች የአፍሪካ አገራት የአህጉሪቱ መዲና ተደርጋ የምትጠቀሰው አዲስ አበበባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ኋላ አየተጎተተች ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ምድብ መቀላቀለ ተስኗት ለነዋሪዎቿ የማትመች የፈተና ምድር ሆናለች፡፡
UDJ 2
ኢህአዴግ ራሱን ልማታዊ መንግሥት በማድረግ ከሰየመበት ቅጽበት አንስቶ በልማት ሰበብ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ቤተሰቦቻቸውን ከሚያስተዳድሩበት የንግድ ቦታ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ በከተማይቱ እንዲነሱ የተደረጉት የንግድ ሱቆች በአብዛኛው በኪራይ

ቤተክርስቲያን መምህር ግርማን ፎርጂድ ደብዳቤ በማሰራጨት ወነጀለች


 
Memeher Girma
(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን “መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ” በሚል ስያሜ የተበተነው ደብዳቤ ሕገ ወጥ በመሆኑ የሚመለከተው ሁሉ ይህን ግንዛቤ እንዲወስድ አሳሰበች፡፡ “መምህር ግርማ ወንድሙ ከፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በመላው ዓለም እየተዘዋወሩ እንዲያገለግሉ ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል” በሚል መምህር ግርማ እያሰራጩት ያለው ደብዳቤ ከቤተክርስቲያኒቱ ጽህፈት ቤት ተፈርሞ ያልወጣ የማጭበርበር ደብዳቤ ነው ሲል በአባ ገርማ (ሊቀጳጳስ/ዶ/ር) የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርል ልዩ ጽህፈት ቤት የውጭ ግኙነት ሃላፊ ስም መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ተገልጿል።
ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም መምህር ግርማ የበተኑትንና በመላው ዓለም ከፓትርያርኩ ተዘዋውሬ ሃብተ ፈውስን እንድሰጥ ተፈቅዶልኛል የሚለውን ደብዳቤ ማስተናገዷ የሚያወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የፓትሪያርኩ ልዩ ጽህፈት ቤት

Wednesday, March 19, 2014

አባ መላ ሳይበላ ተበላ! – ሆዳም! ስለሚበላው እንጂ ስለሚባለው አይጨነቅም!


 
aba-mela-esat
ከአዜብ ጌታቸው
አባ መላ ነኝ የሚለው የፓልቶኩ ብርሃኑ ዳምጤ ሰሞኑን የሰራው ስራ ከማንም በላይ የጎዳው እራሱን ነው። ከአንድ ድርጅት ውልቅ ብለው በዚያው ጀንበር ሌላው ድርጅት ጥልቅ የሚሉ፤ ያም ሳይጥማቸው ወይም ሳይመቻቸው ይቀርና ወዲያው ደሞ ወደ ሌላ 3ኛ 4ኛ….. ድርጅት ጥልቅ ውልቅ የሚሉ ጥቂት የማይባሉ ቅብዝብዞችን አውቃለሁ።እነኚህ አይነቶቹ የቻሉትን ያህል እንደ ፌንጣ ዘለው ዘለው በመጨረሻ እዩኝ እዩኝ ያለ ……እንዲሉ፦ ራስን ብቻ አባል በሚያደርገው ዲፕሬሽን ወደ ተሰኘው ድርጅት ይገቡና ፍጻሜያቸውም እዛው ይሆናል።
ሰሞኑን በአባ መላ የታየው ዝላይ ግን በፌንጣ ተምሳሌት ከተገለጹት ቅብዝብዞች የተለየ ነው፡፡ አባ መላ ውልቅ ካለበት የወያኔ ጓዳ ያሞሌ ተመኑን ቀንሶ ዳግም ጥልቅ ብሏል። ስለዚህ ለአባ መላ ተግባር በተምሳሌነት የምትጠቀሰው ፌንጣ ሳትሆን የተፋውን መልሶ የሚውጠው ጉማሬ ይመስለኛል ።
ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን ወያኔን ጉማሬ ብለው የገለጹበትም ምክንያት ይህው ነበር፡፤ በነገራችን ላይ ብርሃኑ ዳምጤ በአንድ ቃለ ምልልስ ላይ “አባ መላ” የሚለውን ቅጽል ያወጡለት ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን መሆናቸውn (he was my best friend) አይነት ድምጸት) ሲናገር ሰምቸዋለሁ፡፤ የሞተ አይጠይቅ ሆነና ዝም ብለን ሰማነው።
ይሁን እንጂ በበኩሌ እንደሚታየኝ ብርሃኑ ዳምጤ የተሰ|ኘ የተሰፋ ሙዝ የሚሸጥ የምናለሽ ተራ ቁጭ ይበሉ (ምንጭ አብሮ አደጉ)ና የብርቅየውን ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬን ጓደኝነት እንኳን በዕውን በልቦለድ ድርሰትም ቢካተት ለአንባቢ የሚጥም አይመስለኝም፡፤ ልቦለድም ቢሆን እኮ የገሃዱ ዓለም እንጂ የከሃዲው አለም ነጸብራቅ ነው አልተባለም።….
ወደ ቀምነገሩ ልመለስ፦ አዎ ብርሃኑ ዳምጤ እነ ሎሬት ጸጋዬን እየጠቃቀሰ ፕሮፊይሉን ከፍ ከፍ እያደረገ ቢቆይም ሰሞኑን በሰራው

የመብራት መቆራረጥ ያማረረው የአዲስ አበባ የሽሮሜዳ አካባቢ ነዋሪ ሰልፍ ወጣ


 
የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ (ፎቶ ከፋይል)
የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ (ፎቶ ከፋይል)

በአዲስ አበባ የሚሰራጨው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራድዮ እንደዘገበው የመብራት መቆራረጥ ያማረረው በአዲስ አበባ የሽሮሜዳ አካባቢ ነዋሪዎች ሰልፍ ወጡ።
ራድዮው እንዳነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለጻ በአካባቢው የሚኖረው ሕዝብ በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ስሞታ ቢያቀርቡም መፍትሄ ባለማግኘታቸው ስልፍ ለመውጣት ምክንያት ሆኗቸዋል። ሰልፈኞቹ በተደጋጋሚ የሚያጋጥመውን እና ብልጭ ድርግም ከማለት ጀምሮ ለቀናት ጭራሹኑ እስከመጥፋት በሚደርሰው የኤሌክትሪክ ሃይል መማረራቸውን ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት ነው በተቃውሞ ሰልፍ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል ያለው ራድዮ ጣቢያው የሚመለከታቸውን የስራ ሃላፊዎች በማግኘት ምላሻቸውን ለመስማት የተደረገው ጥረት አልተሳካልኝም ሲል ዘግቧል።
በሌላ በኩል በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥን በመማረር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ድምጻቸውን ለማሰማት የወጡ ሰልፈኞች ምላሸ ሳይሰጣቸው “ተበተኑ” በሚል ትእዛዝ እንዲበተኑ እንደሚደረግ ሸገር የዘገበ ሲሆን የሽሮሜዳ አካባቢ ነዋሪዎችም የሬድዮ ጣቢያው ጋዜጠኞች በቦታው ከመድረሳቸው በፊት እንዲበተኑ መደረጉን ነው አስታውቋል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የትራንስፖርት፣ የውሃ፣ የመብራት፣ የቴሌኮምዩኒኬሽን፣ የጋዝ እና የሌሎችም እጥረቶች ሕዝቡን እያማረሩት ከእለት ተእለት እንቅስቃሴው እየገደቡት ይገኛሉ።
የታክሲ ወረፋ በአዲስ አበባ
የታክሲ ወረፋ በአዲስ አበባ

ምንጭ፣ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13690

በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል


ምኒልክ ሳልሳዊ
በዚህ ሳምንት አትክሮት ማግኘት ከሚፈልጉ ወገኖቻችን በዋነኝነት በኩዌት የሚኖሩ እና በስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ናቸው:: ባሳለፍነው ቀናት በዋና ዜናነት በአገሪቱ የስፖርት ሚኒስትር መኖሪያ ቤት ውስጥ የምትሰራ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ የአሰሪዋን ሴት ልጅ ገላለች ተብሎ የተዘገበውን ዜና ተከትሎ ኢትዮጵያውያን በስጋት ላይ ሲሆኑ እንዲሁም ተከራካሪ የዜግነት መብታቸውን የሚያስከብር ኤምባሲ መጥፋቱ እና በኤምባሲው የሚፈጸመውን ደባ በከፊል ለማየት እንሞክራለን::
(ፎቶ ፋይል)
(ፎቶ ፋይል)
በአሁኑ ወቅት በኩዌት ለኢትዮጵያውያን ነገሮች ሁሉ አስቀያሚ እና አስቸጋሪ እየሆኑ እንደሆን ለኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ቅርብ የሆነ ኢትዮጵያዊ ገልጿል::ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደረጉ በደሎች ተከራካሪ የመንግስት አካል እና የኤምባሲ ሰው መጥፋቱ ለአሁኑ ወንጀል መፈጸም እና ስጋት መንስኤ እንደሆነ ጠቁሟል::በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ በደሎች እና ከአሰሪዎቻቸው እና ከቀጣሪ ድርጅቶች ጠፍተው የሚመጡ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው መመለስ ሲገባው ከደላሎች ጋር በመመሳጠር ሌላ ስራ በማስገባት ችግሩ እንዲሰፋ ያደረገው እምባሲው እና ሆዳም ዲፕሎማቶቹ ናቸው ሲል ይኸው የኮሚኒቲው

Monday, March 17, 2014

TPLF Security Agent Points Gun at Arrested Female Activist


Semayawi Party (Blue Party) updated its supporters and the world about the arrested party leaders and female activists prison experience.
Semayawi Party- Ethiopia:-
Some updates on arrested Blue Party’s members and leaders
Lets share you some of the news from the prison we are disgusted with!
A day before one of the girls called out late at night, the security guard took her to a room where there was a man namely Sami (Samson I think) who claim to be from security force and ordered her to sit. The talk was started with threatening and tricking. She reported to us that he told her they cannot be successful with peaceful struggle and asked what the Blues are trying to do if that does not work.Emebet Girma, turned 18 this year is on of the arrested female activists
Semayawi Party Legal Defense Fund 2
Emebet Girma, turned 18 this year was quite smart one, she explained to him “all the Blue members and supporter would not do such an act and we stand and struggle peacefully all the way till we are all arrested or killed for freedom with love and truth that for sure will set them free”… the replay that he got from the young girl irritates him and took out his gun and put it on the table… “I wasn’t disturbed,” she said.
After a pause he pointed the gun at her and threatened her. She said, “he asked me what if he shoots me, and I told him to go ahead.” The brave young women told us this in the narrow window that

[የሃረሩ ቃጠሎ ጉዳይ] መቃጠል መቃጠል መቃጠል – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

 
ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም
ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም
ከአስራ ምናምን ዓመታት በፊት ፔሩቪያዊው ኢኮኖሚስት ሄርናንዶ ደ ሶቶ ስለ “ኢንፎርማል” ኢኮኖሚ በጻፈው መጽሃፍ ውስጥ ፣ በአለም ላይ በህጋዊ መንገድ ያልተዘመገበ ከ10 ትሪሊየን ዶላር በላይ ሃብት መኖሩን፣ ይህን ሃብት መዝግቦ የባለቤትነት ህጋዊ መብት በመስጠት ብዙ ዜጎችን ከድህነት ማውጣት እንደሚቻል ገልጾ ነበር። ደ ሶቶ እንደሚለው በደሃ አገራት ሁለት አይነት ኢኮኖሚ አለ። አንደኛው ጥቂቶች የሚያንቀሳቅሱትና በመንግስት እውቅና የተሰጠው ኢኮኖሚ ሲሆን ሌላው ደግሞ መንግስት የማያውቀው በአብዛኛው ህዝብ የሚንቀሳቀሰው ኢኮኖሚ ነው ፤ ይህ ኢኮኖሚ በመንግስት እውቅና ያልተሰጠው በመሆኑ በዚህ ስር የታቀፉ ዜጎች ከባንክ ተበድረው ቢዝነሳቸውን ለማስፋፋት አይችሉም፤ መንግስትም ከእነዚህ ሰዎች ተገቢውን ታክስ አያገኝም። በደሃ አገራት ውስጥ መንግስታት እውቅና ሳይሰጡት የሚንቀሳቀሰው ሃብት እውቅና ከተሰጠው ሃብት ይበልጣል። ደ ሶቶ እንደሚመክረው ህጋዊው የኢኮኖሚ ስርአት የማያውቃቸውን ሀብቶች በመመዝገብና ህጋዊነት በማላበስ ዜጎች ሃብትና ንብረት እንዲያፈሩና ድህነትን እንዲሻገሩ ማድረግ ይቻላል።

የ ደ ሶቶን ሃሳብ ለማየት በአዲስ አበባ የተገነቡ የጨረቃ ቤቶችን እንመልከት። ነዋሪዎቹ ቤቶችን ለመስራት ብዙ ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ አፍስሰዋል፣ ይሁን እንጅ የመንግስትን የባለቤትነት ማረጋገጫ ቁራጭ ወረቀት ለማግኘት ባለመቻላቸው የሰሩት ቤት ሃብት ሊሆን አልቻለም። ቤታቸውን መሸጥ፣ መለወጥ እንዲሁም በባንክ አስይዘው ገንዘብ መበደር አይችሉም። እነዚህ ሰዎች የባለቤትነት ካርታ እስካላገኙ ድረስ ቤታቸው ሃብታቸው ነው ማለት አይቻልም። ነገር ግን የይዞታ ማረጋገጫ ብጣሽ ወረቀት ባገኙ በሰከንድ ውስጥ ቤታቸው ሃብታቸው ይሆናል፣ መሸጥ መለወጥ፣ ቤታቸውን አስይዘው ከባንክ መበደር ይችላሉ። በአንድ ወረቀት የቤቶቹ ባለቤቶች ከድህነት ወደ ሃብት ባለቤትነት ተሸጋገሩ፣ በሌላ አነጋገር የድህነትን መጋረጃ ቀደዱ ማለት ነው። መንግስት ህጋዊ እውቅና ለሌላቸው ሌሎች ቢዝነሶችም ህጋዊ እውቅና ቢሰጥ ፣ ሰዎችን ባለሀብት ማድረግ ብቻ ሳይሆን መንግስትም ከእነዚህ ቢዝነሶች ብዙ ግብር መሰብሰብ ይችል ነበር። በኢትዮጵያ ያለው የገዢዎች ስብስብ ግን ንብረት በማውደም የሚደሰት ይመስላል። ቤት ማፍረስና ንብረት ማቃጠል ልዩ መልክቱ ሆኗል። ባለፉት 22 ዓመታት ስንትና ስንት ቤቶች ፈረሱ፣ ስንቶቹ ተቃጠሉ፣ ስንትና ስንት የአገር ሃብት አብሮ ወደመ፣ ስንቶቹ ደኸዩ፤ ወረቀት በማደል ህጋዊ ማድረግ ሲቻል ሳይቻል ቀረ።
ከረጅም አመታት በሁዋላ የደ ሶቶን መጽሃፍ እንዳስታውስ ያደረገኝ በሀረር በተደጋጋሚ የሚታየው የእሳት ቃጠሎ ነው። የንግድ ቤቶችን የሚያቃጥላቸው መንግስት ከሆነ የመንግስት የድንቁርና ብዛት ልክ ማጣቱን የሚያመለክት ነው። መንግስት ቤቶችን ሲያቃጥል፣ ቤታቸው የተቃጠለባቸው ሰዎች ወደ ድህነት ጎራ መግባታቸውን አያውቅም ለማለት አልደፍርም። እነዚህ ሰዎች ህጋዊ እውቅና የላቸውም ቢባል እንኳን፣ የህጋዊነት ማረጋገጫ ብጣሽ ወረቀት በመስጠት፣ ህጋዊ በማድረግ ድህነትን እንዲሻገሩ ማድረግ ይቻል ነበር። ንብረትን በእሳት በማጋየት የሚገኝ የኢኮኖሚ እድገት ምን እንደሆነ በፍጹም አይገባኝም፤ የማውደም ኢኮኖሚክስ የሚባል ነገር መኖሩንም አላውቅም።
Harar City
መንግስት አነስተኛና ጥቃቅን እንዱስትሪ የሚለው ነገር አለ። ሃሳቡ ፖለቲካዊ ይዘት ባይኖረው ጥሩ ነው። አውሮፓኖች ያደጉት በተለያዩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች በጊዜው አጠራር ( ጊልዶች) ነው። የዛሬዎቹ ግዙፍ የአውሮፓ ኢንዱስትሪዎች በተለያዩ

የጠፋውን የማሌዥያ አውሮፕላን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፤ (ከዚህ በፊት 5 አውሮፕላኖች ጠፍተው እንደነበር ያውቁ ኖሯል?)


ከአትላንታው አድማስ ራድዮ
ስለ ማሌዢያው የበረራ ቁጥር 370፣ የተሰወረ አውሮፕላን መዘገብ እጅግ ከባድ ነው። ምክንያቱም ነገሮች በየደቂቃው ይቀያየራሉና። ገና ሲጀመር፣ አውሮፕላኑ ለመጨረሻው ጊዜ ድምጽ ያሰማበት ሰአት ልክ አልነበረም፣ ከዚያ ቀጥሎ ሁለት ጥቁሮች በሃሰት ፓስፖርት ተሳፍረዋል ተባለ፣ ጥቂት ቆይቶ ጥቁር አይደሉም፣ ኢራናውያን ናቸው ተባለ፣ .. ከዚያ በኋላ 6 ሰዎች አውሮፕላኑ ውስጥ ሊገቡ ካሉ በኋላ ሃሳባቸውን ቀይረዋል ተባለ፣ ጥቂት ቆይቶ ስድስት አይደሉም 2 ናቸው፣ እነሱም ገና ከቤታቸው ሳይወጡ ሃሳባቸውን የቀየሩ ናቸው ተባለ ….፣ ከዚያ ደግሞ አውሮፕላኑ ከጠፋ ከ 48 ሰአት በኋላ የአንዳንድ ተሳፋሪዎች ስልክ ይጠራል ተባለ . ጥቂት ቆይቶ ፣ ውሸት ነው የማንም ስልክ አይጠራም ተብሎ ተነገረ …፣ ከዚያ በኋላ ቻይናዎች በአንድ የቻይና ባህር ላይ የአውሮፕላኑ ስባሪን አይተናል አሉ ተባለ ..፣ ጥቂት ቆይቶ ውሸት ነው አላዩም በሚል ተስተባበበለ።
Malaysia-Airlines
እያንዳንዱ የሚነገር ጉዳይ ልብ የሚያንጠለጥል ቢሆንም፣ በዚህ በዓለማችን የበረራ ታሪክ እጅግ ውስብስብና አሰገራሚ የሆነ መሰወር ጉዳይ ሁሉም መላምቱን ለመስጠት ቢቸኩል የሚፈርድ አልነበረም። እንደተባለው አውሮፕላኑ በቴክኒክ ችግር አይደለም ድምጹን ያጠፋው፣ እንደተባለው ካቅሙ በላይ የሆነ ነገር ገጥሞትም አይደለም።
ምናልባት ያለፉትን ሰባት ቀናት የተለያዩ ነገሮችን ሰምታችሁ ይሆናልና ቀጥታ ወደፊት በመፈናጠር ዛሬ ጉዳዩ ከደረሰበት ነገር እንጅምር። ከዚያ በኋላ ከዚህ በፊት የጠፉ አውሮፕላኖችን ታሪክ እናሳያችኋለን።
ዛሬ ጠዋት የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአየር ሃይል ሃላፊያቸው ያሉበትን ደረጃ ለመናገር ብቅ ብለው ነበር። በነሱ መረጃ መሰረት ዛሬ የተነገረው ትልቁ ነገር አውሮፕላኑ በቴክኒካል ችግር ሳይሆን ሆን ተብሎ ድምጹን ማጥፋቱንና ፣ ምናልባትም የመጨረሻውን ግንኙነት ከተቆጣጣሪዎች ጋር ካደረገ በኋላ ቢያንስ 7 ሰአት ያህል ሳይበር እንዳልቀረ መናገራቸው ነው፡፡ ያ ማለት አውሮፕላኑ ተጠልፏል ወይም ታግቷል። ይህ የሆነው ደግሞ ወይም ከተሳፋሪዎች መካከል በአንዱ ወይም ደግሞ እንደ ኢትዮጵያው

Sunday, March 16, 2014

አንድነት እና መኢአድ የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት ፊርማ ሊፈራረሙ ነው


 

 

UDJ
aeupየአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤትና የመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት አባላት በጋር ባካሔዱት ስብሰባ ሁለቱ ፓርቲዎች የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት ፊርማ እንዲያደርጉ መመሪያ ማስተላለፋቸውን ስብሰባውን የተከታተለው የፍኖተ ነፃነት ባልደረባ ዘገበ፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ላዕላይ ምክር ቤት አባላት ዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት ባደረጉት ስብሰባ የሁለቱ ፓርቲዎች በአስቸኳይ እንዲዋሀዱ መመሪያ ያስተላለፉት ሁለቱን ፓርቲዎች ፓርቲዎች ለማዋሀድ እያሸማገሉ የሚገኙ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦች የተካተቱበት ኮሚቴ ያቀረባቸው የማስማሚያ ነጥቦች ከቀረቡ በኋላ እና የሁለቱም ፓርቲዎች ፕሬዘዳንቶችና የውህደት ኮሚቴ አባላት ውህደቱ የዘገየበትን ምክንያት ከዘረዘሩ እንዲሁም የሁለቱ ፓርቲዎች ምክር ቤት አባላት ሰፊ ውይይትና የመፍትሔ ሀሳብ ካቀረቡ በኋላ ነው፡፡ የቅድመ ውህደት ፊርማው በሚፈረምበት ዕለት ሁለቱም ፓርቲዎች የውህደቱን ሂደት የሚያመቻቹ ወኪሎቻቸውን እንደሚያሳውቁም የፍኖተ ነፃነት ባልደረባ ዘግቧል፡፡
ምንጭ፣  http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13623

የስርዓቱ ደጋፊ የሆነችው ድምጻዊት ሃመልማል አባተ ለሁለተኛ ጊዜ ከአሜሪካ አፍራ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰች


በአፍቃሬ ወያኔነቷ የምትታወቀው ድምጻዊት ሃመልማል አባተ አዲስ አልበሟን ለማስመረቅና የተለየያዩ ኮንሰርቶችን ለመሥራት ወደሰሜን አሜሪካ መጥታ የነበረ ቢሆንም በደረሰባት ቦይኮት በተመልካች እጦትና በፕሮሞተሮች መጥፋት አፍራ ወደ አዲስ አበባ መመለሷ ታወቀ።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ በሰብአዊ መብት ጥሶትና ንጹሃንን በእስር ቤት ያሰቃያል እየተባለ በዓለም አቀፍ ተቋማት ጭምር የሚነገርለትን የወያኔ/ኢሕአዴግ ስርዓት በመደገፍ የምትታወቀው ድምጻዊት ሃመልማል አባተ በዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛ ገንዘብ ወጥቶ በቨርጂኒያ ክሪስታል ከተማ በሂልተን ሆቴል የሲዲ ማስመረቂያ ኮንሰርት አዘጋጅታ 55 ሰዎች ብቻ የተገኙ ሲሆን አንድም አርቲስት በሲዲ ምርቃቱ ላይ አለመገኘቱ አነጋጋሪ ሆኗል። በተለይ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በርካታ አርቲስቶች የሚገኙ እንደመሆኑ መጠን በሃመልማል አባተ ሲዲ ምርቃት ኮንሰርት ላይ አንድም አርቲስት አለመገኘቱ ኢቢኤስ የተባለው ቲቪ ሳይቀር እንዳስገረመው በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል።
(ሃመልማል በዲሲ አዘጋጅታቸው የነበረውና በተመልካች ድርቅ የተመታው የሲዲ ምርቃት ኮንሰርት ፍላየር ይህ ነበር)
(ሃመልማል በዲሲ አዘጋጅታቸው የነበረውና በተመልካች ድርቅ የተመታው የሲዲ ምርቃት ኮንሰርት ፍላየር ይህ ነበር)

ሃመልማል በወያኔ/ኢህአዴግ እየተረገጠ ያለውን ሰፊውን ሕዝብን ክዳ ለመሬት ቀሚው፣ ለመሬት ሻጩ፣ ለበዝባዡ፣ ለጨፍጫፊውና ለሰብአዊ መብት ረጋጩ ወያኔ ተቆርቋሪ ሆና በመቅረቧ ከጥቂት ዓመታት በፊት` በጀርመን ሃገር የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጅታ ሕዝቡ ቦይኮት በማድረጉ 18 ሰዎች ብቻ የተገኙ ሲሆን ከ3 አመት በፊትም እንዲሁ ወደ ሚኒሶታ በመምጣት ኮንሰርት አዘጋጅታ ከ12 ያነሰ ሰው ብቻ በመገኘት በተመልካች ድርቅ ተመትታ ወደ ሃገሯ ተመልሳለች፤ ያሉት የመረጃ ምንጮች ሃመልማል ከስርዓቱ ጋር ያላት የጥቅም ግንኙነት የተረሳላት መስሎ ወደ አሜሪካ በድጋሚ ብትመጣም በዋሽንግተን ዲሲ 55 ሰዎች ተግኝተው

Ethiopian Prince to Visit Historical Churches and Institutions in Chicago on the 60th Anniversary of King Haile Selassie’s Visit in 1954


 
As movies such as “12 Years A Slave” are praised for their depiction of black history during slavery, the Queen of Sheba Historical Research Foundation, Inc., in Chicago believes black history must not be restricted to the history of slavery alone.
prince
Join the Queen of Sheba Foundation at the DuSable Museum in Chicago on June 29, 2014 when Prince Ermias Sahle Selassie, grandson of King Haile Selassie I, presents an enlighten scholarly presentation on “The Solomonic Dynasty and The Throne of David in Ethiopia. Come learn and reconnect to your Royal History–before slavery.
Chicago, Illinois
In answer to the question “Can knowledge of self really make a difference?” Wolette Selassie President of the Queen of Sheba Foundation responds, “It is important for our people, particularly black youth, to know about the history of ancient Ethiopia, which we are about to reveal, because we believe it will offer a higher cultural identity for black Americans than a history which is restricted to slavery alone.”
In the quest to reconnect black Americans to their ancient royal history, before slavery, Queen of Sheba is hosting His Highness Prince Ermias Sahle Selassie, grandson of King Haile Selassie I, at the DuSable Museum in Chicago on June 29 2014. Prince Ermias will be presenting a lecture on ancient

Saturday, March 15, 2014

የነአርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን አዲስ ሃይማኖት “ቅዱስ ኤልያስ ይዞት የመጣውን መፅሐፍ” ቤተ ክርስትያን እንድትቀበል ጠየቀ


 
Jemanesh Solomon
ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው የነአርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን አዲስ ሃይማኖት “ቅዱስ ኤልያስ ይዞት የመጣውን መፅሐፍ” ቤተ ክርስትያን እንድትቀበል ጠየቀ። የጋዜጣው ዘገባ እንደወረደ ይኸው፦
መጽሐፉ ለአቡነ ማትያስና ለጠ/ሚ ኃይለማርያም እንዲደርሳቸው ተደርጓል
ደብዳቤው ለእስራኤሉ ጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታናሁ እና ለተመድ ተልኳል

ከተፃፈ ከ2 ሺህ ዓመታት በላይ አስቆጥሯል የተባለውንና ስለ ቅዱስ ኤልያስ መምጣት ምስጢር የሚተነትነውን መጽሐፍ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተቀብላ ወደተለያዩ ቋንቋዎች በማስተርጎም ምዕመናኖችን እንድታስተምር፣ “ማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ” ለቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በጻፈው ደብዳቤ ጠየቀ፡፡
ማህበሩ፤የመጽሐፉን ኮፒዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና ለብፁዕ አቡነ ማትያስ ህዝቡን እንዲያስተምሩበት ከሚያሳስብ ደብዳቤ ጋር መላኩን አስታውቋል፡፡
አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን አባል የሆነችበት ማህበረ ሥላሴ፤“ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ለሁለት ሺህ ዘመን ስትጠብቀው የቆየችውን ምስጢራዊ መጽሐፍ በአደራ የመረከብና ለዓለም ሁሉ የማሳወቅ ፅኑ ኃላፊነትን ይመለከታል” በሚል ርዕስ ለፓትርያርኩ፣ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲሁም ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትናሁ እና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፃፈው ደብዳቤ “ማህፈድ ብርህት ዘዲዮስቆሮስ አንበሳ” በሚል ርዕስ በግዕዝ ቋንቋ የተፃፈውን መጽሀፍ፣ የቤተ-ክርስቲያኗ ሊቃውንት ተቀብለው ምእመናኑን ስለ ቅዱስ ኤልያስ እና ትክክለኛይቱ ሰንበት እንዲያስተምሩበት አሳስቧል፡፡
ደብዳቤው ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የተላከው ኢትዮጵያና እስራኤል በመንፈሣዊ አሰራር አንድ ስለሚሆኑበት ሁኔታ

በጎንደር አድማ መርታችኋል የተባሉ 6 ታክሲ ሹፌሮች በእስር ቤት እየተንገላቱ ነው

 
የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)
የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

ክሱን ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ለማገናኘት የሞከረው ፖሊስ አልተሳካለትም
ምንሊክ ሳልሳዊ :- በጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ ላይ ተቃውሞ አሰምታችኋል አድማውን መርታችኋል በሚል ሰበብ የታሰሩ 6 ሰዎች እንዳሉ ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል:: ከአንድ ወር በፊት የጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች አዲሱን የትራፊክ የቅጣት ደንብ በመቃወም የስራ ማቆም አድማ መምታታቸውን ተከትሎ አድማውን አስተባብረዋል በሚል ሰበብ ተፈጥሮ ከየመንገዱ ከስራቸው እና ከየቤታቸው ታፍነው የተወሰዱ የታክሲ ሹፌሮች በእስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ መሆኑን ለወሕኒ ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል::
ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት ቀርበው የዋስትና መብታቸው ሳይከበር ወደ እስር ቤት የተመለሱት የታክሲ ሹፌሮች ከሰማያዊ ፓርቲ የመጣ ትእዛዝ ነው የስራ ማቆም አድማ ያደረጋችሁት በሚል ጉዳዩን ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በሃሰት ለማገናኘት በፖሊሶች በሃይል ለማሳመን ጥረት ቢደረግም እንዳልተሳካ ምንጮቹ ገልጸው እስካሁን ምንም አይነት መረጃም ሆነ ማስረጃ መርማሪዎች

Friday, March 14, 2014

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ታሪክ ሊሆን ነው


ከሰሜን ኮከብ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ክፍል ( ዲፓርትመንት) መዳከሙን ስሰማ በጣም አዘንኩ። ዲፓርትመንቱ እኔ በነበርኩበት ጊዜም ፣ ከዘርና ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ፣ ብዙ ችግሮችን ያስተናግድ ነበር። ኢህአዴግ ” ዲፓርትመንቱ የነፍጠኛው መመሸጊያ ዋሻ ሆኗል” በሚል ብሄር ብሄረሰቦች በብዛት እንዲገቡበት ይወተውት ነበር። አንድ የአማራ ተወላጅ ተማሪ ከፍተኛ ነጥብ ቢያመጣም፣ ከሌላው ብሄረሰብ ሰው ካልታጣ በስተቀር፣ መምህር ሆኖ የመቀጠር እድል አልነበረውም። በ1992 ዓም ነው፣ሁለት ሰቃይ ጓደኞቼ መምህር ለመሆን ያመለክታሉ። በጊዜው የዲፓርትመንቱ ሃላፊ የነበሩት ትግራዋይ ዶክተር ፣ሰቃዮቹን ትተው፣ አንድ የኦሮሞ እና አንድ የትግራይ ተወላጅ ምሩቃንን ይቀጥራሉ። አዲሶቹ ተቀጣሪዎች የነበራቸው ድምር ነጥብ ( Cumulative GPA) ጓደኞቼ ከነበራቸው ነጥብ በጣም ያነሰ ነው። በእንዲህ አይነቱ አሰራር ልባቸው የተሰበረው ጓደኞቼም እስከ ሴኔቱ ድረስ ክስ መሰረቱ፣ በመጨረሻ ያገኙት መልስ ግን ” የብሄር ተዋጽዎን ለመጠበቅ ሲባል የተወሰደ እርምጃ ነው” የሚል ነበር።
ለታሪክ ዲፓርትመንት መዳከም ዋናው ምክንያት የዘር ፖለቲካ የትምህርት ስርዓቱን መቆጣጠሩ ነው።
addis ababa un
በታሪክ ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ብሄርና ፖለቲካ ለይተው ሲደባደቡ አስታውሳለሁ ። የተወሰኑ የኦሮሞ ወይም የትግራይ ተወላጆች የተጻፉ ታሪኮችን ወይም ስያሜዎችን ለመቀበል እየተቸገሩ ከአስተማሪዎች ጋር ዘወትር ይጣሉ ነበር ። መምህራን “ማስተማር አልቻንልም” ብለው ስራ እስከማቆም የደረሱበት ጊዜም ነበር። ያም ሆኖ በማይነር ( በሁለተኛ ትምህርት) ከሚማሩት ውጭ፣ እጅግ በርካታ ተማሪዎች ታሪክ ያጠኑ ነበር ። ታሪክ ለመማር የመጡ ሌሎች አፍሪካውያንና ጥቁር አሜሪካውያንም ነበሩ። ተማሪው

“በሐረር ከተማ በደረሰው ቃጠሉ ከዛም የክልሉ ፖሊስ በንጹሃን ዜጎች ላይ ጉዳት ማድረሱን በቸልታ አንመለከተውም” – አንድነት


ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
Harar City
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

በሐረር ክልል ሕዝብ ላይ የደረሰውን ከፍተኛ ጉዳት አንድነት በቸልታ አይመለከተውም
የካቲት 30 ቀን 20006 ዓ.ም በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ በጀጎል ሸዋበር በደረሰው ቃጠሎ እና ከዚያም በኋላ የክልሉ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ በዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱ የፓርቲያችንን አመራሮች፣ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ያሉ አባላትና ደጋፊዎችን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡
ምንም እንኳን የቃጠሎው መንስኤ ተጣርቶ ይፋ ያልተደረገ ቢሆንም በጀጎል ሸዋ በር እየደረሰ ያለው ተደጋጋሚ ቃጠሎ ድንገቴ ነው ለማለት የሚያስደፍር አይደለም፡፡ በተለይም በየካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም የተነሳውን ቃጠሎ በተገቢ ፍጥነት ለመቆጣጠር የክልሉ መንግስት ፍላጎት ያልታየበት መሆኑ፤ ይልቁንም ግሬደር መኪና አስጠግቶ ቦታውን ለማፅዳት መሞከሩ አጠያያቂ ነው፡፡ የክልሉ መንግስት ቃጠሎውን ለመቆጣጠር ተገቢውን ሁሉ ባለማድረጉ የጉዳቱ ሰለባ የሆነው ህዝብ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበት ክፉኛ እንደ ተማረረ በዚሁ ምክንያትም ቁጣ ተቀስቅሶ ፖሊስ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት ማድረሱንም በክልሉ የሚገኙ

Thursday, March 13, 2014

Health: ስለ ኩላሊት ጠጠር ሊያውቁ የሚገባዎት 5 ነገሮች


ከማስረሻ መሐመድ
የኩላሊት ጠጠር የሚባሉት አብዛኛውን ጊዜ የካልስየም ክሪስትያል የሚሠሯቸው ድንጋዮች ሲሆኑ በኩላሊት ውስጥ የሽንት መጠራቀሚያ ቦታ ላይ የሚፈጠሩም ናቸው፡፡ ይህ ጠጠር መሠል ባዕድ ነገር ብዙ ጊዜ ባለበት ቦታ ላይ ችግርን የሚፈጥር ሳይሆን ሆኖም ግን የሽንት ቧንቧ ላይና ወደ ሌሎች አካላቶች ላይ መግባት ሲጀምር ችግር እየፈጠረ እንደሚመጣ በዘርፉ ያሉ ባለሞያዎች ይገልፃሉ፡፡
ኩላሊት ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ በሰውነታችን ውስጥ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ከደም እያጣራ በሽንት መልክ ማስወገድ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ታዲያ አንዳንድ ሚኒራልና ኬሚካሎች ኩላሊት ውስጥ በመቅረት ወደ አሸዋነት ይቀየራሉ፡፡ ከጊዜ በኋላም እነዚህ አሸዋ መሰል ነገሮች ወደ ድንጋይ
በመቀየር አደጋን ያስከትላሉ ማለት ነው፡፡

Kidney stone
1ኛ. የኩላሊት ጠጠር ለምን ይከሠታል?
የኩላሊት ጠጠር በአንዳንድ ሰዎች ላይ በምን አማካኝነት ሊከሠት እንደሚችል የተረጋገጠ ነገር የለም በአንዳንዶች ላይ ደግሞ በምን እንደተከሰተ ማወቅ የሚቻልበት ደረጃ እንዳለ ባለሞያዎቹ ያስረዳሉ፡፡ ይሁንና ከላይ እንደጠቀስነው ኩላሊት ደምን ሲያጣራ በሚቀሩ ሚኒራሎችና ሌሎች
ጠጠር ነገሮች አማካኝነት ሊከሰት እንደሚችል ነው፡፡
2ኛ. የኩላሉት ጠጠር ተጋለጮች እነማን ናቸው?
• ከ8ዐ በመቶ በላይ የሚሆነው የኩላሊት ጠጠር ተጠቂ ወንዶች ናቸው፡፡
• በዘር አማካኝነት ሊተላለፍ እንደሚችልም ይነገራል በተለይ እንደ ሲስታይን፣ኦክስሬት እና ዩሪክ አሲድ የመሳሰሉ ኬሚካሎችን

የሚሊየኖች ድምጽ – የሚሊየኖች ድምጽ እንቅስቃሴ ለመደገፍ በዉጭ ግብረ ኃይል ተቋቋመ !

አገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን አሳዛኝ ሁኔታ ከማንም የበለጠ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይረዳዋል ብለን እናምናለን። የኢሕአዴግ መንግስት፣ ላያ ላዩን «በዴሞክራሲ አምናለሁ» ቢልም፣ ፍጹም አምባገነን በሆነ መልኩ ፣ ሕዝቡን አፍኖ፣ እያሰራ፣ እየገደለ፣ ዜጎችን እያፈናቀለ፣ ከሃያ አመታት በላይ ቆይቷል። በአብዛኛዉ ሕዝብ ዘንድ እየተጠላ፣ ይሄን ያህል አመት በስልጣን መቆየት የቻለው፣ አገዛዙ በዋናነት ኢትዮጵያዊያን መከፋፈል በመቻሉና ዜጎች ደፍረው ለመብታቸው እንዳይቆሙ በፍርሃት እንዲተበተቡ በማድረጉ ነው። ይሄንን ለማስቆም ሕዝቡን ማስተባበርና ማደራጀት ቀዳሚና ብቸኛ አማራጭ ነው።
አገር ቤት በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶ አሉ። ከነዚህ ድርጅቶች መካከል አንዱ የአንድነት ፓርቲ ነው። የአንድነት ፓርቲ «የሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትህ» እና «የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት» በሚል ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ተዘጋጅቷል። ይህ እንቅስቃሴ የአንድ ፓርቲ እንቅሳቅሴ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንቅስቃሴ እንደመሆኑ፣ በአገራችን ዴሞክራሲና የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ዜጎች ሁሉ ሊቀላቀሉት፣ ሊደግፉት፣ የራሳቸው ሊያደርጉት የሚገባ እንቅስቃሴ ነዉ። ይህ እንቅስቃሴ የሚሊዮኖች እንቅስቃሴ ነው። የእያንዳንዳችን እንቅስቃሴ ነው።
በቅርቡ በባህር ዳር አስደናቂ ሰልፍ መደረጉ ይታወሳል። በቦታዉ የተገኙ ወገኖች ድምጻቸውን ያሰሙት አንድን ፓርቲ ብለው አልነበረም። ኢትዮጵያን ብለው ነዉ እንጂ። የባህር ዳሩ ሰልፉ ያማከለው በአንድ ድርጅት ዙሪያ አልነበረም። ነገር ግን በኢትዮጵያ ዙሪያ እንጂ። ይህ በባህር ዳር የተደረገውን አይነት የነጻነት እንቅስቃሴ በተጧጧፈ መልኩ በመላው አገሪቷ ማድረጉ አስፈላጊ ነው።
በአገሪቷ ሕገ መንግስት አንቀጽ 30 መሰረት፣ የዜጎች የመሰባሰብ ፣ በሰላም ትእይንተ ሕዝብ የማድረግ ሙሉ መብት የተረጋገጠ ነው። በመሆኑም ይህ የሚሊዮኖች ለነጻነት ንቅናቄ ሰላማዊና የአገሪቷ ሕግ በሚፈቅደው መሰረት የሚደረግ በማንም ዜጋ ወይንም

ትዝብት – ደርሶ መልስ ዲያስፖራ (ኢትዮጵያ ደርሶ የመጣ ዲያስፖራ የሚነግራችሁ እውነት) (አንደኛ)


 
አትክልት አሰፋ (ቫንኩቨር) – ጋዜጠኛ
ነገሩ የሆነው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ነው። ቆነጃጅት ወጣት ሴት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ባሉ የከተማው ደለላዎች ጋር በመተባበር እጅግ ዘግናኝ ስራ ይሰራሉ። ደላሎቹ የቆነጃጅቶቹን ተማሪዎች ፎቶ የያዘ ትልቅ ካታሎግ ይዘው ከአዲስ አበባም ሆነ ከአቅራቢያው ከተሞች አለዚያም ከዚያው ከዲላ ከተማ ብቅ የሚሉ ሃብታም ደንበኞቻቸውን የተማሪ ኮረዶችን ፎቶ በመስጠት ያስመርጣሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ (ፎቶ ከፋይል)
የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ (ፎቶ ከፋይል)
ሰውየው ውብ ወጣት ተማሪ ኮረዳ እንደሚፈልግ በሰው በሰው የተገናኘውን ደላላ ይጠይቃል። እናም ከተሰጠው የፎቶ ድርድር ላይ ማመን ያቃተውን የአንዷን ውብ ፎቶ እያሳየ ‘ይህችን ታውቃታለህ?’ ሲል ይጠይቃል። የደላላ መልስ አንድ ነው… ሁሉንም ስለሚያውቃቸው አልተቸገረም ‘አዎ እሷን ይፈልጋሉ?’ ሲል ይጠይቃል። ሰውየውም ‘እባክህ’ ሲል በመማጸን ፈቃደኝነቱን ይገልጻል። ከፊቱ የመጣለትን ገቢ ተደራድሮ ልጅትን ለመጥራት ይሮጣል። ደላላው።
እናም ቆንጅት ተበጃጅታ፣ አምራና ደምቃ ትመጣለች። በቀጥታ ወደ ሰውየው መኪና ስትደርስ ሰውነቷ ይርዳል። በቁጣ አይኑ የተንቀለቀለው ሰውየም ወደ ልጅቷ ያፈጣል… በቀጥታ ተንደርድሮ የልጅቷን ክርን ይይዛል… ደላላው እየሆነ ያለውን ሊረዳ አልቻለም… የልጅቷን እጅ የያዘው ሰው (ደንበኛ) የልጅቷ ወላጅ አባት ኖሯል።
ኢትዮጵያ ደርሶ የሚመጣ የውጭ ሀገር ነዋሪ (ደርሶ መልስ ዲያስፖራ) በተለያየ አይነት እይታ የተለያዩ እውነታዎችን ይዞላችሁ

Wednesday, March 12, 2014

የአውሮፓ ሕብረት በአዲስ አበባ መንግስትን እና ተቃዋሚዎችን እያነጋገረ ነው


የፖለቲካ ምህዳር መስፋት፣ የ2007 ምርጫ፣ የታሳሪዎች ጉዳይ በአጀንዳነት ተነስቷል
ከዘሪሁን ሙሉጌታ
በአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካና የኢትዮጵያ ቋሚ አምባሳደር የኢትዮጵያ መንግስትንና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እያነጋገረ ነው። የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር አማካኝነት መካሄድ የጀመረው ውይይት በሀገሪቱ የፖለቲካ መህዳር መስፋት፣ በ2007ቱ ምርጫ፣ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲሁም በሀገሪቱ ስላለው የሰብአዊና የዴሞክራሲ መብቶች ዙርያ መሆኑ ታውቋል።
au addis ababa
ባለፈው ዓመት የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር በመሆን የተሾሙት አምባሳደር ቻንታል ሔብሪች ኅብረቱን በመወከል በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የበለጠ የሚከበሩበትን ገንቢ አማራጭ እያፈላለጉ ነው። በዚህም የአምባሳደሯ እንቅስቃሴ መሠረት የካቲት 26 ቀን 2006 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በመገኘት ከሌሎች የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር በመሆን በሀገሪቱ አጠቃላይ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ውይይት አካሂደዋል። አምባሳደሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ውይይት ካካሄዱ ከአምስት ቀናት በኋላ በሀገሪቱ ካሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ ከሆነው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባላት ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት አካሂደዋል።
በአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካና የኢትዮጵያ አምባሳደር ቻንታል ሔብሪች ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ጋር በተወያዩበት ወቅት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ዴሞክራሲያዊ ሕጋዊ መሠረት የተከተለ እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ላይ ቢሆንም፤ የበለጠ መሻሻል በሚገባቸው ቀሪ ስራዎች መወያየታቸው መዘገቡ ይታወሳል። በተጨማሪም በመጪው ዓመት የሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ በሚሆንበት ጉዳይ ላይ መወያየታቸው አይዘነጋም።
በተመሳሳይ ባለፈው ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም በአውሮፓ ኅብረት ጽ/ቤት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውና የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ከኅብረቱ አምባሳደር ቻንታል ሔብሪች እንዲሁም በአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድና የህንድ ውቅያኖስ ክፍል

የሀገራችንን ድንበር ለሱዳን መስጠቱን እንደሚቃወሙ በፊርማዎ ያስመዝግቡ

 
meles cartoon
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት በገዥው ህውሀት/ኢህአዴግ እና በሱዳን መንግስት መካከል እየተካሄደ ያለውን ሴራ እንቃወማለን፡፡
ይህ ሴራ የሚካሄደው ህዝብን በማይወክል ጠባብ ቡድን በመሆኑ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጀርባ የሚፈጸመውን ማንኛውንም ውል እንደማንቀበል ካሁኑ እንዲታወቅልን ለተባበሩት መንግስታት፣ ለአፍሪካ ህብረት እና ለሌሎችም አለም አቀፍ ድርጅቶችና መሪወች የሚቀርብ የተቃውሞ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን።
እርስም ስዎን በማስፈር የዚሁ ታሪካዊ እንቅስቃሴ አካል እንዲሆኑ በትህትና እንጠይቃለን። የናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ዳር ድንበር ሲደፈር ሁሉም የሚችለውን ማድረግ ሀገራዊ ግዴታው ነው።
ለመፈረም የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ
http://www.ipetitions.com/petition/stop-secret-border-deal-between-ethiopia-and-Sudan
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
zehabesha.comhttp://www.zehabesha.com/amharic/archives/13540

Tuesday, March 11, 2014

አንድነት – የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄን በተመለከተ የአዉሮፓ ሕብረት አንድነትን አነጋገረ

በኢትዮጵያ የአዉሮፓ ሕብረት ልኡካን ቡድን መሪ አምባሳደር ቻንታል ሔበሬሽ፣ በአዉሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ እና የሕንድ ዉቂያኖስ አካባቢ ዴስክ ኦፌሴር ቪክቶሪያ ጋርሲያ ጉሌን እንዲሁም ቶማስ ሁይገባርቴስ የተሰኙ ፣ የአዉሮፓ ሕብረት ሃላፊ ፣ በነርሱ አነሳሽነት፣ ከአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ጋር ሰፊ ዉይይት አደረጉ።
ከአንድ ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ስላለው የዲሞክራሲ ግንባታ ዙሪያ ከጠ/ሚኒስተር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር እንደተነጋገሩ የገለጹት የአዉሮፓ ሕብረት ባለስልጣናት፣ የአንድነት ፓርቲ በጠራዉ የሚሊዮኖች ድምጽ ሁለተኛ ዙር ንቅናቄ እንዳሳሰባቸው በመገለጽ፣ አንድነት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ፣ ፓርቲው ፍቃደኛ ከሆነ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው፣ ጠይቀዋል።
የአንድነት ፓርቲ ወክለው ከአዉሮፓ ሕብረት ጋር የተነጋገሩት ሊቀመንበሩ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉና የሕዝብ ግንኙነት ክፍል

Health: በዱካክ ተሰቃየሁኝ፤ ምን መፍትሄ አላችሁ? – (የሃኪሙን ምላሽ ይዘናል)


ዕድሜዬ 17 ዓመት ሲሆን በ10+3 ፕሮግራም የኮሌጅ ትምህርቴን ከጀመርኩ ወራትን አስቆጥሬያለሁ፡፡ ከዚህ በላይ ግን በትምህርቴ መግፋት የምችል አይመስለኝም፡፡ የደረሰብኝ ችግር ትምህርቴን ማስተጓጎል ብቻ ሳይሆን አጠቃላዩ ኑሮዬንም ምስቅልቅሉን እያወጣው ነው፡፡
እንደሚታወቀው ክላስ ገብቼ ትምህርት መማር የምችለው ቀን ቀን ነው፡፡ ከአንድ ወር ገደማ በፊት ይመስለኛል ክፍል ውስጥ እንቅልፍ እየወሰደኝ ተቸግሬያለሁ፡፡ ከአየሩ መቃትነት የተነሳ ደግሞ ታግዬ እንኳን የምቆጣጠረው አልሆነልኝም፡፡ ይህ ችግሬ በአሁኑ ጊዜ በጣም እያሳፈረኝ ነው፡፡ ችግሬን እንደ ችግር ቆጥሮ የሚያዝንልኝ ሰው እንኳን የለም፡፡ በስርዓት ተቀምጬ አስተማሪ በምከታተልበት ሳላስበው ዥው ያለ እንቅልፍ ይወስደኛል፡፡ ግንባሬን ከዴስኩ ጋር የማጋጭበት ጊዜም ብዙ ነው፡፡ይህን ችግሬን ያወቁ ልጆች ወደ ኋላ አካባቢ እንድቀመጥ መከሩኝና ያሉትን አደረግሁ፡፡ እኔ ስተኛ ግን ክላሱ እስኪያልቅ ድረስ የሚቀሰቅሰኝ ሰው የለም፡፡ ይህስ ባልከፋ፣ ሆኖም ወዲያው እንቅልፍ እንደወሰደኝ የሚያሳቅቅ ነገር ይደርስብኛል፡፡ ምን መሰላችሁ ይሄ እንደ ዱካክ ነገር ደረቴን ፈጥርቆ ይዞ እንዳልንቀሳቀስ ያሳስረኝና ሳላስበው ቀጭን ጩኸት አሰማለሁ፡፡ በዚህ ጊዜ ነው መምህሩ መተኛቴን የሚያውቁት፡፡ ተቀስቅሼ ስነቃ ደግሞ ተማሪው ሁሉ እየሳቀብኝ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ሁኔታ እንዴት አድርጌ ነው የምማረው? ይኸው ትምህርት ካቋረጥኩ ሁለት ሳምንት ሆኖኛል፡፡
ይህ ዱካክ እና በቀን የመተኛት አባዜ መፍትሄ አለው ትላላችሁ? ማብራሪያችሁን በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡
የእናንተው ጢኖ

የዶ/ር ዓብይ ዓይናለም ምላሽ፡- ውድ ጢኖ ለጥያቄህ ልባዊ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን፡፡ ሳይታሰብ እና ሳፈለግ የሚመጣ የቀን እንቅልፍ በአጠቃላይ ህይወት ላይ የሚያመጣው ምስቅልቅ እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑ ቅድሚያ ሰጥተነዋል፡፡
ምናልባት ለትምህርትህ ከምትሰጠው ላቅ ያለ ግምት አንፃር ክፍል ውስጥ ተቀምጠህ የማንቀላፋቱን ነገር የበለጠ ትኩረት ሰጠኸው እንጂ ህመሙስ ከዚህ የባሰም ፈተና ሊያስከትልብህ ይችላል፡፡ ሳይፈልጉ በቀን መተኛት በጣም መጥፎ ክስተት ነው፡፡ ህመሙ በህክምናው ዓለም ‹‹Narcolepsy›› ተብሎ ይጠራል፡፡
‹‹Narcolepsy›› የእንቅልፍ መዛባት ቢሆንም ከሌሎች ተያያዥነት ካላቸው የእንቅልፍ መዛባት ችግርህ ለየት የሚያደርገው ቁጥራቸው በጣም ውስን በሆኑ ሰዎች ላይ የሚከሰት ህመም በመሆኑ ሳቢያ ነው፡፡ አልጋ ላይ ተጋድመው አይናቸውን ቢጨፍኑም እስከ ውድቅት ሌሊት ወይም እስከ ንጋት ድረስ እንቅልፍ አልወስድ ብሏቸው ሲገላበጡ የሚያድሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርጋቸውም ግማሽ ሰዓት ወይም አንድ ሁለት ሰዓት ብቻ ከቆዩ በኋላ ተመልሰው የሚነቁና የቀረውን የሌሊት ክፍል ፈጠው የሚያድሩም ጥቂት አይደሉም፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ጠዋት ከእንቅልፋቸው መንቃት ተስኗቸው ተጋድመው ያረፍዳሉ፡፡ ከዚህ አንፃር ‹‹Narcolepsy›› የጥቂቶች ብቻ ችግር ነው፡፡
sleep disorder
‹‹Narcolepsy›› በጣም አደገኛ ህመም ነው፡፡ የዕለት ስራን በወጉ ለማከናወን፣ ለመብላት፣ ለመዝናናት፣ ወዲያ ወዲህ ብሎ

Saturday, March 8, 2014

ለአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ፍትሃትና ሽኝት ሲባል ቅዳሴ መቋረጡ ምዕመናኑን አሳዘነ


(ዘ-ሐበሻ) የኦህአዴድ ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት ዓለማየሁ አቶምሳ የቀብር ስነ ሥነ ሥርዓት በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ዛሬ ተፈጸመ። የርሳቸውን ሞት ተከትሎም ዛሬ 5 ኪሎ በሚገኘው ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን የክልሉ ፕሬዚዳንትን ፍትሃትና በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገውን የሽኝት መርሃ ግብር ምክንያት በማድረግ ከጠዋቱ 8:30- እስከ 9፡00 ሰዓት ማለቅ የነበረበት ቅዳሴ ተቋርጦ በጠዋቱ 7 ሰዓት ላይ መፈጸሙ ምዕመናኑን ማስቆጣቱን ለዘ-ሐበሻ የደረሱት መረጃዎች ያመለክታሉ።
Alemayehu Atomsa
ለአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ስንብት በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲደረግ ቅርብ ቤተሰቦቻቸው፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ክልሎች የስራ ሃላፊዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ጀምሮ እንዳጀቧቸው የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደ የስንብት መርሃ ግብር ላይ ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም “አቶ ዓለማየሁ ደርግን ለመጣል የነበረውን ትግል በወጣትነታእው ጀምሮ ተቀላቅለው በተለይ ለኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲና ፍትህ ማግኘት የታገሉ፤ እስከ ሕልፈታቸው ድረስም ታግለው የተሰዉ ታላቅ ሰው ናቸው። እነ አቶ ዓለማሁ ቢሰውም ያፈሯቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ትግሉን ያስቀጥላልይ፤ በመሰዋታቸው ለቁጭትና ለላቀ ትግል የሚያነሳሳን ነው” ሲሉ አወድሰዋቸዋል።
የኢሕአዴግ መንግስት ሕገመንግስቱን በጣሰ ሁኔታ ፓርላማው ሳይሰበሰብ የሶስት ቀን ብሔራዊ ሐዘንና ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ በመላው ሃገሪቱ ማወጁ አነጋጋሪ በሆነበት ሰዓት በሃይማኖት ተቋማት ውስጥም መዋቅር በመዘርጋት ቅዳሴ እስከማቋረጥ መድረሱ ብዙዎችን አስቆጥቷል። “በዚህ ታላቅ ጾም ወቅት ልጆቻችንን ለማቁረብ በፓትሪያሪኩ መቀመጫ በቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን ተገኝተን እያስቀደስን ባለንበት ወቅት ልጆቻችንን እንዳናቆርብ የአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ፍትሃትና ሽኝት አለብን በሚል ቅዳሴው 7 ሰዓት ላይ እንዲቋረጥ መደረጉ አስቆጥቶኛል” ሲል አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ምዕመን ለዘ-ሐበሻ ገልጿል።
alemayeu-atomsaበቅድስተ ማርያም ቤ/ክ የተገኙት ምእመናን “ባለስልጣኑ ሕይወታቸው በማለፉ እናዝናለን፤ እግዚአብሔር ገነትን ያውርሳቸው፤ ሆኖም ግን እኩለ ቀን ላይ ለሚደረግ ቀብር የእኛን መብት ጥሶ ቅዳሴውን ማቋረጥ አግባብ አይደለም” የሚል አቋም ያለቸው ምዕመናን “ይህ የሚያሳየው የመንግስትን በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ መግባትን ነው” ብለዋል።
“በባለስልጣኑ ፍትሃት እና ሽኝት ላይ ቤተክርስቲያን ሰው ወክላ መላክ ትችላለች፤ በዚህ ዓብይ ጾም ወቅት ልጆቻችንን ሳናቆርብ ቅዳሴ ማቋረጥ ግፍ ነው” ሲሉ ሌላው አስተያየት ሰጪ ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ተናግረዋል።
አቶ አለማየሁ አቶምሳ በታይላንድ ባንኮክ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ45 አመታቸው የካቲት 26 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት ነው ያረፉት። በምስራቅ ወለጋ ቢሎ ቦሼ ወረዳ ከአባታቸው አቶ አቶምሳ ሚጃ እና ከእናታቸው ወይዘሮ አየለች ብሩ በ1961 ዓ.ም መወለዳቸውን ከዚህ ቀደም መዘገባችን አይዘነጋም።

ግንቦት ሰባት “ወያኔ በኔ ስም እየሰጠ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሰቃየውን ባስቸኳይ ያቁም” አለ


ግንቦት 7 አቋሙን በሚገልጽበት ሳምንታዊ ርዕሰ አንቀጹ ወያኔ በኔ ስም ሰላማዊ ዜጎችን ማሰቃየቱን ባስቸኳይ ያቁም ሲል ጠየቀ። የግንቦት 7 ርዕሰ አንቀጽ እንደወረደ ይኸው፦
ባለፉት አራትና አምስት አመታት በግልጽ እንዳየነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነቱን፤ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር የሚያደርገዉ ትግል ጫና በፈጠረበት ቁጥር ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የራሱን ህገመንግስት የሚደፈጥጡ ህጎች አርቅቆ አያጸደቀ ሠላማዊ ዜጎችን አስሯል፤ ገድሏል ከአገር እንዲሰደዱም አድርጓል። ለምሳሌ በ2003 ዓም የኢትዮጵያ ፓርላማ ከቤተመንግሰት የተላለፈለትን ትዕዛዝ አክብሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነፃነት መከበር የሚታገለዉን የግንቦት 7 ንቅናቄ ሽብርተኛ አድርጎ ፈርጇል። ይህ ፈር የለቀቀ ፍረጃ ደግሞ ወያኔ የሱን ዘረኛ ስርዐት የሚቃወሙ ግለሰቦችን፤ ሀሳባቸዉን በነፃነት የሚገልጹ ዜጎችን፤ ጋዜጠኞችን፤ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና ከወያኔ ጋር አናብርም ያሉ ወጣት ኢትዮጵያዉያንን “ግንቦት ሰባቶች” ናችሁ እያለ በጅምላ እያሰረ እንዲያሰቃይ ህጋዊ ሽፋን ሰጥቶታል። ለምሳሌ ከፍትህና ከነጻነት ጥማት ዉጭ ከግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የሌለዉን የፖለቲካ ፓርቲ መሪዉን አንዱአለም አራጌን፤ ታዋቂዉን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና መምህርት ርኢዮት አለሙን የግንቦት 7 አባላት ናቸዉ የሚል ሰንካላና መሠረተ ቢስ ክስ መስርቶ ለረጂም ዘመን እስራት ዳርጓቸዋል።
ginbot 7
ወያኔ እንደ ዛሬዉ ከተማ ዉስጥ ሆኖ ሥልጣን ሳይቆጣጠር ገና ጫካ ዉስጥ እያለ ጥርሱን ከነከሰባቸዉና ከተቻለ አጠፋቸዋለሁ ካለዚያም አሽመደምዳቸዋለሁ ብሎ አስራ ሰባት አመት ሙሉ ከተዘጋጀላቸዉ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ የአማራ ብሄረሰብ ነዉ። በለስ ቀንቶት ሥልጣን ከጨበጠ ማግስት ጀምሮም በወሎና በጎንደር በኩል ከትግራይ ጋር የሚያዋሰኑ ሰፊ የሆነ ለም መሬቱን ጠቅልሎ በመውሰድ ዘረኛ ሥርዓቱን ዕድሜ ሊያራዝሙልኛል ይችላሉ ብሎ የሚተማመንባቸውን የቀድሞ የትግል አጋሮቹንና ካድሬዎቹን አስፍሮበታል:: ይህ በደልና ግፍ አልበቃ ብሎትም ቀደምቶቹ የኢትዮጵያ ገዥዎች ለፈጸሙት ግፍና የአስተዳደር በደሎች ሁሉ አማራዉን በጅምላ ተጠያቂ የሚያደርግ ፕሮፖጋንዳ እነሆ እስከዛሬ በመርጨት ለዘመናት በሠላም ከኖረው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በጠላትነት እንዲተያይ አድርጎታል:: በወያኔ አጋፋሪነት በበደኖ ፡በአርሲ በአረካና ሌሎች አካባቢዎች አማራው ላይ በግፍ የተፈጸመው ጭፍጨፋና ከ2004 እስከ 2005 ዓም አማራዉን ከጉራፈርዳና ከቤንሻንጉል ለማፈናቀል የተወሰደው እርምጃ የዚህ የወያኔ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ውጤት መሆኑን የምስት የለም::
ሟቹ መለስ ዜናዊና በህይወት የሚገኙ ቀንደኛ የወያኔ መሪዎች የተጠናወታቸው የአማራ ጥላቻ በጸረ ፋሽስት ዘመቻ ወቅት ባንዳ

Friday, March 7, 2014

ሰበር ዜና: የአዲስ አበባው ሲኖዶስ የአቡነ ጳውሎስ ሐውልት እንዲፈርስ ወሰነ


ሲኖዶሱ ቦሌ መድኃኔ ዓለም የቆመው የፓትርያርኩ ሐውልት እንዲፈርስ፣ በየቤተ ክርስቲያኑ የተሰቀለው የፓትርያርኩ ፎቶም እንዲወርድ ዛሬ ጠዋት ወሰኗል፡፡ እንዴት እዚህ ውሳኔ ላይ ሲኖዶሱ እንደደረሰ በዝርዝር የቀረበ ማብራሪያ ይፋ አልሆነም::
ይህ መልካም ጅምር ይመስላል:: መንግሥተ ሰማያቱ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ ብሎ የተናገረውን ሰው ዓይነት መሆኑ ነው መሰለኝ:: የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ቅዱስነቱ ቀርቶበት በጸጸት እንዲህ ደህናና የአምላክን መስመር ለመያዝ መፈለጉ ጥሩ ጅምር ነው ካዘለቀው:: የአዲስ አበባው ሲኖዶስ የፖለቲካ መሣሪያነቱን ቀነስ አርጎ የእግዚአብሄርን ቃል መከተሉ እሰየው የሚያስኝ ነው::
የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ወደ ልቡ እየተመለሰ ይሆን? የወደፊቱን ደግሞ እንናያለን::
ምንጭ፣ http://www.ethiofreedom.com

አንድነት በ17 ከተሞች ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊያደርግ ነው

 
bahr dar 19
አንድነት ፓርቲ ሁለተኛውን ዙር የሚሊኖች ድምፅለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ይፋ ማድረጉን አስታወቀ። ህዝባዊ ንቅናቄው የሚካሄድባቸው 17 ከተሞችም ተለይተው ታውቀዋል።
የድርጅቱ ልሳን ይፋ እንዳደረገው አንድነት ለዲሞክራሰና ለፍትህ ፓርቲ ዛሬ ይፋ ያደረገው የህዝባዊ ንቅናቄ መርሃግብር በተከታታይ ሊካሂዳቸው ካቀዳቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች መካከል አንዱ በየሆነውን የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት(Millions of voices for land ownership) የሚል ስያሜ የሰጠውን የህዝባዊ ንቅናቄ ነው፡፡ መረሃ ግብር በዛሬው እለት ይፋ የተደረገው ቀበና መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፊተ ለፊት በሚገኘው የፓርቲው ጽ/ቤት ነው፡፡ ህዝባዊ ንቅናቄው ይፋ በተደረገበት መግለጫ ላይ አንድነት የመሬትን ጉዳይ በአጀንዳነት በመምረጥ ህዝባዊ ንቅናቄ ለማድረግ የመረጠባቸው ምክንያቶች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡
በአዲስ አበባ በሚደረግ ትዕይንተ ህዝብ እንደሚጀመር የሚጠበቀው “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባቤትነት” ህዝባዊ ንቅናቅ 14 ከተሞች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግና ሶስት ከተሞችም በተጓዳኝ ለህዝባዊ ንቅናቄው መመረጣቸው ታውቋል፡፡ ንቅናቄው የሚካሄድባቸው ከተሞች አዲስ አበባ ፣ደሴ ፣ሐዋሳ ፣አዳማ/ናዝሬት ፣መቀሌ ፣ደብረታቦር ፣ ደብረ ማርቆስ ፣ድሬ ደዋ፣ ጅንካ፣ ቁጫ፣ አሶሳ፣ነቀምት፣ለገጣፎ፣አዲስ አበባ ሲሆኑ ተጓዳኝ ከተሞቹ ወልዲያ፣ ጋምቤላ፣ ም/አርማጨሆ(አብርሃ ጅራ) እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አንድነት ፓርቲ ባለፈው ዓመት(2005ዓ.ም) ለሶስት ወራት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
ምንጭ፣ zehabesha.comhttp://www.zehabesha.com/amharic/archives/13427

Thursday, March 6, 2014

በመንግስት ታጣቂው በጥይት ተደብድበው የተገደሉት ባልና ሚስት ፎቶ ተገኘ


 

 

Be Hiwehat tataki
እብሪተኛ የመንግስት ታጣቂዎች ለሚቀጥፉት የሰው ህይወት መንግስት ተጠያቂ የሚሆነው መቼ ነው?ከዳዊት ሰለሞን
የመንግስት ታጣቂዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ደማቸው በትንሽ በትልቁ እየፈላ ሲቪል ዜጎችን የሚጨርሱበት አጋጣሚ ከቀን ቀን እየጨመረ ነው፡፡
የባህር ዳሩን ዘግናኝ እልቂት ለጥቆ ቂርቆስ ቤ/ክ አካባቢ ሁለት ሰዎችን በጥይት በመምታት የወሲብ ደምበኛው እንደነበረች የተነገረላትን ሴት ሲገድል አብሯት የነበረውን ማቁሰሉ አይዘነጋም፡፡የታክሲ ሹፌሩ አልጭንህም ስላለው የታጠቀውን ሽጉጥ በመምዘዝ ለፍቶ አዳሪውን በአጭር አስቀርቶታል፣አራት ኪሎ ቤተ መንግስት አቅራቢያ በሚሄድ መኪና የተርከፈከፈ ጥይት ስንቱን እንዳስቀረ እግዜር ይወቀው ፡፡በየአካባቢው እንዲህ አይነት ዘግናኝ ዜናዎችን መስማት አዲስ አይደለም፡፡
ከትናንት በስቲያ በላፍቶ ክፍለ ከተማ አቦ ማዞሪያ አካባቢ በምስሉ የምትመለከቷቸውን የሶስት ልጆች ወላጆች እብሪተኛው ታጣቂ በጥይት በመደብደብ ገድሏቸዋል፡፡ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡እሰየው ነው ፡፡ግን በቃ?እነዚያን ሶስት ህጻናት ማን ነው የሚያሳድጋቸው?ግለሰቡን አምኖ ክላሽ ያስታጠቀው አካል የማይጠየቀውስ እስከመቼ ነው?
መንግስት የመኪና አሽከርካሪዎች የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ እንዲገቡ እያስገደደ መሆኑ በመኪኖቹ አደጋ ለሚደርስበት ሰው አንዳች ነገር ነውና ይበረታታል፡፡መንግስት በነካ እጁ የሚያስታጥቃቸው ሰዎች ለሚያደርሱት የመብት ጥሰት ኢንሹራንስ ይግባ!!!በእኔ እምነት ስለ ተገደሉት ወላጆችና ወላጅ አልባ ስለሆኑት ልጆች መጮህ የሁላችንም ግዴታ ነው።
ምንጭ፣ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13399

(ሰበር ዜና) መርዝ ተሰጥቷቸዋል የተባሉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ አረፉ


 
alemayehu and meles
(ዘ-ሐበሻ) መርዝ ተሰጥቷቸው ነው ለዚህ የበቁት የተባሉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ለህክምና ብዙ ገንዘብ ወጣባቸው በሚል ሕገወጥ በሆነ መንገድ ከስልጣናቸው እርሳቸው ባላወቁበት በፈቃዳቸው እንደለቀቁ ተደርጎ የተነገረባቸው የኦሮሚያው ክልል ፕረዚዳንት ኦቦ አለማየሁ አቶምሳ በተሰጣቸው የተመረዘ ምግብ ምክንያት የጀመራቸው በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ ጸንቶ በተደጋጋሚ በተለያዩ ሃገራት ህክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ዛሬ ግን በባንኮክ ታይላድ ለህክምና በሄዱበት ሆስፒታል ሕይወታቸው አልፏል።
በ45 ዓመታቸው በታይላንድ ባንኮክ ሕይወታቸው ያለፈው ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ በምን ምክንያት የተመረዘ ምግብ እንደተሰጣቸው ባይታወቅም ከርሳቸው ጋር ምግቡን በልቶ የነበረ ግለሰብም እስካሁን በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኝ ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች ያመለክታሉ። ለዘ-ሐበሻ ቅርብ የሆኑ የኦነግ የመረጃ ምንጮች “ኦህዴድን የድሮው ኦህዴድ እንዳይሆን ሊያደርጉ የሚችሉ ሰው ስላልነበሩ በሕወሓቶች መርዝ እንዲሰጣቸው ተደርጓል” የሚል አመለካከት ያላቸው መሆኑን ገልጸው ሕወሓት አቶ

Wednesday, March 5, 2014

የአፍሪካ መሪዎች ለምን ቶሎ ይሞታሉ? – በ6 ዓመት ውስጥ 10 የአፍሪካ መሪዎች ሞተዋል


 
meles zenawi
ቢቢሲ እንደጻፈው – አድማስ ሬዲዮ እንዳቀናበረው።
አንድ የአገር መሪ ፣ ገና በሥልጣን ላይ እያለ መሞቱ የተለመደ አይደለም። ነገር ግን ካለፈው 2008 ዓ.ም ወዲህ በዓለም ላይ 13 የአገር መሪዎች ገና ቢሯቸው እያሉ ሲሞቱ፣ ከዚያ ውስጥ 10 ያህሉ የአፍሪካ መሪዎች ናቸው። አፍሪካ ውስጥ መሪዎች ለምን ሥልጣን ላይ እያሉ ይሞታሉ?
በ 2012 ዓ.ም ብቻ አራት የአፍሪካ መሪዎች ቢሯቸው ውስጥ እያሉ ህይወታቸው አልፏል (የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የጋናው ፕሬዚዳንት፣ የማላዊ ፕሬዚዳንት፣ የጊኒ ቢሳዎ ፕሬዚዳንት) ። የመሪዎቹ ሞት ለጋዜጠኞች ደግሞ አዲስ የምርምር መንገድ ከፍቷል፣ – የአፍሪካ መሪዎች ለምን ቢሯቸው እንዳሉ ይሞታሉ?
“ሌሊት ስልክ ከተደወለልኝ፣ በቃ አንድ የአፍሪካ መሪ ሞቷል ማለት ነው ብዬ ማሰብ ጀምሬያለሁ” የሚለው የደቡብ አፍሪካው ዴይሊ ማቭሪክ ዜና አውታር ጋዜጠኛ ሲሞን ኤሊሰን ነው። እናም ይህን ጥያቄ ይዞ የትኛው መሪ በስንት ዓመቱ፣ በምን ምክንያት ሞተ? የሚለውን ምርምር ማድረጉን ቀጠለ።
ከ 2008 ወዲህ ብቻ 10 የአፍሪካ መሪዎች ሥልጣን ላይ እንዳሉ ህይወታቸው አልፏል። እነሱም ….
1- የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ፣ ዕድሜ 57 የሞት ምክንያት ድንገተኛ ኢንፌክሽን፣ የሞቱበት ወር ኦገስት 2012
2- የጋናው ፕሬዚዳንት ጆን አታ ሚልስ ፣ ዕድሜ 68፣ የሞት ምክንያት የጉሮሮ ካንሰር፣ የሞቱበት ወር ጁላይ 2012
3- የማላዊው ፕሬዚዳንት ቢንጉ ዋ ሙታሪካ ፣ ዕድሜ 78፣ የሞት ምክንያት ካርዲያክ አሬስት፣ የሞቱበት ወር ኤፕሪል 2012
4- የጊኒ ቢሳዎ ፕሬዚዳንት ኤም ቢ ሳኒሃ ፣ ዕድሜ 64፣ የሞት ምክንያት የቆየ በሽታ፣ ለረዥም ጊዜ ታመው ቆይተው። የሞቱበት

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ሊዘጋ ነው፤ ዘንድሮ አንድም ተማሪ አልተመዘገበም


ዘሪሁን ሙሉጌታ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው፦
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎችን በማጣቱ የትምህርት ክፍሉ አደጋ ላይ መውደቁን እያሳዘናቸው መሆኑን የታሪክ መምህራንና ተመራማሪዎች ገለፁ። ሀገሪቱ ጥንታዊና መካከለኛ ታሪኮች ባለቤት ብትሆንም በአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የታሪክ የትምህርት ክፍል ሊዘጋ መቃረቡ እያነጋገረ ነው።
addis ababa un
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል የሚያስተምሩ መምህራንና የታሪክ ተመራማሪዎች “ታሪክ ዳቦ አይሆንም” በሚል የተሳሳተ አመለካከትና የ70/30 የትምህርት ፖሊሲ የፈጠረው ችግር መሆኑን በመግለፅ አሰራሩን አምርረው ተችተዋል። ከታሪክ በላይ ዳቦ የሚሆን የለም። ታሪክ የአንድ ሀገር የማንነትና የእውቀት መሠረት መሆኑ እየታወቀ የትምህርት ክፍሉ በተማሪ እጦት በአደጋ ላይ መገኘቱ እንደሚያስቆጣቸው መምህራኑና የታሪክ ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።
ሰሞኑን ዩኒቨርሲቲው የታሪክ ትምህርት የተከፈተበትን 50ኛ ዓመት ባከበረበት ወቅት በ2006 ዓ.ም አንድም የታሪክ ተማሪ ያልተመዘገበበት መሆኑ አሳፋሪም አሸማቃቂም መሆኑን የጠቀሱት ባለሙያዎቹ ችግሩን ለማስተካከል ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ፕሬዝዳንት ዶ/ር በለጠ ብዙነህ ስለጉዳዩ ተጠይቀው የታሪክ ትምህርት ክፍሉ እየተዳከመ መምጣቱን አምነዋል። ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው ምክንያት በታሪክ ትምህርት የሚመረቁ ተማሪዎች በመስኩ ስራ

Tuesday, March 4, 2014

የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ቅሬታቸው ገለፁ (ከአብርሃ ደስታ)


ባሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል የዉኃና አፈር ጥበቃ (Water and Soil Conservation, ማይን ሓመድን ዕቀባ) ተግባራት የሚከናወኑበት ግዜ ነው። ህዝብ ስራው ትቶ ተገዶ በፕሮግራሙ ይሳተፋል። ለፖለቲካ ሲባል ህዝብ በፍላጎቱ ተሳተፈ ተብሎ ሪፖርት ይቀርባል። እውነታው ግን ሌላ ነው። በየዓመቱ ህዝብ ሳያምንበት ተገዶ ይሰራል። በግዜው ያልሰራ እስከ ሦስት መቶ (300) ብር ተቀጥቶ ይሰራል። በዚሁ ምክንያት ብዙ ሌሎች የግል ሥራዎች ይቆማሉ። ዜጎች ብዙ ኪሳራ ይደርስባቸዋል።
አብርሃ ደስታ
የዉኃና አፈር ጥበቃ ሥራ የጉልበት ስራ ነው። መስራት የሚችል ይሰራል፣ ወይ እንዲሰራ ይገደዳል። በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ጣብያ ሩባ ፈለግ ግን ለየት ያለ ጉዳይ ተከስቷል። የዓፅቢ ወንበርታ ህዝብ በህወሓት የትጥቅ ትግል ወቅት ንቁ ተሳታፊ የመኖሩ ያህል ባከባቢው ብዙ አካል ጉዳተኞች (የቀድሞ ታጋዮች) አሉ። በጉልበት ስራ መሰማራት አይችሉም። ምክንያቱም አካላቸው ጎድሏል። እናም በጡረታ ገንዘብ በገጠር ህይወት ነው የሚኖሩ። የአካል ጉዳተኞች መሆናቸው ታውቆ ላለፉት ሃያ ሦስት (23) ዓመታት በዉሃና አፈር ጥበቃ ሥራ ተሳትፈው አያውቁም። ምክንያቱም አካላዊ ቁመናቸው አይፈቅድላቸውም፤ ግማሾቹ ዓይናቸው የጠፋ ግማሾቹ እግራቸው የተቆረጠ ወዘተ ናቸው።
አሁን ግን ለመጀመርያ ግዜ በተለየ ሁኔታ አካላቸው የጎደሉ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች በዉኃና አፈር ጥበቃ ፕሮግራሙ እንዲሳተፉ በመንግስት አካላት እየተገደዱ ይገኛሉ። ለምን አሁን እነሱን ማስገደድ ተጀመረ? የአፅቢ ወንበርታ ህዝብ በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት በመንግስት አካላት ላይ ተቃውሞ አስነስቶ ነበረ። ህወሓቶች የቀድሞ ታጋዮቹ ዒላማ አድርገው በዉኃና አፈር ጥበቃ እንዲሳተፉ ያስገደዱበት ምክንያትም ህዝብ ፀረመንግስት ሲነሳ የቀድሞ ታጋዮቹ ከመንግስት ጎን ከመሰለፍ ይልቅ የህዝቡን ጥያቄ በመደገፋቸው ነው። ታጋዮቹ ዓፈና በዝቷል፤ ለዚህ አይደለም መስዋእት የከፈልነው፣ ፍትሕ ጠፍቷል ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች በማንሳታቸው ነው።
አሁን የድሮ ታጋዮቹ በግዝያቸው በፕሮግራሙ ባለመሳተፋቸው የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸው ለብቻቸው እንዲሳተፉ ይደረጋል። የገንዘብ ቅጣቱ እስከ ሦስት መቶ ብር ይደርሳል። ሦስት መቶ ብር ደግሞ መክፈል አይችሉም፤ ግድቡም መገደብ አይችሉም። ምክንያቱም ታጋዮቹ የሚተዳደሩት በጥሮታ ገንዘብ ነው። የጥሮታ ገንዘቡ ደግሞ ከሦስት መቶ ብር በላይ አይደለም። ታድያ ሦስት

የሰማያዊ አመራር አባላት በሶስት መስመር ወደ ተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ተጓዙ

ዛሬ ጠዋት ልክ12 ሰዓት ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን የያዘ ሶስት ልኡካን ቡድን ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጉዞ ጀምሯል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል በመላው የሀገሪቷ ክፍል ለማንቀሳቀስና ለማጎልበት ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች የሚመራ የልዑካን ቡድን በሶስት አቅጣጫዎች ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ጉዞ ጀምሯል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በመስክ ጉብኝቱ ወቅት የፓረቲውን መዋቅር የስራ እንቅሰቃሴ መገምገምና ለማጠናከር እንዲሁም መዋቅሩ ያለበትን ችግር ገምግሞ መፍትሄ መስጠትም አንዱ ሌላው የጉዞ አላማው ነው፡፡
የመስክ ጉበኝቱ በአጠቃላይ በ14 ዞኖችን የሚያካትት ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ ወረዳዎች ላይ ያሉ የሰማያዊን የፓርቲ እንቅስቃሴ ከሚመሩ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ይደረጋል፡፡
ጉዞ መስመር አንድ ፡- ደ/ብርሀን ፤ ሸዋሮቢት ፤ ደሴ ፤ ወልዲያ
1. አቶ ስለሺ ፈይሳ – ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ዮናታን ተሰፋዬ – የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ
3. አቶ ሔኖክ መለሰ – በአደረጃጀት ጉዳይ የጥናትና የትግል ስልት ስልጠና ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ጉዞ መስመር ሁለት – ደብረማርቆስ ፤ ባህርዳር ፤ ወረታ ፤ ጎንደር
1. አቶ በቃሉ አዳነ – አደረጃጀት ጉዳይ ም/ኃላፊ
2. አቶ ይድነቃቸው ከበደ – የህግ ጉዳይ ኃላፊ
3. ወ/ሮ ሃና ዋለልኝ የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ
ጉዞ መስመር ሶስት – ሆሳዕና ፤ ሶዶ ፤ አርባ ምንጭ ፤ ባድዋቾ ፤ አዋሳ
1. አቶ ጌታነህ ባልቻ – የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
2. አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. አቶ ይሁን ዓለሙ – የአደረጃጀት ጉዳይ የክትትልና ግምገማ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ምንጭ፣ http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/13443

Sunday, March 2, 2014

Al Jazeera Q&A: Ethiopian journalists languish in prison


Government in Addis Ababa refuses to release award-winning journalists jailed under Anti-Terrorism Proclamation.
As Al Jazeera presses ahead with its campaign to free its journalists detained in Egypt, nine Ethiopian journalists who are receiving less attention continue to languish in prison, held on trumped-up charges of terrorism, according to the New York-based Committee to Protect Journalists (CPJ).
Eskinder Nega (L) is serving an 18-year jail term under the 2009 Anti-Terrorism Proclamation [MLDI/Al Jazeera]
Eskinder Nega (L) is serving an 18-year jail term under the 2009 Anti-Terrorism Proclamation [MLDI/Al Jazeera]

To mark the 900th day of the imprisonment of award-winning journalist Eskinder Nega, who is serving an 18-year jail term, and the 36th birthday of Woubshet Taye, jailed for 14 years, Al Jazeera speaks to Nani Jansen of the Media Legal Defence Initiative, a London-based NGO that helps journalists around the world defend their rights.
Al Jazeera: What are the charges Woubshet Taye and Eskinder Nega are facing?
Nani Jansen: Eskinder Nega, Woubshet Taye and many other journalists in Ethiopia, such as Reeyot Alemu, have been charged and convicted under Ethiopia’s 2009 Anti-Terrorism Proclamation, a deeply flawed law that is being used by the Ethiopian government to systematically suppress free

ከአውሮፕላኑ ጠለፋ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ም/ሥራ አስኪያጅ ካፒቴን ደስታ ዘሩ ለቀቁ


 

 

Desta Zeru Ethiopian captain
በአንድ ጎሳ እና ቋንቋ አመራር ስር ወድቋል በሚልና በዘረኝነት ሰራተኞቹን ፍዳቸውን እያሳየ ነው በሚል የሚተቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የበረራ ክፍል ሃላፊ የሆኑት ካፒቴን ደስታ ዘሩ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤት ምንጮቹን ጠቅሶ ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አስታወቀ። እንደ ሽግግር ምክርቤቱ ዘገባ የስልጣን መልቀቂያው ጉዳይ ግልጽ ምን እንደሆነ አይታወቅም።
ሌሎች ምንጮች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጠልፎ ወደ ስዊዘርላንድ በረዳት ካፒቴን ሃይለመድህን አበራ ካረፈ በኋላ በአየር መንገዱ ውስጥ በተነሳው አለመግባባት ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየቶችን እየሰጡ ይገኛሉ።
ምንጮቹ የአየር መንገዱ አብራሪዎች በቂ እውቀት እና ችሎታ እያላቸው ከውጪ አብራሪዎችን በማስመጣት ለኢትዮጵያውያኑ እድገት እና የበረራ ፍቃድ መከልከል እንዲሁም አላስፈላጊ የሆነ መንግስታዊ የደህንነት ወከባ እና የአይነ ቁራኛ ጥበቃ በአብራሪዎች ላይ ከመደረጉም በላይ የስራ መብቶቻቸው እና የሰብአዊ መብቶቻቸው በዘረኝነት ላይ የተመረኮዘው የአየር መንገዱ ማንጅመንት እንደማያከብርላቸው እነዚሁ ምንጮቹ አክለው የሚገልጹ ሲሆን፤ በወያኔ ፈጠራ ረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራን “የአእምሮ በሽተኛ ነው” በሚል የተወራው ወሬም በአየር መንገዱ የሚበሩ ሰዎች ቁጥር እንዲቀንስ ምክንያት እየሆነው እንደሆነም ምንጮች ይናገራሉ።
ምንጭ፣ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13253

Saturday, March 1, 2014

The Battle of Adwa Changed Ethiopia and the World

February 28, 2014
Abebe Hailu, Special to The Washington Informer
Ethiopia, Yesterday and Today
Ethiopia has a significant history reaching over 3,000 years into the past. The word “Ethiopia” has become a term for the idea of African solidarity and freedom, not just the name of a nation or a region. The ancient Greek historian Herodotus noted the region of Ethiopia as home to “people with burnt faces.” During the Greek and Roman eras, everything south of the Sahara Desert in Africa was generally referred to as Ethiopia or Abysinnia.
"The Battle of Adwa" (Courtesy of A. Davey via Wikipedia)
“The Battle of Adwa” (Courtesy of A. Davey via Wikipedia)
Biblical references also label Ethiopia as Cush, Kesh, Ekosh and Shewa (Sheba) in the Hebrew language. These were the names used in Solomon’s courts when he received a visit from the Ethiopian Queen of Sheba. The biblical “Song of Solomon” praises her physical beauty. In modern times, especially since the battle of Adwa, Ethiopia has been seen as a de facto model of freedom for

በኢንቨስትመንት ስም አፍሪካ ውስጥ የሚደረገውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ የካናዳ የፓርላማ አባላትና እውቅ ምሁራንን ያሳተፈ ውይይት በኦታዋ ተደረገ


Coalition for Equitable Land Acquisitions and Development in Africa በምህጻረ ቃል CELADA በመባል የሚታወቀው በካናዳ ኦታዋ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅት በአፍሪካ እየተኪያሄደ ያለውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ በርካታ የፓርላማ አባላት፣ የተራድኦ ድርጅት ሃላፊዎች የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተገኙበት በአፍሪካ በኢንቨስትመንት ስም የሚደረገውን የመሬት ቅርምትና ካናዳ ልትይዘው የሚገባትን ፖሊሲ በተመለከተ በኦታዋ ፌብሩዋሪ 25 ቀን 2014 ዓም የተሳካ ስብሰባ አድርገዋል።
በሚሊየን የሚቆጠሩ በእርሻ የሚተዳደሩ ማህበረሰቦችን አግባብ በሌለው ሁኔታ የማፈናቀሉ ሥራ እጅጉን ተጧጡፎ ያለው በተለይ በአፍሪካ በመሆኑ CELADA የተሰኘው ድርጅት ይህ ጉዳይ አለም አቀፍ ትኩረት ያገኝ ዘንድ የበኩሉን ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት በተለያየ ተቋማት ውስጥ የሚያገለግሉ ካናዳውያን እንዲሁም ከበርካታ አፍሪካ ሀገራት የመጡና በአህጉሪቱ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ይመለከተናል የሚሉ ትውልደ አፍሪካ ምሁራንን ጭምር ያካተተ ነው። በዚህ ድርጅት ውስጥ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምሁራንም የሚሳተፉበት ሲሆን ከመስራች አባላት አንዱ ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ናቸው።
New Picture (7)
የስብሰባው ዓላማ ድርጅቱን ከፓርላማ አባላትና በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉና አለም አቀፍ እውቅና ካላቸው ካናዳውያን ጋር ማስተዋወቅ ሲሆን። በዋነኛነትም ይህ ህገወጥ የመሬት ነጠቃና ቅርምት በሚደረግባቸው አገሮች ውስጥ የካናዳ ግብር ከፋይ ሕዝብ ገንዘብ ተጨማሪ የመጨቆኛ መሳርያ በመሆን ለአምባገነን መንግስታት እንዳይውል ለሚደረገው እንቅስቃሴ