Wednesday, February 5, 2014

አማራውን በተሳደቡት አቶ አለምነው መኮንን ላይ በባህር ዳር ሰልፍ ሊደረግ ነው፤ በአድዋና አዲስ አበባ የአድዋ ድል በዓል ዝግጅቶች ይኖራሉ

– አማኑኤል ዘሰላም
የአንድነት ፓርቲ፣ በሶስት ከተሞች ታላላቅ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች፣ ለማድረግ መወሰኑን ከሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነት ፌስቡ ገጽ አነበብኩ። እንቅስቃሴዎቹ የሚደረጉባቸው ከተሞች፣ አድዋ፣ አዲስ አበባ እና ባህር ዳር ናቸው። በአድዋ እና በአዲስ አበባ ከሌሎች ደርጅቶ ጋር በጋራ በመሆን (መኢአድ፣ አረና፣ ትብርር፣ መድረክ..) ፣ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ሕዝቡ ሁሉ ኩራት የሆነውን የአድዋ ድል በማሰብ ትልቅ አከባባር ለማድረግ ነው የታቀደው። በአድዋና በአዲስ አበባ ባሉ ብዙ ህዝብ ሊይዙ በሚችሉ አደባባዮች አከባበሩ ሊደረግ እንደሚችል ግምት ቢኖርም ፣ የአንድነት ፓርቲ የአከባበሩ ይዘት፣ ሰዓትና ቦታን ገና ይፋ አላደረገም።
alemenew mekonn
በባህር ዳር የሚደረገዉ ግን ከአድዋና ከአዲስ አበባዉ የተለየ ነዉ የሚሆነው። በቅርቡ የአማራ ክልል ም/ ፕሬዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው፣ በክልሉ የሚኖረው ሕዝብ ላይ የሰነዘሩት ጸያፍና ከአንድ መሪ የማይጠበቅ አባባሎችን በመቃወም የሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ነዉ። ጉዳዩ አንድ ሰው የተናገሩት ቢሆንም፣ ኢሕአዴግ እንደዚህ አይነት ሕዝብን የናቀና ያዋረደ አስተያየት የሰጡ ባለስልጣን ከሃላፊነታቸው ወዲያዉኑ እንዲነሱ አለማድረጉ፣ በሕግም አለመጠየቁ፣ ችግሩ ከግለሰብ አልፎ ድርጅታዊ መሆኑንም የሚያመላክትበትም ሁኔታም አለ።
«የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል»፣ «አማራዉ በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው»፣ «የአማራዉ ሕዝብ የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት» …. የመሳሰሉ አስተያየቶችን ነበር ባለስልጣኑ የሰነዘሩት።
ሰልፍ መጥራት በራሱ ለዉጥ አያመጣም። በባህር ዳር፣ አድዋ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ የሚደረጉ ሰልፎችና ዝግጅቶች በማይሻማ መልኩ ፖለቲካዉን እንዲያናጉት፣ የማያሻማና የሚያስተጋባ መልእክት እንዲያስተላለፉ ከተፈለገ፣ ሕዝብ በነቂስ መዉጣት አለበት። ለዚህም ትልቅ ድርጅታዊና የቅስቀሳ ሥራ መስራቱ የግድ ነዉ። በየወረዳው፣ በየመንደሩ ፣ ቅስቀሳዎች መደረግ አለባችው። በራሪ ወረቀቶች፣ ፓምፍሌቶች በስፋት መዘጋጀትና መበተን ይኖርባቸዋል።
አንድ ነገር አንርሳ። እኛ ኢትዮጵያዉያን ካልደገፍናቸው፣ ከጎናቸው ካልቆምን ፓርቲዎቹ ብቻቸውን በራሳቸው ምንም ሊያመጡ አይችሉም። ገዢው ፓርቲ የሚተማመነው በያዘው ጠመንጃ፣ ባሰማራቸው ሰላዮቹና ካድሬዎችቹ ነዉ። አንድነቶች ግን የሚተማመኑት በሕዝብ ጉልበት ብቻ ነው። እያንዳንዳችን የድርሻችንን ከተወጣን፣ በአዲስ አበባ፣ በአድዋና ባህር ዳር የምንኖር የሚደረጉ ሰልፎችን እና ዝግጅቶችን ከተቀላቀልን፣ ነጋሪና ቀሳቅሽ ሳንፈልግ፣ በኛዉ አነሳሽነት ቅስቀሳ ካደረግን፣ ተዓምር የማንሰራበት ምንም ምክንያት የለም።
በሰልፉ ለመገኘት የማንችል ደግሞ፣ በተለይም በዉጭ አገር ያለን፣ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ከማሳወቁ በተጨማሪ፣ በገንዘባችን ትልቅ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል።
ምንጭ፣ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/12551

No comments:

Post a Comment