Wednesday, December 18, 2013

የኢትዮጲያ ሰላም በአንድነታችን ላይ ነው


 
The shadow of a supporter of Ethiopia's Unity for Democracy and Justice party (UDJ) is seen through an Ethiopian flag during a demonstration in the capital Addis Ababa
               የሚያኮራ የሚያስደስት ኢትዮጲያዊ አንድነት ሰሞኑን በተደረጉት የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ አይተናል:: በሳውዲ አረቢያ እየተሰቃዩ ላሉት እህትና ወንድምቻችን ሀይማኖትና ዘርን ሳንለይ ያሳየነው የአንድነትና የቁጣ መንፈስ በጣም የሚያስደስት ነው:: ይሄ ያሳየነው አንድነት እና ቆራጥነት መቀጠል ሊኖርበት ይገባል:: ካልሆነ ግን የችግራችንን ሥር መንቀል አስችጋሪ ነው:: ሳውዲ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጲያዊያን ሲገደሉ፣ሲደበደቡ እና ሲደፈሩ በኢትዮጲያዊነታችው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል:: ይሄ አይነቱ ኢሰብሐዊ ጥቃቶች በሰፊው እየደረሰ ያለ ሲሆን አንድነታችንን አጠናክረን ወደ ፊት ካልተጓዝን በተለያየ ቦታና ሀገር ኢትዮጲያዊነት ሊደፈር ይችላል::
       በመጀመሪያ መግለፅ የምፈልገው የኢትዮጲያን ክብር እና ማንነት ያጠፋው ወያኔና አመራሩ ናችው:: ስለዚህ ሁል ጊዜ ለሚፈጠሩት ችግሮች ሆይ ብለን መነሳት ብቻ በቂ መፍቴ አይሆንም ዋናው የችግሩን መንሴ ወያኔን ማስወገድ ነው:: ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እህትና ወንድሞቻችን ተሰደዋል፣ተገድለዋል፣ተደፍረዋል ይሄ አዲስ ነገር አይደለም ሁላችንም ቢሆን እየሰማን እያየን የቆየነው ነገር ነው:: በአሁኑ ሰሀት በሳውዲ አረቢያ እየተደረገ ያለው ግፍ በዛ እንጂ በፊትም የነበረ ነው::የወያኔ አገዛዝ በሀገር ፍቅር ወይም በአንድነት ላይ የተመሰረተ አይደለም:: ይሄን በደንብ አድርጎ ለብዙ  አመታት አሳይቶናል:: የእናትና የአባቶቻችንን መሬት ለበአድ ሀገር ተወላጆች በመሸጥ፣መሀበረሰቡን በዘር እና በሀይማኖት በመከፋፈል፣እህትና ወንድሞቻችንን ለበአድ ሀገር አሳልፎ በመስጠት እና በመሳሰሉት ማየት ይቻላል::
 የአንድነታችን  መላላት መንሴወች እና መፍቴያችው ያልኩዋችውን ላብራራ
         አንደኛው እንደ ሰው እናም እንደ ኢትዮጲያዊ ለሚደርሱብን ኢሰብሀዊ ድርጊቶች አይሆንም፣አይደረግም የሚል ቆራጥ መንፈስ በውስጣችን መመንመኑ :: ይሄ ወደ ምን ያመራል ብንል ለገንዘብ እና ላአንዳንድ ጥቅማ  ጥቅሞች አገርን አሳልፎ ወደ መሸጥ:: ሰው እንደመሆናችን መጠን ቆም ብለን ልናስብ ይገባል  የወያኔ መንግስት የህዝብ  ጥርቅም መሆኑን:: ህዝብ ደግሞ የእያንዳንዱ ሰው ስብስብ ነው :: ስለዚህ እንደ ሰው ወያኔ ለሚያደርስብን ጥቃቶች አይሆንም ካልን ወያኔ የሚቀጥልበት ምንም ምክንያት አይኖርም:: ህዝብ የመረጠው መንግስት ደግሞ ለህዝቡ አንድነት የቆመ ነው::
   ሁለተኛው የወያኔ የአገዛዝ ስልት ነው:: በህዝብ ያልተመረጠ መንግስት(ወያኔ) ስልጣን ላይ ለመቆየት የተለያዩ  ጫናዊ የአገዛዝ ስልቶችን ይጠቀማል:: ከሁሉም የሚከፋው ዘርን ከዘር  እና ሀይምኖትን ከሀይማኖት  በማጣላት የህዝቡን አንድነት የሚበታትኑት ነው:: ለዚህም ምስክሩ ኢትዮጲያን ለቀው የሚሰደዱ ሰዎች የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ችግር ያላችው ብቻ አይደሉም ጥሩ
የትምህርት ደረጃ እና ክፍያ ያላችውም ናችው::ይህ የሚያሳየው የደንነት እና የአንድነት ስሜታ በመሀበረሰቡ መመንመኑን ነው::መፍቴው ህዝብ የመረጠውን መንግስት ለማምጣት የበኩላችንን  አስተዋፆ ማድረግ:: ለምናደርጋችው ማንኛውም እንቅስቃሴወች ከማስተዋል ጋር ሊሆን ይገባዋል:: ሌላው እንደ አሜሪካ ካሉ ያደጉት ሀገራት በዘርም በቀለምም በሀይማኖት የማይገናኙ ህዝቦች እንዴት ለአንድ አላማ እንደቆሙ ትምህርት ከነርሱ በመውሰድ::
ሦስተኛው የኛ የሆኑ ችግሮችን ሌላ ሀገሮች መተው ችግራችንን ይፈቱልናል ብሎ መጠበቅ:: ይሄ እምነታችን ያመጣብን የራሱ የሆኑ ችግሮች አሉት፥ ከችግሮቹም አንዱ ያሀገራችንን ታሪክና ሚስጥራት አሳልፈን መስጥት:: ይሄ ደግሞ የተለያዩ የምእራብአዊ ሀገሮች በኢትዮጲያ ፖለቲካ እንደፈለጉት እጃችውን እንዲያስገቡና እንዲያሶጡ መንገድ ከፍቶላችዋል:: ይሄም ለአንድነታችን መላላት ትልቅ አስተዋጾ አለው::ለምሳሌ የጫካ ውስጥ ጎሾችን ብንወስድ በተናጠል ሳር በሚግጡበት ጊዜ በቀላሉ አውሬ ያጠቃችዋል ግን ሶስትም አራትም ሆነው ሲግጡ እራሳችውን በሁሉም አቅጣጫ ከአውሬ መከላከል ይችላሉ:: ስለዚህ መፍቴው ምንልያይበትን ነገር ከማየት አንድ የሚያደርገንን ነገር በማየት ችግራችን እርስ በእራስ በመወያየት መፍታት ነው::
አራተኛው ከታሪክ አለመማራችን ነው:: ኢትዮጲያ ባለ ብዙ ታሪክ ሀገር ስትሆን  የሚያስደስት ታሪክ እንዳላት ሁሉ የሚያስከፋም ታሪክ አላት:: ታሪካችንን በአግባቡ መርምረን አጥንተን ምንጓዝ ብንሆን ኖሮ አንዳይነት ችግሮች በተደጋጋሚ ባልመጡብን ነበር::መፍቴው የሰው አገርን ታሪክ ቀድሞ ከማወቅ ይልቅ የሀገራችንን ታሪክ አምብበን ተረድተን ተገንዝበን ለችግራችን ቀድመን መፍቴ ፈልገን መገኘት ይኖርብናል::
በኔ እምነት ከላይ የጠቀስኩዋችው አራት ነጥቦች ለአንድነታችን መላላት ቁልፍ ከሆኑ መሰረታዊ ችግሮች አንዳንዶቹ ናችው:: በአሁኑ ሰሀት ኢትዮጲያ እየሄደች ያለችበት ጎዳና አስከፊ እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው:: ስለዚህ እኛ ኢትዮጲያውያን ከምን ጊዜ በበለጠ ለአንድነታችን እናም ለሀገራችን  ሰላም የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረግ ያለብን ሰሀት አሁን ነው::
ፍቅር ለኢትዮጲያ እዝብ!
written by; Gebraleu Tesfaye


No comments:

Post a Comment