Monday, November 18, 2013

ወያኔ ብርሀኑን የሰረቀበት ትውልድ


 
                ኑሮ ይሞላልኛል ህይወቴም ይስተካከላል እየተባለ ስደትን ካጎራበትነው ብዙ አመታት ተቆጠሩ:: በየ ባዳ ሀገሮችም ዘራችንን ዘርተን ማጨድ ከጀመርን ሰነበትን:: የአሁኑን አያድርገውና ስደት ለኢትዮጲያ ህዝብ ሽንፈት፣ መዋረድ እና ክብርን ማጣት ነበር ትርጉሙ:: በአሁኑ ሰሀት ስደት ወገኖቻችንን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የአካላዊ እና የስነልቦና ችግርችን አልፎ ተርፎም ሞትን እያመጣ ያለ ሲሆን የሚሰደዱት እህት እና ወንድሞቻችን ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ለምን እንደሆነ፣አስከፊ የስደት አይነቶችን እና ጉዳታችውን ለማየት እንሞክራለን ::

               የስደት ትንሽ የለውም፥ እጅግ በጣም ብዙ ኢትዮጲያን ስደተኞች በተለያዩ ሀገሮች የሚኖሩ ሲሆን የሚደርስባችው ችግርና እንግልት የትየለሌ ነው:: ስደት በሰፊው አፉን ከፍቶ ወደ ሀገራችን የመጣው በኢህአዴግ መንግስት አገዛዝ ስር ሲሆን:: በተለይ ወደ አረብ ሀገራት የሚሄዱት ኢትዮጲያን ቁጥር ከእለት ወደ እለት በከፍተኛ ፍጥነት ጨምሯል:: በአሁኑ ሰሀት ኢትዮጲያኖች የማይገኙበትን ቦታ ማግኘት አስችጋሪ ሲሆን ለመሰደድ የተለያዩ የመውጫ መንገዶች ወይም የትራንስፖርት አይነቶች ይጠቀማሉ:: ከሁሉም በላይ የሚያስፈራውና የከፋው መንገድ ከኢትዮጲያ ወደ ሱዳን ከዚያም ሊቢያ ገብተው ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚጠቀሙት መንገድ ነው:: በዚ መንገድ ቁጥራችው እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ኢትዮጲያን የሚያልቁ ሲሆን በሒወት ተርፈው ወደ አውሮፓ የሚገቡት ደግሞ የስነልቦና ቅውሰት ያጋጥማችዋል:: ይሄም የሚሆንበት ምክንያት በሚያሳልፉት የስደት ጉዞ በሚደርስባችው ኢሰባዊ ጥቃቶች ነው::በህገወጥ ሰውን የሚያጓጉዙ ሽፍቶች በተለያየ የስደት መንገድ ላይ የሚገኙ ሲሆን::ኑሮዋችውን የሚያስተዳድሩት ከእያንዳንዱ ስደተኛ ከሚዘርፉት ንብረት ነው::በአንዳንድ አጋጣሚወችም ስደተኞቹን እንደ ተያዥ አድርገው በውጪው አለም ወይም በኢትዮጲያ ከሚገኙ ዘመዶቻችው ከፍተኛ መጠን ያለው ብር ይጠይቃሉ:: የቤተሰቡ አባላት ብሩን በጊዜ ከፍለው ካልተገኙ ኢሰባዊ ድርጊቶችን በስደተኞቹ ላይ ይፈፀማሉ::እንደ አስገድዶ መድፈር፣መደብደብ በአንዳንድ አሰቃቂ ሁኔታዎችም የሰውነት ክፍላችውን አውጥተው መሸጥ ድረስ ይደርሳሉ::ከዚህም አልፈው አመለጥን ብለው የሚሄዱት ደግሞ በውሀ እጦት ሰሀራ በረሀ ላይ ይሞታሉ:: በጣም እድለኛ እና ጠንካራ የሆኑት ደግሞ ሊቢያ የሚደርሱ ሲሆን እዚያም የሚደርስባችው ስቃይ እና እንግልት አሰቃቂ ነው:: ከዚህ ሁሉ መከራ ያለፉት ደግሞ ተራችውን በመጠበቅ በጀልባ ወደ ጣሊያን ለ ማቅናት ይጠባበቃሉ:: ብዙን ጊዜ የሚጠቀሟችው ጀልባወች በአማካኝ 30᎔50 ሰዎችን መያዝ የሚችሉ ሲሆን ህገወጥ የሰው ደላላወች ግን ከ 300᎔500 ሰዎችን የጭኑባችዋል::ይህ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ስደተኞቹን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሲይሆን በጣም ጥቂት የሆኑት ጣሊያን ሲገቡ የተቀሩት የሻርክ እራት ሆነው ይቀራሉ::በቅርቡም በአለም ዙሪያ መነጋገሪያ የነበረው ዜና ይህ ነበር::









የሚያሳዝነው ግን ይሄን ሁሉ መከራና ችግር ተቋቁመው አውሮፓ ገባን ሲሉ የሚደርስባችው ችግሮች ሲሆኑ ከነሱም አንዳንዶቹ የስነልቦና አለመረጋጋት፣የጠበቁትን አለማግኘት እና የመኖሪያ ወረቀት አተው ከአንዱ አውሮፓ ሀገር ወደ ሌላው እያሉ እድሜያችውን ይጨርሳሉ::


         ሌላው የስደት አይነት ብዬ የምለው በሥራ ቪዛ ወደ አረብ ሀገር የሚሄዱ እህትና ወንድሞቻችን የሚሰደዱትን ስደት ነው:: በጣም ጥቂት የሆኑት በፕሮፌሽናል ሥራ ሲሄዱ የተቀሩት በቤት ውስጥ አገልግሎት ወይም ሰራተኛነት ነው የሚሄዱት::ሆኖም ግን በየቀኑ የምንሰማው ዜና ሰቅጣጭ እና አሳዛኝ ነው፣ ሴት እህቶቻችን ከፎቅ ላይ እየተወረወሩ ሲገደሉ ፣ ሲደፈሩ እና በጭንቀት ምክንያት እራሳችውን አንቀው ሲገድሉ የሚደርስላችው መንግስት የለም::በሌላ በኩል በሳውዲ አረብቢያ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ መንግስት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ዝም ማለቱ በጣም ያሳዝናል::
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
ይሄ ሁሉ መሳቀቅ፣ መደብደብ፣መገደል በህዝባችን ላይ የእለት ከለት ኑሮ ሆኖ ሳለ የሚሰደደው ህዝባችን ቁጥሩ መጨመሩ ምንን ያሳያል? መልሱ አስችጋሪ አይደለም፥ዘርዝረን ለማየት እንሞክር,
 

1, አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት በህዝባችን ላይ የሚያደርሰው ግፍ እና እንግልት እየጨመረ መሄዱ::
2, የሀገሪቱ ሀብት በጥቂት የወያኔ አባላት እና በተከታዮቻችው ቁጥጥር ስር መሆኑ::
3, ስልጣንን ለማቆየት ሲባል ህዝብን እርስ በእራሱ አቃቅሮ የህዝቡን የደንነት ስሜት በማጉደል::
4, ስለውጪው አለም ህዝቡ በቂ መረጃ እንዳይደርሰው በማድረግ ይሄንም የሚያደርጉበት ምክንያት መጠኑ በጣም ብዙ የሆነ ገንዘብ ከዲያስፖራው ስለሚያገኙ ነው::
5, በአደባባይ ህዝብን በመግደል ሀገሪቱ በጦር ወይም በጠበንጃ በሚያምኑ ሰዎች መመራቷን በማሳየት::
6, የህዝቡን የቢሔራዊ አንድነት ስሜት በመቦርቦር::
7, ለነፃነት የሚታገሉትን ባላጠፉት ጥፋት እስር ቤት በመወርወር::
8, የህዝቡን ምርጫ አለማክበር::
9,ለወጣቱ ቦታ አለመስጠት የመሳሰሉት ችግሮች ህዝቡን ሀገሩን እንደ ባዳ እንዲያይ አድርጎታል::
ፍቅር ለኢትዮጲያ ህዝብ እያልኩ!! በሰላም ፣በፍቅር፣በአንድነት ለኢትዮጲያ ነፃነት እንታገል እላለው!
written by: Gebraleu Tesfaye

 



No comments:

Post a Comment