Monday, February 23, 2015

የወያኔ ሚኒስተር ከ30 እስከ 40% የግንባታ ወጭ እንደሚዘረፍ አሳወቁ


1619564_780737625344507_8633815854074255488_n
የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና፣ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አምነዋል።
የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት በባቡር መስመር ግንባታ 2.3 ኪሜ የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 ሚልዮን በር ኪሳራ ደርሷል። የአደጋ መከላከያ ብረቶች የተሰሩት ከወጣላቸው የጥራት ደረጃ በሶስት እጅ ያነሱ ሆነው በመገኘታቸው ጉዳዩ ለቦርድ ሰብሳቢው ዶ/ር አርከበ እቁባይ ቢቀርብም ምላሺ ሰይሰጠው በመቅረቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገባ ማወቅ አለመቻሉን ገልጿል።
የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን ያቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ ምላሺ የሰጡት ሚኒስትር መኩሪያ ሃይሌ ፣ ችግሩ የተፈጠረው ለምርጫው ሲባል የባቡሩ ግንባታ እንደ ትልቅ የምርጫ ማሰመኛ በመያዙ ነው ።
የግንባታ ኢንዱስትሪው ከሚያወጣው ወጪ ከ30 እስከ 60 በመቶ የሚሆነው በሙስና ይባክናል ሲሉም ሚኒስትሩ አክለዋል። እንደዚያም ሆኖ በቅርቡ የተመረቀ የአዲስ አበባ መለስተኛ የባቡር ግንባታ፣ አገልግሎት ከመጀመሩ ከወዲሁ በርካታ የመፈራረስ ችግሮች እያጋጠሙት ነው። ለፖለቲካ ፍጆታና ለፕሮፖጋንዳ ሲባል ቶሎ ቶሎ እንዲሰራ ከማድረግ ዉጭ እነ አቶ አርከበ እቁባይ የሕዝቡን ፍላጎት ከግምት ያላስገቡ ሲሆን፣ አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች አልተወሰዱም። በዋናነት የባቡ ሃኢዱ ከተማዋን ለሁለት የከፈለ ሲሆን ከሃዲዱ በስተቀኝ እና በስተግራ ያሉ ነዋሪዎች ለመገናኘት እጅግ በጣም ብዙ ረቀት ለመጓዝ ተገደዋል።
ምንጭ: http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/17401

No comments:

Post a Comment