Sunday, September 21, 2014

ወጣትነት በአሁኗ ኢትዮጲያ


 
      ወጣትነት ማለት የአንዲት አገር ምሶሶ ወይም መሰረት መሆን የሚለውን ትርጉም ዕሰጠዋለው እንደኔ:: ባደጉት ሀገራት ውስጥ የአንድ ሀገር ሀፍት ወይም የኢኮኖሚ እድገት ሲለካ በዋናነት ወይም በመጀመሪያነት ኢሳብ ውስጥ የሚገባው ያላችውን እምቅ ሊሰራ የሚችል የወጣቱን ሀይል ማወቅ እና  ከዚያም በዋላ ወጣቱን እንዴት አድርገው ወደ ምርታማ አይል መንገድ ማሲያዝ እንደሚቻል በማወቅ ነው:: በምራባዊያን አለም ሞተር ለመኪና መንቀሳቀስ ከፍተኛውን አስተዋጾ እንደሚያደርግ ሁሉ ወጣቶችም ለሀገራችው ሞተር መሆናቸውን እናያለን:: ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል ብለን በምንጠይቅበት ጊዜ መልሱ በወቅቱ የነበሩት የሀገር አስተዳዳሪዎቸ እና ማሀበረሰቡ ለታዳጊው ትውልድ እና ለወጣቱ መሰጠት ያለበትን ትኩረት እና የአገር ፍቅር ሰጥተው ስላለፉ ነው:: ወደ ሀገራችን ኢትዮጲያ ስንመለስ ይሄ ነገር የተገላቢጦሽ ሆኖ እናገኘዋለን:: በይበልጥም ባለፉት 23 አመታት ውስጥ::
      ወጣትነት በኢትዮጲያ አስከፊና አሰቃቂ ሁኔታ ላይ የደረሰ ሲሆን በጣም የሚያሳዝነው ግን መንግስትም በዚው ጥፋት ላይ ከፍተኛውን ሚና መጫወቱ ነው:: እኔ በሙያዬ ፃሀፊ አይደለሁም ግን ወጣት እንደመሆኔ መጠን  በጓደኞቼ እና በአካባቤ የታዘብኩዋቸውን እና የሚያሳዝኑኝ ነገሮችን  እንደ ኢትዮጲያዊ በፃሁፍ መልክ ለአንባቢያን ላቅርብ ብዬ ነው ይሄን ፅሁፍ ለመፃፍ የተነሳሳሁት:: ከሁሉ አስቀድሜ ማየት የምፈልገው ጉዳይ ታዳጊ እፃናትን በተመለከት ነው:: ከአስራወቹ አመታት በፊት በአዲስ
አበባ ከተማ በጣም ብዙ  ለ እግር ኳስ እና ለተለያዩ ጨዋታወች መጫወቻ የሚጠቅሙ ሰፋፊ ሜዳዎች ነበሩ :: ልጆች ከትምህርት ቤት መልስ እና በእረፍት ቀናት ጊዜያቸውን እዚያ ያሳልፉ ነበር:: እንደሚታወቀው ባአብዛኛው የአዲስ አበባ ህዝብ ከእጅ ወደ አፍ ነው የሚኖረው ስለዚ ልጆቹን መዝናኛ ቦታ ወስዶ ማዝናናት ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅ እንዚ ሜዳዎች ተመራጭ ነበሩ:: እነርሱም ልጆችን በበጎ እና በእስፖርታዊ ስነምግባር ከመቅረጽ አኳያ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ:: አሁንስ እነዚ ሜዳዎች አሉ ወይ? መልሱ አብዛኛው ሜዳወች በመንግስት ባለስልጣናት ወይም ካድሬወች በችርቻሮ መልክ በየክፍለ ከተማው ቀርበው ለግል ባለሀፍቶች ተሸጠዋል:: አንዳንድ ሰዎች ለዚ ምክንያቱ የህዝብ ቁጥር መጨመር ነው ሚል ምክንያት ሊያቀርቡ ይችላሉ:: መልሱ ግን እንደ መንግስት ለሀገሪቷ የሚጠቅማትን ቀድሞ አለማወቅ ወይም እያወቁ የራስ ሆድን ለመሙላት ሲባል የወደፊቷ ኢትዮጲያን ማኮላሸት ነው::
     ሌላው መዋለ ህፃናት በተመለከተ ነው:: እፃናት ሲፈጠሩ አይምሮዋቸው ንጹ ሲሆን እዛ አይምሮ ላይ የሚፅፉት ቤተሰቦቹና አካባቢው ናችው:: ስለዚ መዋለ ህፃናት ሲከፈቱ መንግስት ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር ማድረግ ይኖርበታል:: በአሁኑ ሰአት እንደምናየው ከሆነ ግን መንግስት ይሄን እያደረገ አይደለም ኢሄም የራሱ የሆነ መጥፎ ጠባሳ በነገው የአገር ተረካቢ ላይ የሚጭር ነው:: ይሄን ስል ከመዋለ ህፃናት ትምህርት ቤቶቸ ጋር ተገቢውን የሆነ ግንኙነት አለማድረግ ወይም አንዳንድ በመንግስት በኩል ሊያገኟቸው የሚችሉዋችውን ጥቅሞች ምሳሌ:- ሰፊ የመጫወቻ ቦታ እንዲኖራችው ማድረግ እና ትምህርት ቤቱ የሚከፈትበት ቦታ ለህፃናት ተስሚሚ እንዲሆን በማድረግ, እነዚህን የመሳሰሉ እርዳታዎችን ባለማድረግ የእፃናቱ የልጅነት ጊዜ ያለ ጨዋታ ታጥቦ እንዲሄድ አድርጓል:: በአዲስ አበባ ውስጥ  ያሉ መዋለ ህፃናትን ብንመለከት በአንድ ሰው መኖሪያ የሚያክል ግቢ ውስጥ ወደ 60 ወይም ከዚያ በላይ ሚሆኑ እፃናት ታቅፈው ሲማሩ እናያለን ይህ ደግሞ እፃናቱ እንደ ልባቸው እንዳይራገጡ ያግዳቸዋል ይሄም በሚያድጉበት ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ስነ ልቦና ችግር ያመጣል::
       በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምርትቤቶች ከላይ የጠቀስኩዋችው ችግሮች ያሉ ሲሆን ወጣቶችሁ ከትምህርት ቤት መልስ ጊዜያችውን የሚያሳልፉበት ምንም አይነት ቦታ አለመኖሩ ደግም በጣም ያሳዝናል:: ይሄን ስል ኢትዮጲያ ደሀ ሀገር መሆኑዋን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው:: የተለየ የእግር ኳስ ሜዳ ወይም የባስኬት ማለቴ አይደለም:: ለማለት የፈለኩት ባዶ የእግርኳስ ሜዳ ከቀበሌው እና ከመንግስት ትብብር ጋር ብዙ እስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ሊደረግበት በቻለ ነበር:: በምትኩ መንግስት በቀበሌ ውስጥ አምስት ለአንድ ተደራጁ እያለ ገንዘቡን ለማንም ካድሬ ሆድ መሙያ ሲያውል ይታያል:: ታዲያ ከመዋለ እፃናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በንደዚ ሁኔታ ያደጉ ልጆች ሌላ አይነት የጌዜ ማሳለፌያ መንገድ ሲጠቀሙ እናያለን ይሄም በትምርትቤታቸው አጠገብ በየእለቱ የሚከፈቱትን የሺሻ፣የጫት፣ የአሽሽ፣ እና የመጠጥ  ቤቶችን ተጠቃሚ ይሆናሉ:: ከዚያም በለጋ እድሜያችው በሱስ በመለከፍ ለቤተሰብና ለሀገር እዳ ይሆናሉ ማለት ነው:: አሁን አሁንማ ይሄ የሱስ ነገር እንደ ስራ መታየት ጀምሯል:: ጫት እና  ሺሻ ቤት የከፈተ ሰው ሁሉ ልክ ምግቤት እንደከፈተ ሰው መከበር ጀምሯል::
        በዚ መልኩ ያደገ ወጣት እጣ ፋንታው ምንድን ነው? በሱስ የተለከፈ ወጣት በቀላሉ ተስፋ የሚቆርጥ ሲሆን ሰርቶ ለፍቶ ከመኖር ይልቅ በአቋራጭ አጭበርብሮ ወይም ነጥቆ መክበርን ይመርጣል:: ይሄ አይነቱ ፃባይ እራስ ወዳድ እና አገርን የማያከብር ትውልድ እንዲፈጠር ያደርጋል :: ይህ ማለት ስለኢትዮጲያ ብሎ የሚኖር ትውልድ እየመነመነ ይመጣል ማለት ነው:: ያም አገርን ለጥቅም አሳልፎ እስከመስጠት ይደርሳል:: በዚ በዚ ምክንያቶች በአሁን ሰሀት አብዛኛው ወጣት ልቡ ኢትዮጲያ ሳይሆን ባህር ማዶ ነው:: ይህም ስደትን እነደ አማራጭ እንዲያዩ አስገድዶዋቸዋል:: የስደት ጥሩ ባይኖረውም እይነቱ እና መንግዱ በጣም የተለያየ ነው::  በ የእለቱ በ ሺወች የሚቆጠር እህቶቻችን በስራ ስም ለ ተለያዩ አረብ ሀገሮች ገረድነት ይሸጣሉ:: ሌሎቹ ደግሞ አውሮፓ ገብተን ኢወታችንን እንቀይራለን በማለት በስንት በረሀ ሲደፈሩ፣ ሲደበደቡ፣ አልፎተርፎ በበሀር አውሬወች ሲበሉ ይከርማሉ:: ከሁሉም የሚያሳዝነው ግን እፃናት በጉዲፈቻ ስም በየሀገሩ ሲችረችሩ ነው:: ኢትዮጲያ በታሪኳ እንደዚ የተዋረደችበት ዘመን  የለም::
  ከላይ ለጠቀስቁዋቸው ችግሮች በአንደኛና በመጀመሪያ ደረጃ አላፊነቱን የሚወስደው ኢህአዴግ ነው፣ የኢትዮጲያ ህዝብ ባልመረጠው መንግስ መመራት ከጀመረ  አድሮ ሰንብቷል:: ስለዚ ኢህአዴግ ያልመረጣቸውን  ወይም የማይፈልጋቸውን ህዝብ   ለመቆጣጠር  የተለያዩ ሲስተሞቸ ቀይሰው ይንቀሳቀሳሉ:: ከዚያ ውስጥ አንደኛው እና ዋነኛው አገር ተረካቢውን ትውልድ ማኮላሸት ነው:: በየቦታው በየመንደሩ የሱስ ቤቶች እንዲስፋፉ በማድረግ ወጣቱን በራሱ የማይኮራ፣ የማይተማመን፣ ለአገሩ እንዳይቆም፣ ማንነቱን እንዳያውቅ፣ መብቱን እንዳይጠይቅ አድርገውታል:: በሺዎች የሚቆጠሩ የአርከበ ሱቆችን ምንግስት ግብር ለመቀበል እንዴት አድርጎ እንደሚቆጣጠር እናውቃለን ስለዚ ከልቡ ቢጥር ኖሮ አልባሌ የሱስ ቤቶችን ባሸገ ነበር:: ሁለተኛው መንግስት በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር የኢትዮጵያን እዝብ ለመሰለል ይጠቀማል ይሄ ገንዘብ ግን ስንት የእስፖርታዊ መንቀሳቀሻ መአከላትን በከፈተ ነበር:: በሶስተኛ ደረጃ ወጣቱን በየትምህርት ቤቱ በዘር ከፋፍሎ የወጣቱን የአገር ፍቅር ስሜትኡን እና አገር ውስጥ ሰርቶ የመብላት ደንነቱን አሟጦ፣ ወጣቱ በአራቱም አቅጣጫ አገር ጥሎ እንዲሰደድ አድርጎታል:: ይሄም በተዙዋዋሪም ለኢህአዴግ መንግስት የገቢ ምንጭ ሆኖ እድገት አመጣን ይላሉ::
    ከላይ ለተጠቀሱት ቸግሮች መፍቴው አንድ እና አንድ ነው እሱም ኢህአዴግን ማስወገድ ከዝያም ህዝብ የመረጠው መንግስ ማስቀመጥ ነው:: ኢትዮጲያን የመታደጊያ ሰሀት አሁን ነው:: እውቀት ያለህ በእውቀትህ  ገንዘብ ያለ በገንዘብህ ወጣት ከሆንክ በጉልበትህ ያሉትን አማራጮች በመጠቀም አገራችንን መታደግ ያለብን አሁን ነው :: ኢህአዴግ በጉልበት ፈርጣማ ይመስላል ግን ያለ ህዝብ ድጋፍ ምስጥ የበላው እንጨት መሆኑን አንዘንጋ::  ወጣቱ ትውልድ እያለቀ ነው! ሁላችንም ኢትዮጲያን ልንታደግ ይገባናል!
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!
በ ገብርኤሉ ተስፋዬ

No comments:

Post a Comment