(ጋዜጠኛ ሰለሞን ሙሉ ታፈሰ)
የነፃው ፕሬስ በገዢው ፓርቲ በሃይል እንዲዘጋ መደረጉን ተከትሎ ከአምስት አመት በላይ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ጀርባ ጐዳና ያድር እንደነበረ ታውቋል።
ጋዜጠኛ ሰሎሞን ባለፈው አመት ያለበትን ሁኔታ የሚገልፅ ዘገባ በአንድ ጋዜጠኛ አማካይነት በማህበራዊ ድረገፅ መውጣቱን ተከትሎ በለንደን የሚኖሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን የቤት ኪራይ እየከፈሉ ሲረዱት መቆየታቸው ታውቋል። በአሁን ሰአት ግን ይህ እገዛ በመቋረጡ ሰሎሞን ለጎዳና ሕይወት መዳረጉ ሲታወቅ በተጨማሪ በኪንታሮት በሽታ እየተሰቃየ እንደሚገኝ ማረጋገጥ ተችሎዋል።
በአብዛኛው ቀናት ዳቦ ሳይቀምስ እንደሚያሳልፍ በቅርብ የሚያቁት ጠቁመው፣ ጋዜጠኛ ሰሎሞን በባህርይው ቸገረኝ ብሎ ማንንም ሰው እንደማይጠይቅ አያይዘው ገልፀዋል። በተለይ በአሁኑ ወቅት የኪንታሮት በሽታው ከረሃብ ጋር ተደምሮ ክፉኛ የሰውነት መጎሳቆልና ክብደት መቀነስ እንደፈጠረበት ያስታወቁት እነዚህ ወገኖች ጋዜጠኛ ሰሎሞን ለአገሩ የከፈለውን መስዋእትነት በመረዳት አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙና በተለይ ሕክምና የሚያገኝበት ሁኔታ እንዲፈጠር የበኩላቸውን እርዳታ እንዲያደርጉለት ተማፅነዋል።
ጋዜጠኛ ሰሎሞን ሙሉ ታፈሰን በሚከተለው ስልክ ቁጥር በማግኘት መርዳት ይቻላል። +251 933694129
ምንጭ፣ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/12802
No comments:
Post a Comment