ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ በብሄራዊ ደረጃ የአድዋ በዓል፣ በኢሕአዴግ ዘመን፣ ከዚህ በፊት የተከበረበት ሁኔታ ብዙ እንዳለነበረ ይታወቃል። አገዛዙም አሁን በምን መልኩ በዓሉን ለማክበር እንዳቀደ ያሳወቀው አንዳች ነገር የሌለ ሲሆን፣ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ሌሎች ሲዘጋጁ፣ አብሮ ተቀላቅሎ ማክበር እንጂ ፣ መሰናክል መሆን እንዳልነበረበት ብዙዎች ይናገራሉ።
«አድዋን ለማክበር ስለፈለገ አይደለም። አገዝዙ መሰናክል እየፈጠረ ያለው» ያሉን በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ፣ በአዲስ አበባ ሰልፍ መደረጉ ስለሚያስፈራው እንደሆነ ይናገራሉ። «የአንድነት ፓርቲ በሁሉም የአዲስ አበባ ወረዳዎች መዋቅር አለው። በተጨማሪ መኢአድ እንዲሁም የአሥር ድርጅቶች ስብስብ የሆነው ትብብር አብረዉት አሉ። ስለዚህ አንድነት በሚጠራቸዉ ስልፎችና ስብሰባዎች ብዙዎች እንደሚገኙ የታወቀ ነዉ » ያሉት እኝህ ተንታኝ «ቢሆንም እስከአሁን በአንድነት በየቦታዉ የተደረጉ ሰልፎች ሁሉ ሰላማዊ ነበሩ። አንዲት ጠጠር አልተወረወር፣ የጠፋ ሕይወት፣ የወደመ ንብረት የለም። ሰልፈኛው በሰላም ወጥጦ ነው በሰላም የተመለሰው» ሲሉ የሕዝቡ ሰላማዊነት በማስረዳት አገዛዙ መፍራት እንደሌለበት የናገራሉ።
የአንድነት ፓርቲ ከዚህ በኋላ ምን አይነት ምላሽ እንደሚሰጥ የሚገልጽ መረጃ እስከአሁን አልደረሰንም።
ምንጭ፣ http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/13417
No comments:
Post a Comment