Friday, April 11, 2014

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ቀዳሚ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ሆነ

 
ሚያዚያ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ በ2005 በጀት ዓመት ከኤክስፖርት ካገኘችው ገቢ ይበልጥ በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊን በሐዋላ መልክ ያገኘችው ገቢ እንደሚበልጥ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ የጹሑፍ መረጃ አመልክቷል።
መረጃው እንደሚያሳየው በ2005 በጀት ዓመት አገሪቱ ከኤክስፖርት 3.1 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን ኢትዮጵያውያን ከውጭ ከሚልኩት ገንዘብ ደግሞ 3 ቢሊዮን 9 መቶ ሚሊዮን ዶላር አግኝታለች፡፡ በ2004 በጀት ዓመትም ከሐዋላ እና ከኤክስፖርት ያገኘቸው ገቢ ተመሳሳይ ማለትም እያንዳንዳቸው 3.2 ቢሊየን ዶላር መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡
መረጃው የሐዋላ ገንዘብ በፍጥነት እያደገ ሲመጣ በአንጻሩ አገሪቱ እንደቡና ፣የቅባት እህሎችና ጥራጥሬና የመሣሠሉትን በመላክ የምታገኘው ዓመታዊ ገቢ እያሽቆለቆለ መምጣቱን ያሳያል፡፡
ESAT Radio Tuesday November 19, 2013የኤክስፖርት ዘርፍ ባለፉት ሶስት ዓመታት መንግስት ከያዘው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አንጻር አፈጻጸሙ ደካማ መሆኑን መረጃው የሚጠቁም ሲሆን ከገቢ ንግድ ጋር ያለው የንግድ ሚዛን ጉድለት እየሰፋ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን ያመለክታል፡፡በ2004 የገቢ ንግድ(ኢምፖርት) መጠን 11 ቢሊየን ዶላር ሲሆን በ2005 ዓ.ም ወደ 11. ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ብሎአል፡፡ የሸቀጦች የወጪ ንግድ ገቢ ከሸቀጦች የገቢ ንግድ ወጪ ጋር ሲነጻጸር በሚጠበቀው ደረጃ ዕድገት ባላማሳየቱ የንግድ ሚዛን ጉድለቱ በ2003 ዓ.ም ከነበረበት 5 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በ2005 ዓ.ም ወደ 8. ቢሊየን 400 ሚሊዮን ዶላር እንዲሰፋ ማድረጉን መረጃው ጠቁሟል፡፡ ይህን የንግድ ሚዛን ጉድለት ለማጥበብ መፍትሔው ኤክስፖርትን ማሳደግ ነውም ብሏል፡፡
እጅግ የተለጠጠ ነው በሚል ትችት የሚቀርብበት የመንግስት የአምስት ዓመቱ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት ታሳቢ

Thursday, April 10, 2014

ሰበር ዜና – የአዲስ አበባ መስተዳድር የእውቅና ደብዳቤ ጻፈ ፓርቲው አልተስማማም::

 
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ሊያደርገው ለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ የመስተዳድሩ የሰላማዊ ሰልፍና ማሳወቂያ ክፍል ዘግይቶ በጻፈው ደብዳቤ የሰልፉ ቀን በሌላ ፕሮግራም መያዙን በመጥቀስ የቀን ለውጥ እንዲደረግ መጠየቁ አይዘነጋም፡፡
ፓርቲው የቀረበውን አስተያየት በመቀበል ሰልፉ ለሚያዚያ 5 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲደረግ መወሰኑን በመግለጽ ለመስተዳድሩ አሳውቋል፡፡ሆኖም መስተዳድሩ ዕለቱ በታላቁ ሩጫ መያዙን በመጥቀስ ለፖሊስ ጥበቃ ለመስጠት የሚያስቸግረው በመሆኑ ሰልፉ ለሚያዚያ 4 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲደረግ የእውቅና ደብዳቤ ጽፏል፡፡ፓርቲው በመስተዳድሩ የተሰጠውን እውቅና አለመቀበሉን ለማሳወቅ ከፍተኛ አመራሮቹን ወደ ከንቲባው ጽ/ቤት ልኳል፡፡
በአሁኑ ሰዓትም አመራሮቹና የመስተዳድሩ ሰዎች በጉዳዩ ዙሪያ እየተነጋገሩ ነው፡
Andinet AA Application

ምንጭ፣ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/28987

Wednesday, April 9, 2014

የግብጹ እጩ ፕሬዘዳንት ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት የማይቀር መሆኑን አሳወቁ!

በግብፅ በቅርቡ ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ራሳቸውን በዕጩነት ያቀረቡት የሕግ ባለሙያው ሞርታዳ ማንሱር፣ ‹‹ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ካላቆመች ወታደራዊ ኃይል እጠቀማለሁ፤›› በማለት አስጠነቀቁ፡፡
አወዛጋቢና ስሜታዊ እንደሆኑ በይፋ የሚታወቁት የሕግ ባለሙያና ከሳምንት በፊት ደግም ዛማሌክ ለተባለው ታዋቂ የግብፅ እግር ኳስ ቡድን ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ማንሱር፣ ማስጠንቀቂያውን ያስተላለፉት ባለፈው እሑድ ፕሬዚዳንታዊ ውድድርን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ጦነርት በመክፈት የግብፅ ሕዝብን ጥቅም እንደሚያስከብሩም ተናግረዋል፡፡ የዓባይ ወንዝን በተመለከተ እ.ኤ.አ. በ1929 እና በ1959 የተፈረሙ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መኖራቸውን ያስታወሱት ማንሱር፣ ኢትዮጵያ ይህንን ስምምነት ወደጎን ብላ ግንባታውን መቀጠሏን ተቃውመዋል፡፡
‹‹ኢትዮጵያና ግብፅን ከማግባባት የተቆጠቡ ዓለም አቀፍ ተቋማት አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ በአቋሟ ፀንታ ግድቡን መገንባት ቀጥላለች፡፡ ኢትዮጵያ ወታደራዊ አቅም እንዳላት በመግለጽ ግብፅን እያስፈራራች ነው፡፡ ነገር ግን ግብፅም ወታደራዊ አቅም አላት፤›› ብለዋል፡፡
Mortada Mansour
Mortada Mansour
ከኢትዮጵያ ጀርባ እስራኤል እንዳለች የተናገሩት ማንሱር፣ ይህ ቢሆንም የግብፅን የውኃ ድርሻ ለመገደብ የሚደረግ ጥረት ለግብፃውያን የሞትና ሽረት ጉዳይ ነው ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
‹‹ወደ ግድቡ የጦር ጄኔራሎቻቸውን ወስደው እየፎከሩ ግብፅ ከመጣች የሚሉ ከሆነ ግብፅም ጄኔራሎችና ተዋጊ ጄቶች እንዳላት ይወቁ፡፡ ግብፅ ጠብታ ውኃ እንዲጎድልባት አትፈቅድም፡፡ በዚህ ጉዳይ አንደራደርም፡፡ ይህ ለግብፃውያን ሞትና ሽረት ነው፤›› ብለዋል፡፡ ለግብፅ ፕሬዚዳንትነት ራሳቸውን በዕጩነት ያቀረቡት ማንሱር ገና ወደ ውድድር ለመግባት የግብፅ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ኮሚሽንን ይሁንታ ማግኘት እንደሚጠበቅባቸው የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
የሕግ ባለሙያው ማንሱር የኮሚሽኑን ይሁንታ እንኳን ማግኘት ቢችሉ የሚወዳደሩት በቅርቡ ከግብፅ መከላከያ ሚኒስትርነትና

Monday, April 7, 2014

Independent Magazine in Ethiopia Shut Down


 
By Betre Yacob
ebonyOne of the few independent Ethiopian magazines, Ebony, has been shut down after 6 years of publishing, putting many full-time and part-time workers out of a job. Tessema Dessalgn, the share holder and editor in chief of the magazine, told to journalists today that they had closed the magazine because of exaggerated tax.
“We hadn’t other option but to shut down the magazine” Tessema told to journalists. “The tax was so exaggerated, and impossible to us to manage. We didn’t have even the half of the requested amount”, he explained. Tessema said that the tax had come while they had already been in a serious financial

Thursday, April 3, 2014

“የእሪታ ቀን” እንዲሰረዝ የኢህአዴግ መንግስት ጠየቀ (ደብዳቤውን ይዘናል)

(EMF) በአንድነት ፓርቲ አማካኝነት – መጋቢት 28 ቀን፣ 2006 ሊደረግ የነበረው የ እሪታ ቀን በአዲስ አበባ መስተዳድር ተቃውሞ ገጥሞታል። ከአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የወጣው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ከሆነ፡ ሰልፈኞቹ የሚሄዱበት ስፍራ የተከለከለ በመሆኑ የሰላማዊ ሰልፉን ጥያቄ እውቅና አንሰጠውም ብሏል። ቀበና መድሃኔአለም ከሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ተነስቶ በፒያሳ እና ቸርችል ጎዳና አድርጎ፤ ጥቁር አንበሳ ድላችን ሃውልት ጋር ይጠናቀቅ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ፤ የአዲስ አበባ አስተዳደር ጽ/ቤት… መንገዱ የባቡር መስመር የሚዘረጋበት፣ ትራፊክ የሚበዛበት እና ሆስፒታል የሚገኝበት መሆኑን በመግለጽ ነው፤ ለሰልፉ እውቅና የነፈገው። ይህ በ’ንዲህ እንዳለ የአንድነት ፓርቲ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰልፉን የሚያካሂድ መሆኑን

Wednesday, April 2, 2014

የሰው ለሰው ድራማ 6 ሚሊዮን ብር የት ደረሰ? * በአካውንቱ ውስጥ 78 ብር ብቻ ነው የተገኘው


 
sew le sew
በርናባስ
(ለሎሚ መጽሔት እንደጻፈው)
በኢትዮጵያ ውስጥ ጥበብ በሁለት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፡፡ የመጀመሪያው በአሁን ሰዓት ደራሲዎችም ሆኑ የጥበብ ባለሙያዎች አዲስ ነገር ይዘው መምጣት ካለመቻላቸው ጋር በተያያዘ በህብረተሰቡ ዘንድ ቦታ እያጣ መምጣቱ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደረጃ ደግሞ ጥበብን ንግድ ያደረጉ አርቲስቶች መበራከት በራሳቸው አንገት ላይ ሸምቀቆ በማሰር ጥበቡን እየገደሉት ይገኛሉ፡፡ በአሁን ወቅት ምናልባትም ጥበብ ያለ ንግድ የታባቱ ያለ የጥበብ ሥራን ከተመለከትን ያለምንም ጥርጥር ‹‹ሠው ለሠው›› ድራማን በግንባር ቀደምትነት ማየት ይቻላል፡፡ ሲጀመር በርካቶች ለመመልከት የተሻሙበት ዛሬ ላይ ግን ‹‹ይህ ነገር አያልቅም እንዴ?›› ተብሎ የተለያየ ሂስ እየተሰጠበት ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ ውስጥ እንደ ሠው ለሠው የዘመኑ ማለቂያ አጥቶና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም መረን የለቀቀ ዕድል የሰጠው የለም፡፡
መቼም በየሣምንቱ እንደምንመለከተው ከሆነ የሠው ለሠው ድራማ ሃሣብ አልቆበት እዛው በዛው መዳከሩ ብቻ ሣይሆን፣ ገንዘብ የማባከንና የመዝናናትንም ነገር እየተመለከትን ነው፡፡ ከድራማው መውረድ ጐን ለጐን ካላስፈላጊ ታሪኮችም ጋር ተደማምሮ አሁን በተለይ ተዋናዮቹ እራስን የማዝናናት ጊዜ ላይ የደረሱ ይመስላል፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ ምናልባትም ለሌሎች ባይገባም መስፍን

በሐዋሳ ከተማ 2 ትምህርት ቤቶች በቋንቋ የተነሳ ብጥብጥ ተነስቶ ሰዎች ቆሰሉ


 
hawasa federal policeከዳዊት ሰለሞን
በሀዋሳ ከተማ ታቦር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚማሩ የሲዳማ ተወላጆች የሚኒ ሚዲያ ፕሮግራም በሲዳመኛ ቋንቋ ይተላለፍ፣ ታቦር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚለውን ታፔላ በሲዳመኛ ቋንቋ ይጻፍ በሚል መነሻና ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ረብሻ ተፈጥሮ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ግቢው ሲጠጉ ተማሪዎቹ ድንጋይ በመወርወር በርካታ ፖሊሶች ቆስለዋል፡፡ ፖሊሶቹ በወሰዱት ርምጃ ብዙዎች ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡
በሐዋሳ ከተማ በሚገኙ ሁለት የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች እንደቀሰቀሱት በተገመተ ረብሻ ከፍተኛ ጉዳት በተማሪዎችና በአስተማሪዎች ላይ መድረሱ ተሰምቷል፡፡
የትምህርት ቤቱ የመማሪያ ቋንቋ እንዲለወጥ በጠየቁ የኦሮሞ ተወላጆችና በሲዳማ ተወላጆች መካከል ረብሻው መቀስቀሱን ከስፍራው ያናገርኳቸው ሰዎች በስልክ ገልጸውልኛል፡፡ ረብሻውን ለማብረድ ፖሊሶች መሳሪያ መተኮስ በመጀመራቸውም የተጎዱ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ሐዋሳ ውስጥ የተኩስ ድምጽ ያለ ማቋረጥ እንደሚሰማም ምንጮች ተናግረዋል።